Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 8:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 እነሆ አስ​ማት የማ​ይ​ከ​ለ​ክ​ላ​ቸ​ውን የሚ​ገ​ድሉ እባ​ቦ​ችን እሰ​ድ​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ይነ​ድ​ፉ​አ​ች​ኋል፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 “እነሆ፤ በመካከላችሁ መርዘኛ እባቦችን፣ የአስማተኛ ብልኀት የማይገታቸው እፉኝቶችን እሰድዳለሁ፤ እነርሱም ይነድፏችኋል፤” ይላል እግዚአብሔር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 እነሆ፥ መርዛቸውን አስማት የማያረክሰው እባቦችንና እፉኝቶችን በእናንተ መካከል እልካለሁ፤ እነርሱም ይነድፉአችኋል፥” ይላል ጌታ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ተጠንቀቁ! እነሆ የአስማተኛ ድግምት ሊገታቸው የማይችል መርዘኛ እባቦችንና እፉኝቶችን በመካከላችሁ እልካለሁ፤ እነርሱም ይነድፉአችኋል።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 እነሆ፥ አስማት የማይከለክላቸውን እባቦችንና እፉኝቶችን እሰድድባችኋለሁ፥ እነርሱም ይነድፉአችኋል።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 8:17
9 Cross References  

እባብ ቢነ​ድፍ ባለ መድ​ኀ​ኒ​ትም ባያ​ድን ባለ መድ​ኀ​ኒቱ አይ​ጠ​ቀ​ምም።


በራብ ያል​ቃሉ፤ ለሰ​ማይ ወፎ​ችም መብል ይሆ​ናሉ፤ ኀይ​ላ​ቸ​ውም ይደ​ክ​ማል፥ ከም​ድር ይጠፉ ዘንድ የም​ድር አራ​ዊ​ትን ጥርስ፥ ከመ​ርዝ ጋር እል​ክ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሕ​ዝቡ ላይ የሚ​ገ​ድሉ እባ​ቦ​ችን ሰደደ፤ ሕዝ​ቡ​ንም ነደፉ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ብዙ ሰዎች ሞቱ።


የፈረሶቹ ሥልጣን በአፋቸውና በጅራታቸው ነውና፥ ጅራታቸው እባብን ይመስላልና፥ ራስም አላቸው፤ በእርሱም ይጐዳሉ።


በቀ​ር​ሜ​ሎስ ራስ ውስጥ ቢሸ​ሸጉ ፈልጌ ከዚያ አወ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በባ​ሕ​ሩም ጥልቅ ውስጥ ከዐ​ይኔ ቢደ​በቁ በዚያ እባ​ቡን አዝ​ዛ​ለሁ፤ እር​ሱም ይነ​ድ​ፋ​ቸ​ዋል፤


ከአ​ን​በሳ ፊት እንደ ሸሸ፥ ድብም እን​ዳ​ገ​ኘው ሰው፥ ወደ ቤትም ገብቶ እጁን በግ​ድ​ግዳ ላይ እን​ዳ​ስ​ደ​ገ​ፈና እባብ እንደ ነደ​ፈው ሰው ይሆ​ናል።


ፍል​ስ​ጥ​ኤም ሆይ፥ ከእ​ባቡ ዘር እፉ​ኝት ይወ​ጣ​ልና፥ ፍሬ​ውም የሚ​በ​ር​ርና እሳት የሚ​መ​ስል እባብ ይሆ​ና​ልና፥ የኀ​ይ​ላ​ችሁ ቀን​በር ተሰ​ብ​ሮ​አ​ልና ሁላ​ች​ሁም ደስ አይ​በ​ላ​ችሁ።


ማታ ይመ​ለሱ እንደ ውሾ​ችም ይራቡ፥ በከ​ተ​ማም ይዙሩ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements