Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 7:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 “ስለ​ዚህ እነሆ ስፍራ ከማ​ጣት የተ​ነሣ በቶ​ፌት ይቀ​በ​ራ​ሉና የታ​ረ​ዱት ሰዎች ሸለቆ ይባ​ላል እንጂ የቶ​ፌት ኮረ​ብታ ወይም የሄ​ኖም ልጅ ሸለቆ ዳግ​መኛ የማ​ይ​ባ​ል​በት ዘመን ይመ​ጣል፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 ስለዚህ አስተውሉ፤ ይላል እግዚአብሔር፤ ስፍራ እስከማይገኝ ድረስ ሙታንን በቶፌት ስለሚቀብሩ፣ የዕርድ ሸለቆ እንጂ ከእንግዲህ ቶፌት ወይም የሄኖም ልጅ ሸለቆ ተብሎ የማይጠራበት ጊዜ ይመጣል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 ስለዚህ፥ እነሆ፥ ስፍራ ከመታጣቱ የተነሣ በቶፌት ይቀበራሉና የእርድ ሸለቆ ይባላል እንጂ ቶፌት ወይም የሄኖም ልጅ ሸለቆ ዳግመኛ የማይባልበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል ጌታ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 ስለዚህ የዚያ ቦታ ስም የቤን ሂኖም ሸለቆ ወይም ቶፌት መባሉ ቀርቶ የዕርድ ሸለቆ ተብሎ የሚጠራበት ጊዜ ይመጣል፤ ሌላ የመቃብር ስፍራ ስለማይገኝ ያ ሸለቆ ራሱ የሕዝቡ መቃብር ይሆናል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 ስለዚህ፥ እነሆ፥ ስፍራ ከማጣት የተነሣ በቶፌት ይቀበራሉና የእርድ ሸለቆ ይባላል እንጂ ቶፌት ወይም የሄኖም ልጅ ሸለቆ ዳግመኛ የማይባልበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 7:32
10 Cross References  

እን​ዲ​ህም ትላ​ቸ​ዋ​ለህ፦ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የሸ​ክላ ማድጋ እን​ደ​ሚ​ሰ​ባ​በር ደግ​ሞም ይጠ​ገን ዘንድ እን​ደ​ማ​ይ​ቻል፥ እን​ዲሁ ይህን ሕዝ​ብና ይህ​ችን ከተማ እሰ​ብ​ራ​ለሁ፤ የሚ​ቀ​በ​ሩ​በ​ትም ስፍራ ሌላ የለ​ምና በቶ​ፌት ይቀ​በ​ራሉ።


ስለ​ዚህ እነሆ ይህ ስፍራ የእ​ርድ ሸለቆ ይባ​ላል እንጂ ቶፌት ወይም የሄ​ኖም ልጅ ሸለቆ ዳግ​መኛ የማ​ይ​ባ​ል​በት ዘመን ይመ​ጣል፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ሰው ሁሉ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን ለሞ​ሎክ በእ​ሳት እን​ዲ​ሠዋ በሄ​ኖም ልጅ ሸለቆ ቆሞ የነ​በ​ረ​ውን ጣፌ​ትን ርኩስ አደ​ረ​ገው።


የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቤቶ​ችና የይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት ቤቶች እንደ ቶፌት የረ​ከሱ ይሆ​ናሉ፤ እነ​ዚ​ያም በሰ​ገ​ነ​ታ​ቸው ላይ ለሰ​ማይ ሠራ​ዊት ሁሉ ያጠ​ኑ​ባ​ቸው፥ ለሌ​ሎ​ችም አማ​ል​ክት የመ​ጠጥ ቍር​ባን ያፈ​ሰ​ሱ​ባ​ቸው ቤቶች ሁሉ ይፈ​ር​ሳሉ።”


እኔም ያላ​ዘ​ዝ​ሁ​ት​ንና በልቤ ያላ​ሰ​ብ​ሁ​ትን፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን በእ​ሳት ያቃ​ጥሉ ዘንድ በሄ​ኖም ልጅ ሸለቆ ያለ​ች​ውን የቶ​ፌ​ትን መሥ​ዊ​ያ​ዎች ሠር​ተ​ዋል።


የኮ​ረ​ብታ መስ​ገ​ጃ​ዎ​ቻ​ች​ሁን አፈ​ር​ሳ​ለሁ፤ በእጅ የተ​ሠሩ የዕ​ን​ጨት ምስ​ሎ​ቻ​ች​ሁ​ንም አጠ​ፋ​ለሁ፤ ሬሳ​ች​ሁ​ንም በጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ችሁ ሬሳ​ዎች ላይ እጥ​ላ​ለሁ፤ ነፍ​ሴም ትጸ​የ​ፋ​ች​ኋ​ለች።


በከ​ር​ሲት በር መግ​ቢያ አጠ​ገብ ወዳ​ለው ወደ ሄኖም ልጅ ሸለቆ ሂድ፥ በዚ​ያም የም​ነ​ግ​ር​ህን ቃል አን​ብብ፤ እን​ዲ​ህም በል፦


የአ​ስ​ሬ​ሞ​ትም ሸለቆ ሁሉ እስከ ቄድ​ሮን ወንዝ ድረስ በም​ሥ​ራቅ በኩል እስ​ካ​ለው እስከ ፈረስ በር ማዕ​ዘን ድረስ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ ይሆ​ናል፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ነ​ቀ​ልም፤ አይ​ፈ​ር​ስ​ምም።


መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቻ​ች​ሁም ይፈ​ር​ሳሉ፤ የፀ​ሐይ ምስ​ሎ​ቻ​ች​ሁም ይሰ​በ​ራሉ፤ የተ​ገ​ደሉ ሰዎ​ቻ​ች​ሁ​ንም በጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ችሁ ፊት እጥ​ላ​ለሁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements