Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 7:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 አን​ተም፦ የአ​ም​ላ​ኩን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ያል​ሰማ፥ ተግ​ሣ​ጽ​ንም ያል​ተ​ቀ​በለ ሕዝብ ይህ ነው፤ እው​ነት ጠፍ​ቶ​አል፤ ከአ​ፋ​ቸ​ውም ተቈ​ር​ጦ​አል ትላ​ቸ​ዋ​ለህ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ስለዚህ እንዲህ በላቸው፤ ‘ይህ ሕዝብ አምላኩን እግዚአብሔርን ያልታዘዘ፣ ምክሩን ያልተቀበለ ወገን ነው፤ እውነት ጠፍቷል፤ ከአንደበታቸውም ሸሽቷል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 አንተም፦ “የአምላኩን የጌታን ድምፅ ያልሰማ፥ ተግሣጽንም ያልተቀበለ ሕዝብ ይህ ነው፤ እውነት ጠፍቶአል ከአፋቸውም ታጥቶአል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ይህ ሕዝብ ለእኔ ለአምላኩ የማይታዘዝና ከቅጣቱም ሥነ ሥርዓትን መማር የማይፈልግ ሆኖአል፤ በዚህ ምክንያት እውነት ጨርሳ ጠፍታለች፤ ስለ እርስዋ በአንደበቱ የሚያነሣ እንኳ የለም።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 አንተም፦ የአምላኩን የእግዚአብሔርን ቃል ያልሰማ፥ ተግሣጽንም ያልተቀበለ ሕዝብ ይህ ነው፥ እውነት ጠፍቶአል ከአፋቸውም ተቈርጦአል ትላቸዋለህ።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 7:28
21 Cross References  

ድምፅን አልሰማችም፥ ተግሣጽንም አልተቀበለችም፣ በእግዚአብሔርም አልታመነችም፥ ወደ አምላክዋም አልቀረበችም።


ፊታ​ቸ​ው​ንም ሳይ​ሆን ጀር​ባ​ቸ​ውን ወደ እኔ መለሱ፤ እኔም በማ​ለዳ ተነ​ሥቼ ሳስ​ተ​ም​ራ​ቸው ተግ​ሣ​ጽን ይቀ​በሉ ዘንድ አል​ሰ​ሙም።


የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ዕውቀት ለሚያደርጋት ሁሉ መልካም ናት። እግዚአብሔርን መፍራት የዕውቀት መጀመሪያ ነው፥ ሰነፎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ።


እኔም- ይፈሩኛል፥ ተግሣጽንም ይቀበላሉ፣ ካዘዝኋትም ሁሉ ከዓይንዋ ምንም አይጠፋም ብዬ ነበር፣ እነርሱ ግን በማለዳ ተነሥተው ድርጊታቸውን ሁሉ አረከሱ።


እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሆይ! እው​ነ​ትና ምሕ​ረት፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ማወቅ በም​ድር ስለ​ሌለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ድር ላይ የሚ​ኖ​ሩ​ትን ይወ​ቅ​ሳ​ልና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።


ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፤ ነፍሴ ከአ​ንቺ እን​ዳ​ት​ለይ፥ አን​ቺ​ንም ባድ​ማና ወና እን​ዳ​ላ​ደ​ር​ግሽ፥ ተግ​ሣ​ጽን ተቀ​በዪ።


አቤቱ! ዐይ​ኖ​ችህ ለሃ​ይ​ማ​ኖት አይ​ደ​ሉ​ምን? አንተ ቀሥ​ፈ​ሃ​ቸ​ዋል፤ ነገር ግን አላ​ዘ​ኑም፤ ቀጥ​ቅ​ጠ​ሃ​ቸ​ው​ማል፤ ነገር ግን ተግ​ሣ​ጽን እንቢ አሉ፤ ፊታ​ቸ​ውን ከድ​ን​ጋይ ይልቅ አጠ​ን​ክ​ረ​ዋል፤ ይመ​ለ​ሱም ዘንድ እንቢ አሉ።


“በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም መን​ገ​ዶች ሩጡ፤ ተመ​ል​ከ​ቱም፤ ዕወ​ቁም፤ በአ​ደ​ባ​ባ​ይ​ዋም ፈልጉ፤ ፍር​ድን የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን እው​ነ​ት​ንም የሚ​ሻ​ውን ሰው ታገኙ እንደ ሆነ ይቅር እላ​ቸ​ዋ​ለሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ልጆ​ቻ​ች​ሁን በከ​ንቱ ቀሥ​ፌ​አ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ተግ​ሣ​ጼን አል​ተ​ቀ​በ​ላ​ች​ሁም፤ ሰይ​ፋ​ችሁ እን​ደ​ሚ​ሰ​ብር አን​በሳ ነቢ​ያ​ቶ​ቻ​ች​ሁን በል​ቶ​አል፤ በዚ​ህም አል​ፈ​ራ​ች​ሁ​ኝም።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት የዋህ መን​ፈስ ነው፥ የተ​ዋ​ረ​ደ​ው​ንና የዋ​ሁን ልብ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ን​ቅም።


እኔም፥ “የመ​ለ​ከ​ቱን ድምፅ አድ​ምጡ” ብዬ ጠባ​ቂ​ዎ​ችን ሾም​ሁ​ባ​ቸው፤ እነ​ርሱ ግን፥ “አና​ዳ​ም​ጥም” አሉ።


ቃሌን ይሰሙ ዘንድ እንቢ ወደ አሉ ወደ አባ​ቶ​ቻ​ቸው ኀጢ​አት ተመ​ለሱ፥ ያመ​ል​ኩ​አ​ቸ​ውም ዘንድ እን​ግ​ዶ​ችን አማ​ል​ክት ተከ​ተሉ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤትና የይ​ሁዳ ቤት ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ቃል ኪዳን አፈ​ረሱ።


እነ​ርሱ ግን አል​ሰ​ሙም፤ ጆሮ​አ​ቸ​ው​ንም አላ​ዘ​ነ​በ​ሉም፤ እን​ዳ​ይ​ሰ​ሙና ተግ​ሣ​ጼን እን​ዳ​ይ​ቀ​በ​ሉም ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ይልቅ አን​ገ​ታ​ቸ​ውን አደ​ነ​ደኑ።”


እስከ መቼ በነ​ፍሴ ኀዘ​ንን አኖ​ራ​ለሁ? እስከ መቼ ልቤ ሁል​ጊዜ ትጨ​ነ​ቅ​ብ​ኛ​ለች? እስከ መቼ ጠላ​ቶች በላዬ ይታ​በ​ያሉ?


ዐመ​ፀኛ ወገን፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ ለመ​ስ​ማት እምቢ ያሉ የሐ​ሰት ልጆች ናቸ​ውና፤


እነ​ርሱ ሁሉ እጅግ ደን​ቆ​ሮ​ዎች ናቸው፤ በጠ​ማ​ማ​ነት ይሄ​ዳሉ፤ ሁሉም እንደ ናስና ብረት የዛጉ ናቸው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements