Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 51:60 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

60 ሠራ​ያም የቤቱ አዛዥ ነበረ፤ በባ​ቢ​ሎ​ንም ላይ የሚ​መ​ጣ​ውን ክፉ ነገር ሁሉ፥ ስለ ባቢ​ሎን የተ​ጻ​ፈ​ውን ይህን ቃል ሁሉ ኤር​ም​ያስ በአ​ንድ መጽ​ሐፍ ላይ ጻፈው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

60 ኤርምያስ ስለ ባቢሎን ጽፎ ያስቀመጠውን ሁሉ፣ በባቢሎን ላይ የሚመጣውን ጥፋት ሁሉ በብራና ጥቅልል ላይ ጻፈው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

60 በባቢሎንም ላይ የሚመጣውን ክፉ ነገር ሁሉ፥ ስለ ባቢሎን የተጻፈውን ይህን ቃል ሁሉ፥ ኤርምያስ በመጽሐፍ ላይ ጻፈው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

60 በባቢሎን ላይ የሚመጣውን ጥፋት እንዲሁም ስለ እርስዋ የተነገረውን ቃል በመጽሐፍ ጻፍኩ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

60 በባቢሎንም ላይ የሚመጣውን ክፉ ነገር ሁሉ፥ ስለ ባቢሎን የተጻፈውን ይህን ቃል ሁሉ፥ ኤርምያስ በመጽሐፍ ላይ ጻፈው።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 51:60
11 Cross References  

ኤር​ም​ያ​ስም ሌላ ክር​ታስ ወሰደ፤ ለኔ​ር​ዩም ልጅ ለጸ​ሓ​ፊው ለባ​ሮክ ሰጠው፤ እር​ሱም የይ​ሁዳ ንጉሥ ኢዮ​አ​ቄም በእ​ሳት ያቃ​ጠ​ለ​ውን የመ​ጽ​ሐ​ፉን ቃል ሁሉ ከኤ​ር​ም​ያስ አፍ ጻፈ​በት፤ ደግ​ሞም እንደ ቀድ​ሞው ያለ ቃል ብዙ ቃል ተጨ​መ​ረ​በት።


አሁን ተቀ​መጥ፤ ለሚ​መ​ጣ​ውም ዘመን ለዘ​ለ​ዓ​ለም እን​ዲ​ሆን በሰ​ሌዳ ላይ በመ​ጽ​ሐ​ፍም ውስጥ ጻፍ​ላ​ቸው።


እንግዲህ ያየኸውን አሁንም ያለውን ከዚህም በኋላ ይሆን ዘንድ ያለውን ጻፍ።


እንዲሁም “የምታየውን በመጽሐፍ ጽፈህ ወደ ኤፌሶንና ወደ ሰምርኔስ ወደ ጴርጋሞንም ወደ ትያጥሮንም ወደ ሰርዴስም ወደ ፊላደልፊያም ወደ ሎዲቅያም በእስያ ወዳሉት ወደ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ላክ፤” አለኝ።


ኤር​ም​ያ​ስም ሠራ​ያን እን​ዲህ አለው፥ “ወደ ባቢ​ሎን በገ​ባህ ጊዜ እይ፤ ይህ​ንም ቃል ሁሉ አን​ብ​ብና፦


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ፥ በባ​ቢ​ሎን ላይና በከ​ለ​ዳ​ው​ያን ምድር በሚ​ኖ​ሩት ላይ የሚ​ያ​ቃ​ጥ​ልና የሚ​ያ​ጠፋ ነፋ​ስን አስ​ነ​ሣ​ለሁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements