Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 51:49 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

49 ባቢ​ሎ​ንም በእ​ስ​ራ​ኤል ስለ ተገ​ደ​ሉት ትወ​ድ​ቃ​ለች፤ ስለ ባቢ​ሎ​ንም በም​ድር ሁሉ የተ​ገ​ደ​ሉት ይወ​ድ​ቃሉ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

49 “በምድር ሁሉ የታረዱት፣ በባቢሎን ምክንያት እንደ ወደቁ፣ ባቢሎንም በእስራኤል በታረዱት ምክንያት መውደቅ ይገባታል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

49 ለባቢሎን በምድሪቱ ሁሉ ተወግተው የሞቱት ወድቀዋል እንዲሁ ለእስራኤል ተወግተው ለሞቱት ባቢሎን መውደቅ አለባት።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

49 ባቢሎን ለዓለም ሕዝብ እልቂት ምክንያት ሆናለች፤ ለብዙ እስራኤላውያን እልቂት ምክንያት በመሆንዋም እነሆ ባቢሎን ራስዋ መውደቅ አለባት፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

49 ባቢሎንም ከእስራኤል ተወግተው የሞቱት እንዲወድቁ እንዳደረገች፥ እንዲሁ በባቢሎን ከምድሩ ሁሉ ተወግተው የሞቱት ይወድቃሉ።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 51:49
13 Cross References  

በጽ​ዮን በዐ​ይ​ና​ችሁ ፊት ስለ ሠሩት ክፋ​ታ​ቸው ሁሉ በባ​ቢ​ሎ​ንና በከ​ለ​ዳ​ው​ያን ምድር የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሁሉ እበ​ቀ​ላ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


“ቀስ​ትን የሚ​ገ​ትሩ ቀስ​ተ​ኞ​ችን ሁሉ በባ​ቢ​ሎን ላይ ጥሩ​አ​ቸው፤ በዙ​ሪ​ያዋ ስፈ​ሩ​ባት፤ ከእ​ር​ስ​ዋም ሰዎች አንድ አያ​ም​ልጥ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቅዱስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተቃ​ው​ማ​ለ​ችና እንደ ሥራዋ መጠን መል​ሱ​ላት፤ እን​ዳ​ደ​ረ​ገ​ችም ሁሉ አድ​ር​ጉ​ባት።


ምሕረትን ለማያደርግ ምሕረት የሌለበት ፍርድ ይሆናልና፤ ምሕረትም በፍርድ ላይ ይመካል።


በጽ​ዮን የም​ት​ኖር በእኔ ላይ የተ​ደ​ረገ ግፍና ሥቃይ በባ​ቢ​ሎን ላይ ይሁን ትላ​ለች፤ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ደሜ በከ​ለ​ዳ​ው​ያን ምድር በሚ​ኖ​ሩት ላይ ይሁን ትላ​ለች።”


“ርስ​ቴን የም​ት​በ​ዘ​ብዙ እና​ንተ ሆይ! ደስ ብሎ​አ​ች​ኋ​ልና፥ ሐሤ​ት​ንም አድ​ር​ጋ​ች​ኋ​ልና፥ በመ​ስክ ላይም እን​ዳ​ለች ጊደር ሆና​ችሁ ተቀ​ና​ጥ​ታ​ች​ኋ​ልና፥ እንደ ብር​ቱ​ዎ​ችም በሬ​ዎች ቷጋ​ላ​ች​ሁና፤


አዶ​ኒ​ቤ​ዜ​ቅም፥ “የእ​ጆ​ቻ​ቸ​ውና የእ​ግ​ሮ​ቻ​ቸው አውራ ጣቶች የተ​ቈ​ረጡ ሰባ ነገ​ሥ​ታት ከገ​በ​ታዬ በታች ፍር​ፋሪ ይለ​ቅሙ ነበሩ፤ እኔ እን​ዳ​ደ​ረ​ግሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲሁ መለ​ሰ​ልኝ” አለ። ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ወሰ​ዱት፥ በዚ​ያም ሞተ።


በእርስዋም ውስጥ የነቢያትና የቅዱሳን ደም በምድርም የታረዱ ሁሉ ደም ተገኘባት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements