Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 51:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 አሕ​ዛ​ብ​ንም፥ የሜ​ዶ​ን​ንም ነገ​ሥ​ታት፥ አለ​ቆ​ች​ንም፥ መሳ​ፍ​ን​ት​ንም ሁሉ፥ የግ​ዛ​ታ​ቸ​ው​ንም ምድር ሁሉ ለዩ​ባት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 የሜዶንን ነገሥታት፣ ገዦቿንና ባለሥልጣኖቿን ሁሉ፣ በግዛታቸው ሥር ያሉትን አገሮች ሁሉ፣ እነዚህን ሕዝቦች ለጦርነት አዘጋጁባት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 አሕዛብን የሚዶንንም ነገሥታት ገዢዎችዋንም ሹማምንቶችዋንም ሁሉ የግዛትዋንም ምድር ሁሉ በእርሷ ላይ ለጦርነት አዘጋጁ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ባቢሎንን ይወጉ ዘንድ ሕዝቦችን አዘጋጁ፤ መድቡ፤ ወደ ሜዶን ነገሥታት፥ ወደ መሪዎቻቸውና ጦር አዛዦቻቸው እንዲሁም እነርሱ በሚቈጣጠሩአቸው አገሮች ወደሚኖሩ ሠራዊት ሁሉ መልእክት ላኩ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 አሕዛብን የሚዶንንም ነገሥታት አለቆችንም ሹማምቶችንም ሁሉ የግዛታቸውንም ምድር ሁሉ አዘጋጁባት።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 51:28
18 Cross References  

“ፍላ​ጾ​ችን አዘ​ጋጁ፤ ጕራ​ን​ጕ​ሬ​ዎ​ች​ንም ሙሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያጠ​ፋት ዘንድ ቍጣው በባ​ቢ​ሎን ላይ ነውና የሜ​ዶ​ንን ንጉሥ መን​ፈስ አስ​ነ​ሥ​ቶ​አል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀል የመ​ቅ​ደሱ በቀል ነውና።


“በም​ድር ላይ ዓላ​ማን አንሡ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል መለ​ከ​ትን ንፉ፤ አሕ​ዛ​ብ​ንም ለዩ​ባት፤ የአ​ራ​ራ​ት​ንና የሚ​ኒን የአ​ስ​ከ​ና​ዝ​ንም መን​ግ​ሥ​ታት እዘ​ዙ​ባት፤ ጦረ​ኞ​ች​ንም በላ​ይዋ አቁሙ፤ ብዛ​ታ​ቸው እንደ አን​በጣ የሆኑ ፈረ​ሶ​ችን በላ​ይዋ አውጡ።


የዘ​ምሪ ነገ​ሥ​ታ​ት​ንም ሁሉ፥ የኤ​ላም ነገ​ሥ​ታ​ት​ንም ሁሉ፥ የሜ​ዶን ነገ​ሥ​ታ​ት​ንም ሁሉ፤


ከባድ ራእይ ተነ​ገ​ረኝ፤ ወን​ጀ​ለ​ኛው ይወ​ነ​ጅ​ላል፤ በደ​ለ​ኛ​ውም ይበ​ድ​ላል። የኤ​ላም ሰዎ​ችና የሜ​ዶን መል​እ​ክ​ተኛ በእኔ ላይ ይመ​ጣሉ። ዛሬ ግን እጨ​ነ​ቃ​ለሁ፤ እረ​ጋ​ጋ​ለ​ሁም።


እነሆ፥ ብር የማ​ይ​ሹ​ትን፥ ወር​ቅም የማ​ያ​ም​ራ​ቸ​ውን ሜዶ​ና​ው​ያ​ንን በእ​ና​ንተ ላይ አስ​ነ​ሣ​ለሁ።


የያ​ፌት ልጆች ጋሜር፥ ማጎግ፥ ማዳይ፥ ይሕ​ያን፥ ኤልሳ፥ ቶቤል፥ ሞሳ​ሕና ቲራም።


የያ​ፌት ልጆች ጋሜር፥ ማጎግ፥ ማዴ፥ ይህ​ያን፥ ይልሳ፥ ቶቤል፥ሞሳሕ፥ ቴራስ ናቸው።


ብዙ አሕ​ዛ​ብና ታላ​ላ​ቆች ነገ​ሥ​ታት እነ​ር​ሱን ይገ​ዙ​አ​ቸ​ዋል፤ እኔም እንደ አደ​ራ​ረ​ጋ​ቸ​ውና እንደ እጃ​ቸው ሥራ እከ​ፍ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ።”


“እነሆ ሕዝብ ከሰ​ሜን ይመ​ጣል፤ ታላቅ ሕዝ​ብና ብዙ ነገ​ሥ​ታ​ትም ከም​ድር ዳርቻ ይነ​ሣሉ።


ማንም እን​ዳ​ይ​ቀ​መ​ጥ​ባት የባ​ቢ​ሎ​ንን ምድር ባድማ ያደ​ር​ጋት ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐሳብ በባ​ቢ​ሎን ላይ ጸን​ቶ​አ​ልና ምድር ተና​ወ​ጠች፤ ታመ​መ​ችም።


Follow us:

Advertisements


Advertisements