Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 51:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 በጽ​ዮን በዐ​ይ​ና​ችሁ ፊት ስለ ሠሩት ክፋ​ታ​ቸው ሁሉ በባ​ቢ​ሎ​ንና በከ​ለ​ዳ​ው​ያን ምድር የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሁሉ እበ​ቀ​ላ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 “በጽዮን ላይ ስላደረሱት ጥፋት ሁሉ ለባቢሎንና በባቢሎን ለሚኖሩት ሁሉ ዐይናችሁ እያየ ዋጋቸውን እከፍላቸዋለሁ” ይላል እግዚአብሔር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 በጽዮን በዓይናችሁ ፊት ስለ ሠሩት ክፋታቸው ሁሉ በባቢሎንና በከለዳውያን ምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ ፍዳቸውን እከፍላለሁ፥ ይላል ጌታ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ባቢሎንና ሕዝብዋ በኢየሩሳሌም ስላደረጉት ክፉ ሥራ ሁሉ በመበቀል ብድራታቸውን ስከፍላቸው ታያላችሁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 በጽዮን በዓይናችሁ ፊት ስለሠሩት ክፋታቸው ሁሉ በባቢሎንና በከለዳውያን ምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ ፍዳቸውን እከፍላለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 51:24
25 Cross References  

እጆ​ችዋ ደክ​መ​ዋ​ልና ክበ​ቡ​አት፤ ግንቧ ወድ​ቋል፤ ቅጥ​ር​ዋም ፈር​ሶ​አል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በቀል ነውና ተበ​ቀ​ሏት፤ እንደ ሠራ​ች​ውም ሥሩ​ባት።


በእርስዋም ውስጥ የነቢያትና የቅዱሳን ደም በምድርም የታረዱ ሁሉ ደም ተገኘባት።


“ሰማይ ሆይ! ቅዱሳን ሐዋርያት ነቢያትም ሆይ! በእርስዋ ላይ ደስ ይበላችሁ፤ እግዚአብሔር ፈርዶላችኋልና።”


በታላቅ ድምፅም እየጮኹ “ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ! እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም? ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም?” አሉ።


ባቢ​ሎ​ንም በእ​ስ​ራ​ኤል ስለ ተገ​ደ​ሉት ትወ​ድ​ቃ​ለች፤ ስለ ባቢ​ሎ​ንም በም​ድር ሁሉ የተ​ገ​ደ​ሉት ይወ​ድ​ቃሉ።


በጽ​ዮን የም​ት​ኖር በእኔ ላይ የተ​ደ​ረገ ግፍና ሥቃይ በባ​ቢ​ሎን ላይ ይሁን ትላ​ለች፤ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ደሜ በከ​ለ​ዳ​ው​ያን ምድር በሚ​ኖ​ሩት ላይ ይሁን ትላ​ለች።”


“ፍላ​ጾ​ችን አዘ​ጋጁ፤ ጕራ​ን​ጕ​ሬ​ዎ​ች​ንም ሙሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያጠ​ፋት ዘንድ ቍጣው በባ​ቢ​ሎን ላይ ነውና የሜ​ዶ​ንን ንጉሥ መን​ፈስ አስ​ነ​ሥ​ቶ​አል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀል የመ​ቅ​ደሱ በቀል ነውና።


የጩ​ኸት ድምፅ ከከ​ተማ፥ ድም​ፅም ከመ​ቅ​ደስ፥ በጠ​ላ​ቶ​ቹም ላይ ፍዳን የሚ​ያ​መጣ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ድምፅ ተሰ​ም​ቶ​አል።


የተ​ወ​ደ​ደ​ች​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ዓመት የተ​መ​ረ​ጠች ብዬ እጠ​ራት ዘንድ፥ አም​ላ​ካ​ች​ንም የሚ​በ​ቀ​ል​በ​ትን ቀን እና​ገር ዘንድ፥ የሚ​ያ​ለ​ቅ​ሱ​ት​ንም ሁሉ አጽ​ናና ዘንድ፥


ሁሉም በአ​ን​ድ​ነት ተሰ​ብ​ስ​በው ይሰ​ማሉ፤ ይህን ማን ነገ​ራ​ቸው? አን​ተን በመ​ው​ደድ የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንን ዘር አስ​ወ​ግድ ዘንድ ፈቃ​ድ​ህን በባ​ቢ​ሎን ላይ አደ​ረ​ግሁ።


ብዙ አሕ​ዛ​ብና ታላ​ላ​ቆች ነገ​ሥ​ታት እነ​ር​ሱን ይገ​ዙ​አ​ቸ​ዋል፤ እኔም እንደ አደ​ራ​ረ​ጋ​ቸ​ውና እንደ እጃ​ቸው ሥራ እከ​ፍ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ።”


የከ​ላ​ው​ዴ​ዎን ምድር ትዘ​ረ​ፋ​ለች፤ የማ​ረ​ኳ​ትም ሁሉ ይጠ​ግ​ባሉ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


በአ​ን​ቺም እረ​ኛ​ው​ንና መን​ጋ​ውን እበ​ት​ና​ለሁ፤ በአ​ን​ቺም አራ​ሹ​ንና ጥማ​ዱን እበ​ት​ና​ለሁ፤ በአ​ን​ቺም አለ​ቆ​ች​ንና መሳ​ፍ​ን​ትን እበ​ት​ና​ለሁ።


ጥፋት በባ​ቢ​ሎን ላይ መጥ​ቶ​ባ​ታ​ልና፥ ተዋ​ጊ​ዎ​ችዋ ተያዙ፤ ቀስ​ታ​ቸ​ውም ተሰ​ባ​በረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተበ​ቅ​ሎ​አ​ቸ​ዋ​ልና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፍዳን ከፍ​ሎ​አ​ቸ​ዋ​ልና።


ታው። አቤቱ፥ እንደ እጃ​ቸው ሥራ ፍዳ​ቸ​ውን ክፈ​ላ​ቸው።


ጥላዋ ተራ​ሮ​ችን ከደነ፥ ጫፎ​ች​ዋም እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዝግባ ሆኑ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements