Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 50:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 እነሆ ከሰ​ሜን ምድር የታ​ላ​ላቅ አሕ​ዛ​ብን ጉባኤ አነ​ሣ​ለሁ፤ በባ​ቢ​ሎ​ንም ላይ አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በእ​ር​ስ​ዋም ላይ ይሰ​ለ​ፋሉ፤ ከዚ​ያም ትወ​ሰ​ዳ​ለች፤ ፍላ​ጾ​ቻ​ቸ​ውም ባዶ​ውን እን​ደ​ማ​ይ​መ​ለስ እንደ ብልህ ተዋጊ ፍላጻ ናቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 የታላላቅ መንግሥታትን ማኅበር፣ ከሰሜን በባቢሎን ላይ አስነሣለሁ፤ እነርሱም በርሷ ላይ ይሰለፋሉ፤ መጥተውም ይይዟታል። ቀስቶቻቸው ባዶ እጃቸውን እንደማይመለሱ፣ እንደ ሥልጡን ተዋጊዎች ናቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 እነሆ፥ ከሰሜን ምድር የታላላቅ አሕዛብን ጉባኤ አስነሣለሁ በባቢሎንም ላይ አመጣቸዋለሁ፤ በእርሷም ላይ ይሰለፋሉ፥ ከዚያም ትያዛለች፤ ፍላጾቻቸውም ተጨናግፎ ባዶውን እንደማይመለስ እንደ ብልህ ጀግና ፍላጻ ናቸው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 እኔ ከወደ ሰሜን የተባበሩ ሕዝቦች በባቢሎን ላይ እንዲዘምቱ አነሣሣለሁ፤ በእርስዋም ላይ አደጋ ይጥሉባታል፤ ከዚያም ትያዛለች፤ የእነርሱም ቀስቶች ተወርውረው ዒላማቸውን እንደማይስቱ እንደ ሠለጠኑ ወታደሮች ቀስቶች ናቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 እነሆ፥ ከሰሜን ምድር የታላላቅ አሕዛብን ጉባኤ አስነሣለሁ በባቢሎንም ላይ አመጣቸዋለሁ፥ በእርስዋም ላይ ይሰለፋሉ፥ ከዚያም ትወሰዳለች፥ ፍላጾቻቸውም ባዶውን እንደማይመለስ እንደ ብልህ ጀግና ፍላጻ ናቸው።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 50:9
20 Cross References  

“ፍላ​ጾ​ችን አዘ​ጋጁ፤ ጕራ​ን​ጕ​ሬ​ዎ​ች​ንም ሙሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያጠ​ፋት ዘንድ ቍጣው በባ​ቢ​ሎን ላይ ነውና የሜ​ዶ​ንን ንጉሥ መን​ፈስ አስ​ነ​ሥ​ቶ​አል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀል የመ​ቅ​ደሱ በቀል ነውና።


“ቀስ​ትን የሚ​ገ​ትሩ ቀስ​ተ​ኞ​ችን ሁሉ በባ​ቢ​ሎን ላይ ጥሩ​አ​ቸው፤ በዙ​ሪ​ያዋ ስፈ​ሩ​ባት፤ ከእ​ር​ስ​ዋም ሰዎች አንድ አያ​ም​ልጥ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቅዱስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተቃ​ው​ማ​ለ​ችና እንደ ሥራዋ መጠን መል​ሱ​ላት፤ እን​ዳ​ደ​ረ​ገ​ችም ሁሉ አድ​ር​ጉ​ባት።


ጊዜዋ ደር​ሶ​አ​ልና ሣጥ​ኖ​ች​ዋን ከፍ​ታ​ችሁ እንደ ዋሻ በር​ብ​ሯት፤ ጨር​ሳ​ች​ሁም አጥ​ፏት፥ ምንም አታ​ስ​ቀ​ሩ​ላት።


“በላ​ይ​ዋና በሚ​ኖ​ሩ​ባት ላይ በም​ሬት ውጡ፤ ሰይፍ ሆይ! ተበ​ቀዪ፥ ፍጻ​ሜ​ያ​ቸ​ው​ንም አጥፊ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ያዘ​ዝ​ሁ​ሽ​ንም ሁሉ አድ​ርጊ።


“እና​ንተ ቀስ​ትን የም​ት​ገ​ትሩ ሰዎች ሁሉ፥ በባ​ቢ​ሎን ላይ በዙ​ሪ​ያዋ ተሰ​ለፉ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ኀጢ​አት ሠር​ታ​ለ​ችና ወር​ው​ሩ​ባት፤ እር​ስ​ዋ​ንም ከመ​ው​ጋት ቸል አት​በሉ፤


ሕዝቤ ከሰ​ሜን በእ​ር​ስዋ ላይ ወጥ​ት​ዋል፤ ምድ​ር​ዋ​ንም ባድማ ያደ​ር​ጋል፤ የሚ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ትም አይ​ገ​ኝም፤ ከሰው ጀምሮ እስከ እን​ስሳ ድረስ ሸሽ​ተው ሄደ​ዋል።


እሳት ከቍ​ጣዬ ትነ​ድ​ዳ​ለ​ችና፥ እና​ን​ተ​ንም ታቃ​ጥ​ላ​ች​ኋ​ለ​ችና በማ​ታ​ው​ቀው ሀገር ለጠ​ላ​ቶ​ችህ አስ​ገ​ዛ​ሃ​ለሁ።


ከሰ​ሜ​ንና ከፀ​ሐይ መውጫ የሚ​መ​ጡ​ትን አስ​ነ​ሣሁ፤ በስ​ሜም ይጠ​ራሉ፤ አለ​ቆች ይምጡ፤ እንደ ሸክላ ሠሪ ጭቃና ጭቃን እን​ደ​ሚ​ረ​ግጥ ሸክላ ሠሪ እን​ዲሁ ይረ​ግ​ጡ​አ​ቸ​ዋል።


ከባድ ራእይ ተነ​ገ​ረኝ፤ ወን​ጀ​ለ​ኛው ይወ​ነ​ጅ​ላል፤ በደ​ለ​ኛ​ውም ይበ​ድ​ላል። የኤ​ላም ሰዎ​ችና የሜ​ዶን መል​እ​ክ​ተኛ በእኔ ላይ ይመ​ጣሉ። ዛሬ ግን እጨ​ነ​ቃ​ለሁ፤ እረ​ጋ​ጋ​ለ​ሁም።


ከሞ​ቱት ደምና ከኀ​ያ​ላን ስብ፥ የዮ​ና​ታን ቀስት ባዶ​ዋን አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም፤ የሳ​ኦ​ልም ሰይፍ ባዶ​ዋን አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም።


ሁሉም ሰይፍ የያ​ዙና ሰልፍ የተ​ማሩ ናቸው፤ በሌ​ሊት ከሚ​ወ​ድ​ቀው ፍር​ሀት የተ​ነሣ ሰው ሁሉ ሰይፉ በወ​ገቡ አለ።


ብዙ አሕ​ዛ​ብና ታላ​ላ​ቆች ነገ​ሥ​ታት እነ​ር​ሱን ይገ​ዙ​አ​ቸ​ዋል፤ እኔም እንደ አደ​ራ​ረ​ጋ​ቸ​ውና እንደ እጃ​ቸው ሥራ እከ​ፍ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ።”


የቀ​ረ​ቡና የራቁ፥ አንዱ ከሌ​ላው ጋር ያሉ የሰ​ሜን ነገ​ሥ​ታ​ት​ንም ሁሉ፥ በም​ድር ፊት ላይ ያሉ የዓ​ለም መን​ግ​ሥ​ታ​ት​ንም ሁሉ አጠ​ጣ​ኋ​ቸው፤ የሲ​ሳ​ርም ንጉሥ ከእ​ነ​ርሱ በኋላ ይጠ​ጣል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements