Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 50:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ምድ​ርን ሁሉ የም​ት​ፈ​ጫት መዶሻ እን​ዴት ደቀ​ቀች! እን​ዴ​ትስ ተሰ​በ​ረች! ባቢ​ሎ​ንስ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል እን​ዴት ባድማ ሆነች!

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 የምድር ሁሉ መዶሻ፣ እንዴት ተሰበረ! እንዴትስ ደቀቀ! በሕዝቦች መካከል፣ ባቢሎን እንዴት ባድማ ሆነች!

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 የምድር ሁሉ መዶሻ እንዴት ደቀቀ እንዴትስ ተሰበረ! ባቢሎንስ በአሕዛብ መካከል እንዴት መሣቀቅያ ሆነች!

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 የዓለምን ሕዝብ እንደ መዶሻ ታደቅ የነበረችው ባቢሎን እርስዋ ራስዋ ደቃለች፤ በዚያች አገር ላይ የደረሰው በሕዝቦች ዘንድ ምንኛ አስደንጋጭ ነው?

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 የምድር ሁሉ መዶሻ እንዴት ደቀቀ እንዴትስ ተሰበረ! ባቢሎንስ በአሕዛብ መካከል እንዴት ባድማ ሆነች!

See the chapter Copy




ኤርምያስ 50:23
5 Cross References  

“በቀጭን ተልባ እግርና በቀይ ሐምራዊም ልብስ ለተጐናጸፈች በወርቅና በከበረ ድንጋይም በዕንቁም ለተሸለመች ለታላቂቱ ከተማ ወዮላት! ወዮላት! ይህን የሚያህል ታላቅ ባለ ጠግነት በአንድ ሰዓት ጠፍቶአልና፤” እያሉ ስቃይዋን ከመፍራት የተነሣ በሩቅ ይቆማሉ። የመርከብም መሪ ሁሉ በመርከብም ወደ ማናቸውም ስፍራ የሚሄድ ሁሉ መርከበኞችም ከባሕርም የሚጠቀሙ ሁሉ በሩቅ ቆሙ፤


በአ​ን​ቺም ላይ ሙሾ ያሞ​ሻሉ፤ እን​ዲ​ህም ይሉ​ሻል፦ በባ​ሕር የተ​ቀ​መ​ጥሽ፥ በባ​ሕ​ርም ውስጥ የጸ​ናሽ፥ ከሚ​ቀ​መ​ጡ​ብ​ሽም ጋር በዙ​ሪ​ያሽ የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሁሉ ያስ​ፈ​ራሽ፥ የከ​በ​ርሽ ከተማ ሆይ! እን​ዴት ጠፋሽ!


Follow us:

Advertisements


Advertisements