Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 49:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 በይ​ሁዳ ንጉሥ በሴ​ዴ​ቅ​ያስ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ዓመተ መን​ግ​ሥት ስለ ኤላም ወደ ነቢዩ ወደ ኤር​ም​ያስ የመ​ጣው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ይህ ነው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ ዘመነ መንግሥት መጀመሪያ፣ ስለ ኤላም ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ መንግሥት መጀመሪያ ላይ ስለ ኤላም ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ የመጣው የጌታ ቃል ይህ ነው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 ሴዴቅያስ በይሁዳ ላይ እንደ ነገሠ ወዲያውኑ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ስለ ዔላም አገር ተናገረኝ፤ እንዲህም አለኝ፦

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ መንግሥት መጀመሪያ ስለ ኤላም ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 49:34
12 Cross References  

የዘ​ምሪ ነገ​ሥ​ታ​ት​ንም ሁሉ፥ የኤ​ላም ነገ​ሥ​ታ​ት​ንም ሁሉ፥ የሜ​ዶን ነገ​ሥ​ታ​ት​ንም ሁሉ፤


በሰ​ና​ዖር ንጉሥ በአ​ሚ​ሮ​ፌል፥ በእ​ላ​ሳር ንጉሥ በአ​ር​ዮክ፥ በኤ​ላም ንጉሥ በኮ​ሎ​ዶ​ጎ​ሞር፥ በአ​ሕ​ዛብ ንጉሥ በቴ​ሮ​ጋል ዘመን እን​ዲህ ሆነ፤


የሴ​ምም ልጆች ኤላም፥ አሦር፥ አር​ፋ​ክ​ስድ፥ ሉድ፥ አራም፥ ቃይ​ናን።


ከባድ ራእይ ተነ​ገ​ረኝ፤ ወን​ጀ​ለ​ኛው ይወ​ነ​ጅ​ላል፤ በደ​ለ​ኛ​ውም ይበ​ድ​ላል። የኤ​ላም ሰዎ​ችና የሜ​ዶን መል​እ​ክ​ተኛ በእኔ ላይ ይመ​ጣሉ። ዛሬ ግን እጨ​ነ​ቃ​ለሁ፤ እረ​ጋ​ጋ​ለ​ሁም።


እኛ በተ​ወ​ለ​ድ​ን​በት በጳ​ርቴ፥ በሜድ፥ በኢ​ላ​ሜጤ፥ በሁ​ለቱ ወን​ዞች መካ​ከል፥ በይ​ሁዳ፥ በቀ​ጰ​ዶ​ቅያ፥ በጳ​ን​ጦ​ስና በእ​ስያ፥


በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ ከአ​ሦ​ርና ከግ​ብፅ፥ ከባ​ቢ​ሎ​ንና ከኢ​ት​ዮ​ጵያ፥ ከኤ​ላ​ሜ​ጤን፥ ከም​ሥ​ራ​ቅና ከም​ዕ​ራብ ለቀ​ሩት ለሕ​ዝቡ ቅሬታ ይቀና ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ገና እጁን ይገ​ል​ጣል።


አዛዡ ሬሁም፥ ጸሓ​ፊ​ውም ሲም​ሳይ፥ የቀ​ሩ​ትም ተባ​ባ​ሪ​ዎ​ቻ​ቸው፥ ዲና​ው​ያን፥ አፈ​ር​ሳ​ት​ካ​ዋ​ያን፥ ጠር​ፈ​ላ​ው​ያን፥ አፈ​ር​ሳ​ው​ያን፥ አር​ካ​ው​ያን፥ ባቢ​ሎ​ና​ው​ያን፥ ሱስ​ና​ካ​ው​ያን፥ ዴሐ​ው​ያን፥ ኤላ​ማ​ው​ያን፥


ከኤ​ላም ንጉሥ ከኮ​ሎ​ዶ​ጎ​ሞር፥ ከአ​ሕ​ዛብ ንጉሥ ከቴ​ሮ​ጋል፥ ከሰ​ና​ዖር ንጉሥ ከአ​ሜ​ሮ​ፌል፥ ከእ​ላ​ሳር ንጉሥ ከአ​ር​ዮክ ጋር ተጋ​ጠሙ። እነ​ዚህ አራቱ ነገ​ሥ​ታት ከአ​ም​ስቱ ነገ​ሥ​ታት ጋር ተዋጉ።


ከዚ​ህም በኋላ እን​ዲህ ሆነ፤ በዚያ ዓመት፥ በይ​ሁዳ ንጉሥ በሴ​ዴ​ቅ​ያስ መን​ግ​ሥት መጀ​መ​ሪያ፥ በአ​ራ​ተ​ኛው ዓመት በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ወር ሐሰ​ተ​ኛው ነቢይ የገ​ባ​ዖን ሰው የዓ​ዙር ልጅ ሐና​ንያ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በካ​ህ​ና​ትና በሕ​ዝብ ሁሉ ፊት እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረኝ፦


Follow us:

Advertisements


Advertisements