ኤርምያስ 49:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 ሐሴቦን ሆይ! ጋይ ፈርሳለችና አልቅሽላት፤ እናንተም የራባት ሴቶች ልጆች ሆይ! ሚልኮም፥ ካህናቱና አለቆቹም በአንድነት ይማረካሉና ጩኹ፤ ማቅም ታጠቁ፤ አልቅሱም። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 “ሐሴቦን ሆይ፤ ጋይ ጠፍታለችና ዋይ በይ፤ የረባት ሴቶች ልጆች ሆይ ጩኹ፤ ማቅ ለብሳችሁ አልቅሱ፤ ሚልኮም ከካህናቱና ከመኳንንቱ ጋራ፣ ተማርኮ ይወሰዳልና፣ በቅጥር ውስጥ ወዲያ ወዲህ ተሯሯጡ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 ሐሴቦን ሆይ! ጋይ ፈርሳለችና አልቅሺ፤ እናንተም የረባት ሴቶች ልጆች ሆይ! ሚልኮም ካህናቱና አለቆቹም በአንድነት ይማረካሉና ጩኹ፥ ማቅም ታጠቁ፥ አልቅሱም፥ በቅጥሮችም መካከል ተርዋርዋጡ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 የዐይ ከተማ ስለ ፈረሰች አልቅሱ! በራባ ከተማ አካባቢ መንደሮች የምትኖሩ ሕዝቦች ሁሉ ጮክ ብላችሁ አልቅሱ! ሚልኮም የተባለው ጣዖት ከካህናቱና ከረዳቶቹ ጋር ተማርኮ የሄደ ስለ ሆነ ማቅ ለብሳችሁ በቅጥሮችዋ መካከል ወዲያና ወዲህ እያላችሁ አልቅሱ! See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 ሐሴቦን ሆይ፥ ጋይ ፈርሳለችና አልቅሺላት፥ እናንተም የረባት ሴቶች ልጆች ሆይ፥ ሚልኮም ካህናቱና አለቆቹም በአንድነት ይማረካሉና ጩኹ፥ ማቅም ታጠቁ፥ አልቅሱም፥ በቅጥሮችም መካከል ተርዋርዋጡ። See the chapter |