Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 49:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 በዓ​ለት ንቃ​ቃት ውስጥ የም​ት​ቀ​መጥ፥ የተ​ራ​ራ​ውን ከፍታ የም​ት​ይዝ ሆይ! ድፍ​ረ​ት​ህና የል​ብህ ኵራት አነ​ሣ​ሥ​ተ​ው​ሃል። ቤት​ህ​ንም ምንም እንደ ንስር ከፍ ብታ​ደ​ርግ፥ ከዚያ አወ​ር​ድ​ሃ​ለሁ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 አንተ በዐለት ንቃቃት ውስጥ የምትኖር፣ የተራራውንም ከፍታ የያዝህ ሆይ፤ የምትነዛው ሽብር፣ የልብህም ኵራት አታልሎሃል፤ መኖሪያህን እስከ ንስር ከፍታ ቦታ ብትሠራም፣ ከዚያ ወደ ታች አወርድሃለሁ፤” ይላል እግዚአብሔር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 በዓለት ንቃቃት ውስጥ የምትቀመጥ፥ የተራራውን ከፍታ የምትይዝ ሆይ! ማሣቀቅያህና የልብህ ኩራት አታልለውሃል። ምንም እንኳ ጎጆህን እንደ ንስር ጎጆ ከፍ ብታደርግ፥ ከዚያ አወርድሃለሁ፥ ይላል ጌታ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 አለታማው ገደል ላይ የምትኖሪ፥ እስከ ተራራማው ጫፍ ድረስ የምትደርሽ ሆይ! ተፈሪነትሽና የልብሽ ኲራት አታለውሻል፤ ምንም እንኳ መኖሪያሽን እንደ ንስር ጎጆ ብታደርጊ እኔ ከዚያ ላይ አወርድሻለሁ ይላል እግዚአብሔር።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 በዓለት ንቃቃት ውስጥ የምትቀመጥ፥ የተራራውን ከፍታ የምትይዝ ሆይ፥ ድፍረትህና የልብህ ኵራት አታልለውሃል። ቤትህን ምንም እንደ ንስር ከፍ ብታደርግ፥ ከዚያ አወርድሃለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 49:16
21 Cross References  

ወደ ሲኦል ቢወ​ርዱ እጄ ከዚያ ታወ​ጣ​ቸ​ዋ​ለች፤ ወደ ሰማ​ይም ቢወጡ ከዚያ አወ​ር​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን እን​ዲህ ይላል፥ “በኀ​ያ​ላን የተ​ማ​ረኩ ይወ​ሰ​ዳሉ፤ የጨ​ካ​ኞ​ችም ብዝ​በዛ ያመ​ል​ጣል፤ እኔም ፍር​ድ​ሽን እፈ​ር​ድ​ል​ሻ​ለሁ፤ ልጆ​ች​ሽ​ንም አድ​ና​ለሁ።


በአ​ፍህ ትእ​ዛዝ ንስር ከፍ ከፍ ይላ​ልን? ጆፌ አሞ​ራስ ልጆ​ቹን አቅፎ ያድ​ራ​ልን?


ከጥል በፊት ስድብ ይቀድማል፥ ከመውደቅም በፊት ክፋትን ማወቅ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ምድ​ርን ያና​ውጥ ዘንድ በተ​ነሣ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከመ​ፍ​ራ​ትና ከግ​ር​ማው ክብር የተ​ነሣ ወደ ድን​ጋይ ዋሻና ወደ ተሰ​ነ​ጠቁ ዓለ​ቶች ውስጥ ያገ​ባሉ።


ፊት​ህን አሳ​የኝ፥ ቃል​ህ​ንም አሰ​ማኝ፤ ቃልህ ያማረ፥ ፊት​ህም የተ​ዋበ ነውና።


ሞትና ሕይወት በምላስ እጅ ናቸው፤ የሚያጸኑአትም ፍሬዋን ይበላሉ።


እር​ሱም በጨው ሸለቆ ከኤ​ዶ​ም​ያስ ዐሥር ሺህ ሰው ገደለ፤ ሴላ​ንም በጦ​ር​ነት ወስዶ ስም​ዋን እስከ ዛሬ ድረስ “ዮቅ​ት​ኤል” ብሎ ጠራት።


የሚ​ቀ​መ​ጡ​ባ​ቸ​ው​ንም ከተ​ሞች አና​ው​ጣ​ለሁ። በእ​ጄም ዓለ​ምን ሁሉ እንደ ወፍ ቤት እሰ​በ​ስ​ባ​ለሁ፤ እንደ ተተወ እን​ቍ​ላ​ልም እወ​ስ​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ከእ​ኔም የሚ​ያ​መ​ልጥ የለም፤ የሚ​ቃ​ወ​መ​ኝም የለም።


እነሆ በሕ​ዝብ ዘንድ የተ​ጠ​ቃህ፥ በሰ​ዎ​ችም ዘንድ የተ​ና​ቅህ አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ።


“ቀስ​ትን የሚ​ገ​ትሩ ቀስ​ተ​ኞ​ችን ሁሉ በባ​ቢ​ሎን ላይ ጥሩ​አ​ቸው፤ በዙ​ሪ​ያዋ ስፈ​ሩ​ባት፤ ከእ​ር​ስ​ዋም ሰዎች አንድ አያ​ም​ልጥ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቅዱስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተቃ​ው​ማ​ለ​ችና እንደ ሥራዋ መጠን መል​ሱ​ላት፤ እን​ዳ​ደ​ረ​ገ​ችም ሁሉ አድ​ር​ጉ​ባት።


ባቢ​ሎ​ንም ወደ ሰማይ ብት​ወጣ፥ ቅፅ​ሮ​ች​ዋ​ንም በኀ​ይ​ልዋ ብታ​ጸና፥ ከእኔ ዘንድ አጥ​ፊ​ዎች ይመ​ጡ​ባ​ታል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ከክፉ እንዲድን ጐጆውን በከፍታ ላይ ያደርግ ዘንድ ለቤቱ ክፉ ትርፍን ለሚሰበስብ ወዮለት!


ተራሮቹንም በረሃ አደረግኋቸው፥ ርስቱንም ለምድረ በዳ ቀበሮች አሳልፌ ሰጠኋቸው።


እና​ንተ፦ እኛ ኀያ​ላን በሰ​ል​ፍም ጽኑ​ዓን ነን እን​ዴት ትላ​ላ​ችሁ?


Follow us:

Advertisements


Advertisements