ኤርምያስ 48:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 እግዚአብሔርም እንደ ተናገረ፥ ጥፋት ወደ ከተማ ሁሉ ይመጣል፤ አንዲትም ከተማ አትድንም፤ ሸለቆውም ይጠፋል፤ ሜዳውም ይበላሻል። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም8 በእያንዳንዱ ከተማ ላይ አጥፊ ይመጣል፤ አንድም ከተማ አያመልጥም። እግዚአብሔር ተናግሯልና፣ ሸለቆው ይጠፋል፤ ዐምባውም ይፈርሳል። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 ጌታም እንደ ተናገረው፥ አጥፊው ወደ ከተማ ሁሉ ይመጣል አንዲትም ከተማ አትድንም፤ ሸለቆውም ይጠፋል ሜዳውም እንዳልነበረ ይሆናል። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 እግዚአብሔር እንደ ተናገረ አጥፊው በከተሞች ሁሉ ላይ ይመጣል፤ አንድም የሚያመልጥ ከተማ የለም። ሸለቆውንና ሜዳውን እንዳልነበሩ ያደርጋል። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 እግዚአብሔርም እንደ ተናገረ፥ አጥፊ ወደ ከተማ ሁሉ ይመጣል አንዲትም ከተማ አትድንም፥ ሸለቆውም ይጠፋል ሜዳውም ይበላሻል። See the chapter |