Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 48:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 የሞ​አ​ብን ስድብ፥ የተ​ዋ​ረ​ደ​ው​ንም ብዙ ውር​ደ​ቱን፥ ልቡ​ና​ው​ንም ያስ​ታ​በ​የ​በ​ትን ትዕ​ቢ​ቱን ሰም​ተ​ናል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 “ስለ ሞዓብ ትዕቢት፣ ስለ እብሪቱና ስለ ኵራቱ፣ ስለ ትምክሕቱና ስለ መጓደዱ፣ ስለ ልቡም ማበጥ ሰምተናል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 እጅግ እንደ ታበየ ስለ ሞዓብ ትዕቢት ስለ ትምክህቱም ስለ ኩራቱም ስለ እብሪቱም ስለ ልቡም ትዕቢት ሰምተናል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ሞአብ በከፍተኛ ኲራት፥ ራሷን ከፍ ከፍ በማድረግ በትዕቢተኛነት፥ በመጀነንና በልበ ደንዳናነት የተወጠረች መሆንዋን ሰምቼአለሁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 እጅግ እንደ ታበየ ስለ ሞዓብ ትዕቢት ስለ ትምክህቱም ስለ ኵራቱም ስለ መጓደዱም ስለ ልቡም ትዕቢት ሰምተናል።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 48:29
13 Cross References  

የሞ​ዓ​ብን ትዕ​ቢ​ትና እጅግ መኵ​ራ​ቱን ሰም​ተ​ናል፤ ትዕ​ቢ​ቱ​ንም አስ​ወ​ገ​ድሁ፤ ጥን​ቈ​ላህ እን​ዲህ አይ​ደ​ለ​ምና፥ እን​ዲ​ህም አይ​ደ​ለም፤


ዕው​ቀ​ትህ በእኔ ላይ ተደ​ነ​ቀች፤ በረ​ታ​ች​ብኝ፥ ወደ እር​ሷም ለመ​ድ​ረስ አል​ች​ልም።


ነገር ግን ጸጋን አብልጦ ይሰጣል፤ ስለዚህ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል፤” ይላል።


ራሱን ከፍ የሚ​ያ​ደ​ርግ ሁሉ ይዋ​ረ​ዳ​ልና፤ ራሱ​ንም ያሚ​ያ​ዋ​ርድ ከፍ ይላ​ልና።”


ከመውደቅ በፊት የሰው ልቡ ከፍ ከፍ ይላል፥ ሳይከብርም ይዋረዳል።


እግዚአብሔርን የሚፈራ ዐመፃን ይጠላል፤ ጥልንና ትዕቢትን፥ ክፉ መንገድንም ይጠላል። የክፉ ሰዎችንም ጠማማ መንገድ ጠላሁ።


የችኩል፥ የነዝናዛና የነገረኛ ሰው ስሙ ቸነፈር ነው፥ ክፉን የሚያስብም ኃጥእ ነው።


በዓ​ለም ሁሉ ላይ ክፋ​ትን አዝ​ዛ​ለሁ፤ የኀ​ጢ​አ​ተ​ኞ​ች​ንም ኀጢ​አት እጐ​በ​ኛ​ለሁ፤ የት​ዕ​ቢ​ተ​ኞ​ች​ንም ኵራት እሽ​ራ​ለሁ፤ የጨ​ካ​ኞ​ቹ​ንም ኵራት አዋ​ር​ዳ​ለሁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements