ኤርምያስ 48:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 ስለዚህ እነሆ ጠማሞችን የምልክበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፤ እነርሱም ይጠሙበታል፤ ጋኖቹንም ይቀጠቅጣሉ፤ ፊቀኖቹንም ይሰብራሉ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም12 ስለዚህ ዕቃውን የሚገለብጡ ሰዎችን የምልክበት ጊዜ ይመጣል፤” ይላል እግዚአብሔር። “እነርሱም ይደፉታል፤ ዕቃውን ባዶ ያስቀራሉ፤ ማንቈርቈሪያዎቹንም ይሰባብራሉ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 ስለዚህ፥ እነሆ፥ የሚያገላብጡትን የምልክበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል ጌታ፥ እነርሱም ያገላብጡታል፤ ጋኖቹንም ባዶ ያደርጋሉ፥ መስቴዎቹንም ይሰብራሉ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 አንድ ሰው የወይን ጠጅን ከአንድ ዕቃ ወደ ሌላ ዕቃ ገልብጦ ባዶውን ዕቃ እንደሚሰብር፥ እኔም ሞአብን የሚያወድምና ሕዝብዋን የሚያፈልስ ሰው የምልክበት ጊዜ በእርግጥ ተቃርቦአል። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 ስለዚህ፥ እነሆ፥ የሚያገላብጡትን የምልክበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እነርሱም ያገላብጡታል፥ ጋኖቹንም ባዶ ያደርጋሉ፥ መስቴዎቹንም ይሰብራሉ። See the chapter |