Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 40:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 የሳ​ፋ​ንም ልጅ የአ​ኪ​ቃም ልጅ ጎዶ​ል​ያስ ለእ​ነ​ር​ሱና ለሰ​ዎ​ቻ​ቸው እን​ዲህ ብሎ ማለ፥ “ለከ​ለ​ዳ​ው​ያን ትገዙ ዘንድ አት​ፍሩ፤ በም​ድር ተቀ​መጡ፤ ለባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ተገዙ፤ መል​ካ​ምም ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 የሳፋን ልጅ የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ለእነርሱና ለሰዎቻቸው እንዲህ ሲል ቃል ገባላቸው፤ “ለባቢሎናውያን መገዛት አትፍሩ፤ በምድሪቱ ተቀምጣችሁ የባቢሎንን ንጉሥ አገልግሉ፤ መልካም ይሆንላችኋል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 የሳፋንም ልጅ የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ለእነርሱና ለሰዎቻቸው እንዲህ ብሎ ማለ፦ “ለከለዳውያን ለማገልገል አትፍሩ፤ በምድሪቱ ተቀመጡ ለባቢሎንም ንጉሥ አገልግሉ፥ መልካምም ይሆንላችኋል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ገዳልያም እንዲህ ሲል ማለላቸው፦ “በእውነት ቃል ልግባላችሁ፤ ለባቢሎናውያን እጃችሁን ስለ መስጠት ምንም የሚያስፈራችሁ ነገር የለም፤ በዚህች ምድር ሰፍራችሁ ኑሮአችሁን መሥርቱ፤ ለባቢሎን ንጉሥ ገብሩ፤ ለእናንተም ሁሉ ነገር መልካም ይሆንላችኋል፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 የሳፋንም ልጅ የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ለእነርሱና ለሰዎቻቸው እንዲህ ብሎ ማለ፦ ለከለዳውያን ትገዙ ዘንድ አትፍሩ፥ በምድር ተቀመጡ ለባቢሎንም ንጉሥ ተገዙ፥ መልካምም ይሆንላችኋል።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 40:9
9 Cross References  

ነገር ግን ከባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ቀን​በር በታች አን​ገ​ቱን ዝቅ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ው​ንና የሚ​ገ​ዛ​ለ​ትን ሕዝብ በሀ​ገሩ ላይ እተ​ወ​ዋ​ለሁ፤ እር​ሱም ያር​ሳ​ታል፤ ይቀ​መ​ጥ​ባ​ት​ማል።”


ጎዶ​ል​ያም፥ “ከከ​ለ​ዳ​ው​ያን ሎሌ​ዎች የተ​ነሣ አት​ፍሩ፤ በሀ​ገሩ ተቀ​መጡ፤ ለባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ተገዙ፤ መል​ካ​ምም ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል” ብሎ ለእ​ነ​ር​ሱና ለሰ​ዎ​ቻ​ቸው ማለ​ላ​ቸው።


ከት​ን​ሽ​ነቴ ጀምሮ ሁል​ጊዜ ተሰ​ለ​ፉ​ብኝ፤ ነገር ግን አል​ቻ​ሉ​ኝም።


ከቍ​ጣህ ፊት የተ​ነሣ ለሥ​ጋዬ ድኅ​ነት የለ​ውም፤ ከኀ​ጢ​አ​ቴም ፊት የተ​ነሣ ለአ​ጥ​ን​ቶቼ ሰላም የላ​ቸ​ውም።


ዕረ​ፍ​ትም መል​ካም መሆ​ን​ዋን፥ ምድ​ሪ​ቱም የለ​ማች መሆ​ን​ዋን በአየ ጊዜ ምድ​ርን ያር​ሳት ዘንድ ትከ​ሻ​ውን ዝቅ አደ​ረገ፤ በሥ​ራም ገበሬ ሆነ።


አሌፍ። ሕዝብ ሞል​ቶ​ባት የነ​በ​ረች ከተማ ብቻ​ዋን እን​ዴት ተቀ​መ​ጠች! በአ​ሕ​ዛብ ተመ​ልታ የነ​በ​ረች እንደ መበ​ለት ሆና​ለች፤ አሕ​ዛ​ብን ትገዛ የነ​በ​ረች፥ አው​ራ​ጃ​ዎ​ች​ንም ትገዛ የነ​በ​ረች ገባር ሆና​ለች።


ከም​ድረ በዳ ሰይፍ የተ​ነሣ፥ በሕ​ይ​ወ​ታ​ችን እን​ጀ​ራ​ች​ንን እና​መ​ጣ​ለን።


Follow us:

Advertisements


Advertisements