Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 40:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 “የአ​ሞን ልጆች ንጉሥ በኣ​ሊስ ይገ​ድ​ልህ ዘንድ የና​ታ​ን​ያን ልጅ እስ​ማ​ኤ​ልን እንደ ላከ ታው​ቃ​ለ​ህን?” አሉት። የአ​ኪ​ቃም ልጅ ጎዶ​ል​ያስ ግን አላ​መ​ና​ቸ​ውም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 “የአሞናውያን ንጉሥ በአሊስ አንተን ለመግደል የናታንያን ልጅ እስማኤልን እንደ ላከው አታውቅምን?” አሉት። የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ግን አላመናቸውም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 “የአሞን ልጆች ንጉሥ በኣሊስ አንተን ለመግደል የናታንያን ልጅ እስማኤልን እንደ ላከ ፈጽሞ አታውቅምን?” አሉት። የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ግን አላመናቸውም።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 “እስማኤል አንተን እንዲገድልህ የዐሞን ንጉሥ በዐሊስ የላከው መሆኑን አታውቅምን?” ብለው ጠየቁት። ገዳልያ ግን ይህን አላመነም፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 የአሞን ልጆች ንጉሥ በኣሊስ ይገድልህ ዘንድ የናታንያን ልጅ እስማኤልን እንደ ሰደደ ታውቃለህን? አሉት። የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ግን አላመናቸውም።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 40:14
15 Cross References  

እስ​ማ​ኤ​ልም በመ​ሴፋ የነ​በ​ረ​ውን የሕ​ዝ​ቡን ቅሬታ ሁሉ፥ የን​ጉ​ሡን ሴቶች ልጆች፥ የአ​ዛ​ዦች አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳን ለአ​ኪ​ቃም ልጅ ለጎ​ዶ​ል​ያስ የሰ​ጠ​ውን በመ​ሴፋ የቀ​ሩ​ትን ሕዝብ ሁሉ መለሰ፤ የና​ታ​ን​ያም ልጅ እስ​ማ​ኤል ወደ አሞን ልጆች ይሄድ ዘንድ ተነሣ።


ኤዶ​ም​ያ​ስ​ንም፥ ሞዓ​ብ​ንም፥ የአ​ሞ​ን​ንም ልጆች፤


ባልንጀራን አትመኑ፥ በወዳጅም አትታመኑ፥ የአፍህን ደጅ በብብትህ ከምትተኛው ጠብቅ።


የና​ታ​ን​ያም ልጅ እስ​ማ​ኤል ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩት ዐሥሩ ሰዎች ተነ​ሥ​ተው የሳ​ፋ​ንን ልጅ የአ​ኪ​ቃ​ምን ልጅ ጎዶ​ል​ያ​ስን በሰ​ይፍ መቱ፤ የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ በሀ​ገሩ ላይ የሾ​መ​ውን ገደሉ።


የና​ታ​ንያ ልጅ እስ​ማ​ኤል፥ የቃ​ር​ሔም ልጆች ዮሐ​ና​ንና ዮና​ታን፥ የተ​ን​ሁ​ሜ​ትም ልጅ ሠራያ፥ የነ​ጦ​ፋ​ዊ​ውም የዮፌ ልጆች፥ የመ​ከጢ ልጅ አዛ​ን​ያም ከሰ​ዎ​ቻ​ቸው ጋር ወደ ጎዶ​ል​ያስ ወደ መሴፋ መጡ።


በም​ድር ጽድ​ቅን የማ​ይ​ማ​ርና መል​ካ​ምን የማ​ያ​ደ​ርግ ኃጥእ አል​ቆ​አ​ልና፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ክብር እን​ዳ​ያይ ኀጢ​አ​ተ​ኛን ያስ​ወ​ግ​ዱ​ታል።


የቃ​ር​ሔም ልጅ ዮሐ​ናን፥ በየ​ሜ​ዳ​ውም የነ​በሩ የጭ​ፍራ አለ​ቆች ሁሉ ወደ ጎዶ​ል​ያስ ወደ መሴፋ መጥ​ተው፦


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛው ወር ከመ​ን​ግ​ሥት ወገ​ንና ከን​ጉሡ ዋና ዋና አለ​ቆች አንዱ የኤ​ሊ​ሳማ ልጅ የና​ታ​ንያ ልጅ እስ​ማ​ኤል ከዐ​ሥር ሰዎች ጋር ወደ መሴፋ ወደ አኪ​ቃም ልጅ ወደ ጎዶ​ል​ያስ መጣ፤ በዚ​ያም በመ​ሴፋ በአ​ንድ ላይ እን​ጀራ በሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements