Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 40:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 አይ​ሁ​ድም ሁሉ ከተ​ሰ​ደ​ዱ​በት ስፍራ ሁሉ ተመ​ለሱ፤ ወደ ይሁ​ዳም ሀገር ጎዶ​ል​ያስ ወዳ​ለ​በት ወደ መሴፋ መጡ፤ ወይ​ን​ንና የበ​ጋን ፍሬ፥ ዘይ​ት​ንም እጅግ ብዙ አከ​ማቹ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ሁላቸውም ከተበታተኑበት አገር ሁሉ ወደ ይሁዳ ምድር ተመለሱ፤ በምጽጳ ወደሚኖረውም ወደ ጎዶልያስ መጡ፤ ወይንና የበጋ ፍሬም በብዛት አከማቹ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 አይሁድ ሁሉ ከተሰደዱበት ስፍራ ሁሉ ተመለሱ፤ ወደ ይሁዳም አገር ጎዶልያስ ወዳለበት ወደ ምጽጳ መጡ፤ ወይንና የበጋንም ፍሬ እጅግ ብዙ አከማቹ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ስለዚህም ተበታትነው የሚኖሩባቸውን ስፍራዎች ሁሉ ትተው ወደ ይሁዳ ተመለሱ፤ በምጽጳ ወደሚገኘው ወደ ገዳልያም መጥተው እጅግ ብዙ የሆነ የወይን ዘለላና የሌላውንም ተክል ፍሬ በመሰብሰብ አከማቹ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 አይሁድ ሁሉ ከተሰደዱበት ስፍራ ሁሉ ተመለሱ፥ ወደ ይሁዳም አገር ጎዶልያስ ወዳለበት ወደ ምጽጳ መጡ፥ ወይንና የበጋንም ፍሬ እጅግ ብዙ አከማቹ።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 40:12
8 Cross References  

የቃ​ር​ሔም ልጅ ዮሐ​ናን፥ የጭ​ፍራ አለ​ቆ​ችም ሁሉ በይ​ሁዳ ምድር ለመ​ቀ​መጥ ከተ​ሰ​ደ​ዱ​ባ​ቸው ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ የተ​መ​ለ​ሱ​ትን የይ​ሁ​ዳን ቅሬታ ሁሉ ወሰዱ።


ስለ​ዚህ በኢ​ያ​ዜር ልቅሶ ስለ ሴባማ ወይን ግንድ አለ​ቅ​ሳ​ለሁ፤ ሐሴ​ቦ​ንና ኤል​ያሊ ሆይ፥ ዛፎ​ችሽ ወድ​ቀ​ዋል፤ የዛ​ፍ​ሽን ፍሬና የወ​ይ​ን​ሽን መከር እረ​ግ​ጣ​ለሁ፤ ተክ​ሎ​ችሽ ሁሉ ይወ​ድ​ቃሉ።


እነሆ እኔም ወደ እኛ በሚ​መ​ጡት ከለ​ዳ​ው​ያን ፊት እቆም ዘንድ በመ​ሴፋ እኖ​ራ​ለሁ፤ እና​ንተ ግን ወይ​ኑ​ንና ፍሬ​ውን፥ ዘይ​ቱ​ንም አከ​ማቹ፤ በየ​ዕ​ቃ​ች​ሁም ውስጥ ክተቱ፤ በያ​ዛ​ች​ኋ​ቸ​ውም ከተ​ሞ​ቻ​ችሁ ተቀ​መጡ።”


የቃ​ር​ሔም ልጅ ዮሐ​ናን፥ በየ​ሜ​ዳ​ውም የነ​በሩ የጭ​ፍራ አለ​ቆች ሁሉ ወደ ጎዶ​ል​ያስ ወደ መሴፋ መጥ​ተው፦


እስ​ማ​ኤ​ልም በመ​ሴፋ የነ​በ​ረ​ውን የሕ​ዝ​ቡን ቅሬታ ሁሉ፥ የን​ጉ​ሡን ሴቶች ልጆች፥ የአ​ዛ​ዦች አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳን ለአ​ኪ​ቃም ልጅ ለጎ​ዶ​ል​ያስ የሰ​ጠ​ውን በመ​ሴፋ የቀ​ሩ​ትን ሕዝብ ሁሉ መለሰ፤ የና​ታ​ን​ያም ልጅ እስ​ማ​ኤል ወደ አሞን ልጆች ይሄድ ዘንድ ተነሣ።


ለሰ​ማይ ንግ​ሥት ማጠ​ንን፥ ለእ​ር​ስ​ዋም የመ​ጠ​ጥን ቍር​ባን ማፍ​ሰ​ስን ከተ​ውን ወዲህ ግን፥ እኛ ሁላ​ችን አን​ሰ​ናል፤ በሰ​ይ​ፍና በራ​ብም አል​ቀ​ናል።


በጎች በተ​ራ​ሮች ሁሉና በረ​ዘሙ ኮረ​ብ​ቶች ሁሉ ላይ ተበ​ት​ነ​ዋል፤ በጎ​ችም በም​ድር ፊት ሁሉ ላይ ተበ​ት​ነ​ዋል፤ የሚ​ፈ​ል​ግም አል​ነ​በ​ረም፤ የሚ​መ​ል​ስም አል​ነ​በ​ረም።


Follow us:

Advertisements


Advertisements