ኤርምያስ 40:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 እነሆ እኔም ወደ እኛ በሚመጡት ከለዳውያን ፊት እቆም ዘንድ በመሴፋ እኖራለሁ፤ እናንተ ግን ወይኑንና ፍሬውን፥ ዘይቱንም አከማቹ፤ በየዕቃችሁም ውስጥ ክተቱ፤ በያዛችኋቸውም ከተሞቻችሁ ተቀመጡ።” See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 እኔም ራሴ ወደ እኛ በሚመጡት በባቢሎናውያን ፊት ልቆምላችሁ፣ በምጽጳ እቀመጣለሁ፤ እናንተ ግን ወይን፣ የበጋ ፍሬና ዘይት አምርቱ፤ በማከማቻ ዕቃዎቻችሁ ውስጥ ክተቱ፤ በያዛችኋቸውም ከተሞች ተቀመጡ።” See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 እኔም፥ እነሆ፥ ወደ እኛ በሚመጡት ከለዳውያን ፊት ለእናንተ ዋስትና ለመቆም በምጽጳ እኖራለሁ፤ እናንተ ግን ወይንንና የበጋ ፍሬ ዘይትንም አከማቹ፥ በየዕቃችሁም ውስጥ ክተቱ፥ በያዛችኋቸውም ከተሞቻችሁ ተቀመጡ።” See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 እኔም በዚህቹ በምጽጳ ከእናንተ ጋር ስለምኖር ባቢሎናውያን በሚመጡበት ጊዜ የእናንተ ወኪል ሆኜ እቆምላችኋለሁ፤ እናንተ ግን በምትኖሩባቸው መንደሮች ሁሉ የወይኑን ዘለላ፥ የወይራውን ዘይትና የሌላውን ተክል ፍሬ ሰብስባችሁ አከማቹ” See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 እኔም፥ እነሆ፥ ወደ እኛ በሚመጡት ከለዳውያን ፊት እቆም ዘንድ በምጽጳ እኖራለሁ፥ እናንተ ግን ወይንንና የበጋ ፍሬ ዘይትንም አከማቹ፥ በየዕቃችሁም ውስጥ ክተቱ፥ በያዛችኋቸውም ከተሞቻችሁ ተቀመጡ። See the chapter |