Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 3:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 በዚ​ህም ሁሉ ከዳ​ተ​ኛ​ዪቱ ይሁዳ በሐ​ሰት እንጂ በፍ​ጹም ልብዋ ወደ እኔ አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ይህም ሁሉ ሆኖ ከሓዲዋ እኅቷ ይሁዳ ወደ እኔ የተመለሰችው በማስመሰል እንጂ በሙሉ ልቧ አልነበረም” ይላል እግዚአብሔር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 በዚህም ሁሉ ግን አታላይቱ ይሁዳ በሐሰት እንጂ በፍጹም ልብዋ ወደ እኔ አልተመለሰችም፥ ይላል ጌታ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ይህን ሁሉ ከፈጸመች በኋላ እምነት የማይጣልባት የእስራኤል እኅት የሆነችው ይሁዳ፥ እንደገና ወደ እኔ ለመመለስ የምትሞክር መስላ የታየችው ከልብዋ ሳይሆን ከአንገት በላይ ነበር፤ ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 በዚህም ሁሉ አታላይቱ ይሁዳ በሐሰት እንጂ በፍጹም ልብዋ ወደ እኔ አልተመለሰችም።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 3:10
13 Cross References  

በመ​ኝ​ታ​ቸው ላይ ሆነው ያለ​ቅሱ ነበር እንጂ በል​ባ​ቸው ወደ እኔ አል​ጮ​ኹም፤ ስለ እህ​ልና ስለ ወይን ይገ​ዳ​ደሉ ነበር፤


አንተ ተክ​ለ​ሃ​ቸ​ዋል፤ ሥር ሰድ​ደ​ዋል፤ ወል​ደ​ዋል አፍ​ር​ተ​ው​ማል፤ በአ​ፋ​ቸ​ውም አንተ ቅርብ ነህ፤ ከል​ባ​ቸው ግን ሩቅ ነህ።


ቍጣ​ዬን በኀ​ጢ​አ​ተኛ ሕዝብ ላይ እል​ካ​ለሁ፤ ይማ​ር​ኳ​ቸ​ውና ይበ​ዘ​ብ​ዙ​አ​ቸው ዘንድ፥ ከተ​ሞ​ች​ንም ይረ​ግ​ጡ​አ​ቸ​ውና እንደ ትቢያ ያደ​ር​ጓ​ቸው ዘንድ ሕዝ​ቤን አዝ​ዛ​ለሁ።


አቤቱ፥ አሕ​ዛብ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል፥ አሕ​ዛብ ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል። አሕ​ዛብ ደስ ይላ​ቸ​ዋል፥ ሐሤ​ትም ያደ​ር​ጋሉ።


ኢዮ​ስ​ያ​ስም ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ምድር ሁሉ ርኩ​ሱን ሁሉ አስ​ወ​ገደ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም የተ​ገ​ኙ​ትን ሁሉ አም​ላ​ካ​ቸ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዲ​ያ​መ​ልኩ አደ​ረገ። በዘ​መኑ ሁሉ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከመ​ከ​ተል አል​ራ​ቁም።


ትበ​ድሉ ዘንድ ጥልቅ ምክ​ርን የም​ት​መ​ክሩ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሆይ፥ ተመ​ለሱ።


ቃሌን ይሰሙ ዘንድ እንቢ ወደ አሉ ወደ አባ​ቶ​ቻ​ቸው ኀጢ​አት ተመ​ለሱ፥ ያመ​ል​ኩ​አ​ቸ​ውም ዘንድ እን​ግ​ዶ​ችን አማ​ል​ክት ተከ​ተሉ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤትና የይ​ሁዳ ቤት ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ቃል ኪዳን አፈ​ረሱ።


በአ​ባ​ርና በቸ​ነ​ፈር መታ​ኋ​ችሁ፤ አት​ክ​ል​ታ​ችሁ፥ ወይ​ና​ች​ሁና በለ​ሳ​ችሁ፥ ወይ​ራ​ች​ሁም ከበጀ በኋላ ተምች በላው፤ ይህም ሆኖ እና​ንተ ወደ እኔ አል​ተ​መ​ለ​ሳ​ች​ሁም፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ጌታም አለ፥ “ይህ ሕዝብ በከ​ን​ፈ​ሮቹ ያከ​ብ​ረ​ኛ​ልና፥ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነውና፥ በከ​ንቱ ያመ​ል​ኩ​ኛል፤ ሰው ሠራሽ ትም​ህ​ር​ትም ያስ​ተ​ም​ራሉ፤


ስለ ተገ​ደሉ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ሰዎች ሌሊ​ትና ቀን አለ​ቅስ ዘንድ ለራሴ ውኃን፥ ለዐ​ይ​ኔም የዕ​ን​ባን ምንጭ ማን በሰ​ጠኝ?


እግዚአብሔር የወደደውን መቅደስ ይሁዳ አርክሶአልና፥ የእንግዳውንም አምላክ ልጅ ሚስት አድርጎ አግብቶአልና ይሁዳ አታልሎአል፥ በእስራኤልና በኢየሩሳሌም ውስጥ ርኵሰት ተሠርቶአል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements