Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 27:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ወደ ይሁዳ ንጉ​ሥም ወደ ሴዴ​ቅ​ያስ፥ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በመ​ጡት መል​እ​ክ​ተ​ኞች እጅ ወደ ኤዶ​ም​ያስ ንጉሥ፥ ወደ ሞዓ​ብም ንጉሥ፥ ወደ አሞን ልጆች ንጉሥ፥ ወደ ጢሮ​ስም ንጉሥ፥ ወደ ሲዶ​ናም ንጉሥ ላክ።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሴዴቅያስ፣ ወደ ኢየሩሳሌም በመጡት ሰዎች በኩል ለኤዶም፣ ለሞዓብ፣ ለአሞን፣ ለጢሮስና ለሲዶና ነገሥታት መልእክት ላክ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ወደ ይሁዳ ንጉሥም ወደ ሴዴቅያስ ወደ ኢየሩሳሌም በመጡት መልእክተኞች እጅ ወደ ኤዶምያስ ንጉሥ፥ ወደ ሞዓብም ንጉሥ፥ ወደ አሞንም ልጆች ንጉሥ፥ ወደ ጢሮስም ንጉሥ፥ ወደ ሲዶናም ንጉሥ ትልካቸዋለህ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 በኢየሩሳሌም ወደሚኖረው ወደ ይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ በመጡት መልእክተኞች በኩል ወደ ኤዶም፥ ሞአብ፥ ዐሞን፥ እንዲሁም ወደ ጢሮስና ሲዶና ነገሥታት መልእክት ላከ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ወደ ይሁዳ ንጉሥም ወደ ሴዴቅያስ ወደ ኢየሩሳሌም በመጡት መልእክተኞች እጅ ወደ ኤዶምያስ ንጉሥ ወደ ሞዓብም ንጉሥ ወደ አሞንም ልጆች ንጉሥ ወደ ጢሮስም ንጉሥ ወደ ሲዶናም ንጉሥ ላካቸው።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 27:3
12 Cross References  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የሰ​ሎ​ሞን ምር​ኮ​ኞ​ችን በኤ​ዶ​ም​ያስ ዘግ​ተ​ዋ​ልና፥ የወ​ን​ድ​ሞ​ች​ንም ቃል ኪዳን አላ​ሰ​ቡ​ምና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የጢ​ሮስ ኀጢ​አት አል​መ​ለ​ስ​ላ​ቸ​ውም።


“የሰው ልጅ ሆይ! የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ሠራ​ዊ​ቱን በጢ​ሮስ ላይ ጽኑ ሥራን አሠ​ራ​ቸው፤ ራስ ሁሉ የተ​ላጨ፥ ጫን​ቃም ሁሉ የተ​ላጠ ሆኖ​አል፤ ነገር ግን በላ​ይዋ ስለ አሠ​ራው ሥራ እር​ሱና ሠራ​ዊቱ ከጢ​ሮስ ደመ​ወዝ አል​ተ​ቀ​በ​ሉም።


ደግ​ሞም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም አም​ሎት በነ​በ​ረው በን​ጉሡ በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ላይ ዐመፀ፤ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ይ​መ​ለስ አን​ገ​ቱን አደ​ነ​ደነ፤ ልቡ​ንም አጠ​ነ​ከረ።


ሲዶና ሆይ፥ ባሕር፥ የባ​ሕር ምሽግ፥ “አላ​ማ​ጥ​ሁም፥ አል​ወ​ለ​ድ​ሁም፤ ጐበ​ዛ​ዝ​ት​ንም አላ​ሳ​ደ​ግ​ሁም፥ ደና​ግ​ል​ንም አላ​ሳ​ደ​ግ​ሁም” ብሎ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና እፈሪ።


ለጌ​ቶ​ቻ​ቸው እን​ዲ​ነ​ግሩ እን​ዲህ ብለህ እዘ​ዛ​ቸው፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ለጌ​ቶ​ቻ​ችሁ እን​ዲህ በሉ፦


ለይ​ሁዳ ንጉሥ ለሴ​ዴ​ቅ​ያ​ስም ይህን ቃል ሁሉ ተና​ገ​ርሁ፥ “ከባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ቀን​በር በታች አን​ገ​ታ​ች​ሁን ዝቅ አድ​ርጉ፤ ለእ​ር​ሱና ለሕ​ዝ​ቡም ተገ​ዙ​ላ​ቸው በሕ​ይ​ወ​ትም ኑሩ።


ከዚ​ህም በኋላ እን​ዲህ ሆነ፤ በዚያ ዓመት፥ በይ​ሁዳ ንጉሥ በሴ​ዴ​ቅ​ያስ መን​ግ​ሥት መጀ​መ​ሪያ፥ በአ​ራ​ተ​ኛው ዓመት በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ወር ሐሰ​ተ​ኛው ነቢይ የገ​ባ​ዖን ሰው የዓ​ዙር ልጅ ሐና​ንያ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በካ​ህ​ና​ትና በሕ​ዝብ ሁሉ ፊት እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረኝ፦


Follow us:

Advertisements


Advertisements