Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 27:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ስላ​ል​ወ​ሰ​ዳ​ቸው ዓም​ዶች፥ ስለ ባሕ​ሩም፥ ስለ መቀ​መ​ጫ​ዎ​ቹም፥ በዚች ከተማ ስለ ቀሩት ዕቃ​ዎች ሁሉ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በዚህች ከተማ ስለ ቀሩት ዐምዶች፣ ከናስ ስለ ተሠራው ትልቁ ገንዳ፣ ስለ ተንቀሳቃሽ ማስቀመጫዎችና ስለ ሌሎቹም ዕቃዎች እንዲህ ይላልና፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 በዚህች ከተማ ቀርተው ስለ ተተዉት ዕቃዎች፥ ስለ ዓምዶቹ፥ ስለ ኩሬውም፥ ስለ መቀመጫዎቹም፥ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19-20 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የይሁዳ ንጉሥ የሆነውን የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንን ከይሁዳና ከኢየሩሳሌም ታላላቅ ሰዎች ጋር ወደ ባቢሎን ማርኮ በወሰደው ጊዜ ዐምዶችን፥ ከነሐስ የተሠራውን የውሃ ማጠራቀሚያ፥ የብረት ማስቀመጫዎችንና ሌሎችንም የቤተ መቅደስ ዕቃዎች በኢየሩሳሌም ትቶአቸው ሄዶ ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19-20 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የይሁዳን ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንንና የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ከበርቴዎች ሁሉ ማርኮ ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ባፈለሳቸው ጊዜ ስላልወሰዳቸው ዓምዶች ስለ ኵሬውም ስለ መቀመጫዎቹም በዚህችም ከተማ ስለ ቀረች ዕቃ ሁሉ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፥

See the chapter Copy




ኤርምያስ 27:19
10 Cross References  

ከለ​ዳ​ው​ያ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ውስጥ የነ​በ​ሩ​ትን የናስ ዓም​ዶች፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት የነ​በ​ሩ​ትን መቀ​መ​ጫ​ዎ​ችና የናስ ኵሬ​ዎች ሰባ​በሩ፤ ናሱ​ንም ወደ ባቢ​ሎን ወሰዱ።


የአ​ን​ዱም ዓምድ ቁመት ዐሥራ ስም​ንት ክንድ ነበረ፥ የና​ስም ጕል​ላት ነበ​ረ​በት፤ የጕ​ል​ላ​ቱም ርዝ​መት ሦስት ክንድ ነበረ፥ በጕ​ል​ላ​ቱም ላይ በዙ​ሪ​ያው የናስ መር​በ​ብና ሮማ​ኖች ነበሩ፤ እን​ዲ​ሁም ደግሞ በሁ​ለ​ተ​ኛው ዓምድ ላይ መር​በብ ነበ​ረ​በት።


ከፈ​ሰ​ሰም ናስ ከዳር እስከ ዳር ዐሥር ክንድ፥ ቁመ​ቱም አም​ስት ክንድ፥ በዙ​ሪ​ያ​ውም ሠላሳ ክንድ የሆነ ክብ ኩሬ ሠራ።


ዐሥ​ርም የናስ መቀ​መ​ጫ​ዎ​ችን ሠራ፤ የአ​ን​ዱም መቀ​መጫ ርዝ​መት አራት ክንድ፥ ወር​ዱም አራት ክንድ፥ ቁመ​ቱም ሦስት ክንድ ነበረ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት ዕቃ ሁሉ፥ ታላ​ቁ​ንና ታና​ሹን፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት መዝ​ገብ፥ የን​ጉ​ሡ​ንም ቤት መዝ​ገብ፥ የአ​ለ​ቆ​ቹ​ንም ቤት መዝ​ገብ፥ እነ​ዚ​ህን ሁሉ ወደ ባቢ​ሎን ወሰደ።


ዮድ። አስ​ጨ​ና​ቂው በም​ኞቷ ሁሉ ላይ እጁን ዘረጋ፤ ወደ ጉባ​ኤህ እን​ዳ​ይ​ገቡ ያዘ​ዝ​ሃ​ቸው አሕ​ዛብ ወደ መቅ​ደ​ስዋ ሲገቡ አይ​ታ​ለ​ችና።


Follow us:

Advertisements


Advertisements