Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 27:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ለካ​ህ​ና​ትም ለዚ​ህም ሕዝብ እን​ዲህ ብዬ ተና​ገ​ርሁ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ሐሰ​ተ​ኛ​ውን ትን​ቢት ይና​ገ​ሩ​ላ​ች​ኋ​ልና፦ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ዕቃ በቅ​ርብ ጊዜ ከባ​ቢ​ሎን ይመ​ለ​ሳል የሚ​ሉ​አ​ች​ሁን የነ​ቢ​ያ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ቃል አት​ስሙ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 እኔም ለካህናቱና ለዚህ ሕዝብ ሁሉ እንዲህ አልሁ፤ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘የእግዚአብሔር ቤት ዕቃ ከባቢሎን ቶሎ ይመለሳል’ የሚሏችሁን ነቢያት አትስሟቸው፤ የሚነግሯችሁ የሐሰት ትንቢት ነውና።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ለካህናትም ለዚህም ሕዝብ ሁሉ እንዲህ ብዬ ተናገርሁ፦ “ጌታ እንዲህ ይላል፦ ሐሰተኛን ትንቢት ለእናንተ በመናገር፦ ‘እነሆ፥ የጌታ ቤት ዕቃዎች በቅርብ ጊዜ ከባቢሎን ይመለሳሉ’ ብለው ትንቢት የሚነግሩአችሁን የነብዮቻችሁን ቃላት አትስሙ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ከዚህ በኋላ ለካህናቱና ለሕዝቡ እንዳስታውቅ እግዚአብሔር የሚከተለውን ነገረኝ፤ እንዲህ ብዬም ነገርኳቸው፦ “ ‘የቤተ መቅደሱ ዕቃ ሁሉ ከባቢሎን ተመልሶ በፍጥነት ይመጣል’ እያሉ የሚነግሩአችሁን ነቢያት ሁሉ አትስሙአቸው፤ እነርሱ የሚናገሩት የሐሰት ትንቢት ነው፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ለካህናትም ለዚህም ሕዝብ እንዲህ ብዬ ተናገርሁ፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሐሰተኛውን ትንቢት ይናገሩላችኋልና፦ የእግዚአብሔር ቤት ዕቃ በቅርብ ጊዜ ከባቢሎን ይመለሳል የሚሉአችሁን የነቢያቶቻችሁን ቃል አትስሙ።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 27:16
7 Cross References  

የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ከዚች ስፍራ ወደ ባቢ​ሎን የወ​ሰ​ዳ​ቸ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ዕቃ​ዎች ሁሉ በሁ​ለት ዓመት ውስጥ ወደ​ዚ​ህች ስፍራ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤተ መዛ​ግ​ብት ሁሉ የን​ጉ​ሡ​ንም ቤተ መዛ​ግ​ብት ከዚያ አወጣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገ​ረው የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ሰሎ​ሞን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ የሠ​ራ​ውን የወ​ር​ቁን ዕቃ ሁሉ ሰባ​በረ።


ከም​ድ​ራ​ችሁ እን​ዲ​ያ​ር​ቁ​አ​ችሁ፥ እኔም እን​ዳ​ሳ​ድ​ዳ​ችሁ፥ እና​ን​ተም እን​ድ​ት​ጠፉ ሐሰ​ተኛ ትን​ቢ​ትን ይና​ገ​ሩ​ላ​ች​ኋ​ልና።


ሐሰ​ተ​ኛን ትን​ቢት ይና​ገ​ሩ​ላ​ች​ኋ​ልና፦ ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ አት​ገ​ዙም የሚ​ሉ​አ​ች​ሁን የነ​ቢ​ያ​ትን ቃል አት​ስሙ።


ሽማ​ግ​ሌ​ውና ለፊት የሚ​ያ​ደ​ላው እርሱ ራስ ነው፤ ዐመ​ፅ​ንም የሚ​ያ​ስ​ተ​ምር ነቢይ እርሱ ጅራት ነው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements