Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 27:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ነገር ግን ከባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ቀን​በር በታች አን​ገ​ቱን ዝቅ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ው​ንና የሚ​ገ​ዛ​ለ​ትን ሕዝብ በሀ​ገሩ ላይ እተ​ወ​ዋ​ለሁ፤ እር​ሱም ያር​ሳ​ታል፤ ይቀ​መ​ጥ​ባ​ት​ማል።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ነገር ግን ከባቢሎን ንጉሥ ቀንበር በታች ዐንገቱን ዝቅ የሚያደርገውንና የሚያገለግለውን ማንኛውንም ሕዝብ በገዛ ምድሩ እንዲቀርና እያረሰም በዚያ እንዲኖር አደርገዋለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር።” ’ ”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ነገር ግን ከባቢሎን ንጉሥ ቀንበር በታች አንገቱን ዝቅ የሚያደርገውንና የሚያገለግለውን ሕዝብ በአገሩ ላይ እተወዋለሁ፤ እነርሱም ያርሱአታል ይቀመጡባታልም፥ ይላል ጌታ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ነገር ግን በባቢሎን ንጉሥ ቀንበር ሥር ሆኖ የሚገዛለትና የሚያገለግለው ሕዝብ በገዛ ምድሩ እያረሰ እንዲኖር እፈቅድለታለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ነገር ግን ከባቢሎን ንጉሥ ቀንበር በታች አንገቱን ዝቅ የሚያደርገውንና የሚገዛለትን ሕዝብ በአገሩ ላይ እተወዋለሁ፥ እነርሱም ያርሱአታል ይቀመጡባትማል።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 27:11
8 Cross References  

“ለባ​ቢ​ሎን ንጉ​ሥም ለና​ቡ​ከ​ን​ደ​ነ​ፆር የማ​ይ​ገ​ዛ​ውን፥ ከባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ቀን​በር በታች አን​ገ​ቱን ዝቅ የማ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን ሕዝ​ብና መን​ግ​ሥት፥ ያን ሕዝብ በእጁ እስ​ካ​ጠ​ፋው ድረስ በሰ​ይ​ፍና በራብ፥ በቸ​ነ​ፈ​ርም እቀ​ጣ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሰን​ሰ​ለ​ትና ቀን​በር ሥራ፤ በአ​ን​ገ​ት​ህም ላይ አድ​ርግ፤


በዚ​ህች ከተማ ውስጥ የሚ​ቀ​መጥ በሰ​ይ​ፍና በራብ፥ በቸ​ነ​ፈ​ርም ይሞ​ታል፤ ወጥቶ ወደ ከበ​ቡ​አ​ችሁ ወደ ከለ​ዳ​ው​ያን የሚ​ገባ ግን በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል፤ ሰው​ነ​ቱም ምርኮ ትሆ​ና​ለች።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በዚች ከተማ የሚ​ቀ​መጥ በሰ​ይ​ፍና በራብ፥ በቸ​ነ​ፈ​ርም ይሞ​ታል፤ ወደ ከለ​ዳ​ው​ያን የሚ​ወጣ ግን በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል፤ ነፍ​ሱም እንደ ምርኮ ትሆ​ን​ለ​ታ​ለች፤ በሕ​ይ​ወ​ትም ይኖ​ራል።


ለይ​ሁዳ ንጉሥ ለሴ​ዴ​ቅ​ያ​ስም ይህን ቃል ሁሉ ተና​ገ​ርሁ፥ “ከባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ቀን​በር በታች አን​ገ​ታ​ች​ሁን ዝቅ አድ​ርጉ፤ ለእ​ር​ሱና ለሕ​ዝ​ቡም ተገ​ዙ​ላ​ቸው በሕ​ይ​ወ​ትም ኑሩ።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቤት ከተ​በ​ተ​ኑ​ባ​ቸው አሕ​ዛብ ዘንድ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብና በሕ​ዝብ ፊትም እቀ​ደ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ለባ​ሪ​ያዬ ለያ​ዕ​ቆ​ብም በሰ​ጠ​ኋት ምድ​ራ​ቸው ይቀ​መ​ጣሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements