Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 26:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ንጉ​ሡም ኢዮ​አ​ቄም ሰዎ​ችን ወደ ግብፅ ላከ፤ የአ​ክ​ቦ​ርን ልጅ ኤል​ና​ታ​ንን፥ ሌሎ​ች​ንም ሰዎች ከርሱ ጋራ ወደ ግብፅ ላካ​ቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ይሁን እንጂ ንጉሥ ኢዮአቄም የዓክቦርን ልጅ ኤልናታንንና ከርሱም ጋራ ሌሎችን ሰዎች ወደ ግብጽ ላካቸው፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ንጉሡም ኢዮአቄም የዓክቦርን ልጅ ኤልናታንን ከእርሱም ጋር ሌሎችን ሰዎች ወደ ግብጽ ላካቸው፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ይሁን እንጂ ንጉሥ ኢዮአቄም የዓክቦር ልጅ ኤልናታንና ሌሎችም ሰዎች ወደ ግብጽ ወርደው ኡሪያን ይዘው እንዲመጡ አዘዘ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ንጉሡም ኢዮአቄም የዓክቦርን ልጅ ኤልናታንን ከእርሱም ጋር ሌሎችን ሰዎች ወደ ግብጽ ላካቸው፥

See the chapter Copy




ኤርምያስ 26:22
10 Cross References  

ወደ ንጉ​ሡም ቤት ወደ ጸሓ​ፊው ክፍል ወረደ፤ እነ​ሆም አለ​ቆቹ ሁሉ፥ ጸሓ​ፊው ኤሊ​ሳማ፥ የሸ​ማያ ልጅ ድላያ፥ የዓ​ክ​ቦር ልጅ ኤል​ና​ታን፥ የሳ​ፋን ልጅ ገማ​ርያ፥ የሐ​ና​ንያ ልጅ ሴዴ​ቅ​ያስ፥ አለ​ቆ​ቹም ሁሉ በዚያ ተቀ​ም​ጠው ነበር።


እን​ዲ​ሁም ካህኑ ኬል​ቅ​ያ​ስና አኪ​ቃም ዓክ​ቦ​ርም ሳፋ​ንና ዓሳ​ያም ወደ ልብስ ጠባ​ቂው ወደ ሓስራ ልጅ ወደ ቴቁዋ ልጅ ወደ ሴሌም ሚስት ወደ ነቢ​ዪቱ ወደ ሕል​ዳና ሄዱ፤ እር​ስ​ዋም በዚያ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በሁ​ለ​ተ​ኛው ክፍል ተቀ​ምጣ ነበር፤ ለእ​ር​ስ​ዋም ነገ​ሩ​አት።


ንጉ​ሡም ካህ​ኑን ኬል​ቅ​ያ​ስን፥ የሳ​ፋ​ን​ንም ልጅ አኪ​ቃ​ምን፥ የሚ​ክ​ዩ​ንም ልጅ ዓክ​ቦ​ርን፥ ጸሓ​ፊ​ው​ንም ሳፋ​ንን፥ የን​ጉ​ሡ​ንም ብላ​ቴና ዓስ​ያን እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፦


ነገር ግን ኤል​ና​ታ​ንና ጎዶ​ልያ፥ ገማ​ር​ያም ክር​ታ​ሱን እን​ዳ​ያ​ቃ​ጥል ንጉ​ሡን ለመ​ኑት፤ እርሱ ግን አል​ሰ​ማ​ቸ​ውም።


ሳኦ​ልም ሞተ፤ በእ​ር​ሱም ፈንታ የዓ​ክ​ቦር ልጅ በአ​ል​ሐ​ናን ነገሠ።


ኤር​ም​ያ​ስም የይ​ሁዳ ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያስ ወደ ባቢ​ሎን ንጉሥ ወደ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ወደ ባቢ​ሎን በላ​ካ​ቸው በሳ​ፋን ልጅ በኤ​ል​ዓ​ሣና በኬ​ል​ቅ​ያስ ልጅ በገ​ማ​ርያ እጅ ደብ​ዳ​ቤ​ውን እን​ዲህ ሲል ላከው፦


ኤር​ም​ያ​ስ​ንም ከግ​ዞት ቤቱ አደ​ባ​ባይ አወ​ጡት፤ ወደ ቤቱም ይወ​ስ​ደው ዘንድ ለሳ​ፋን ልጅ ለአ​ኪ​ቃም ልጅ ለጎ​ዶ​ል​ያስ ሰጡት፤ እን​ዲ​ህም በሕ​ዝብ መካ​ከል ተቀ​መጠ።


በፊ​ታ​ቸ​ውም ከእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሰባ ሰዎ​ችና የሳ​ፋን ልጅ ያእ​ዛ​ንያ ቆመው ነበር፤ ሰውም ሁሉ እያ​ን​ዳ​ንዱ በእጁ ጥና​ውን ይዞ ነበር፥ የዕ​ጣ​ኑም ጢስ ሽታ ይወጣ ነበር።


Follow us:

Advertisements


Advertisements