Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 26:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 አለ​ቆ​ቹና ሕዝ​ቡም ሁሉ ለካ​ህ​ና​ትና ለነ​ቢ​ያተ ሐሰት፥ “ይህ ሰው በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ተና​ግ​ሮ​ና​ልና ሞት አይ​ገ​ባ​ውም” አሉ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ባለሥልጣኖቹና ሕዝቡም ሁሉ ለካህናትና ለነቢያት፣ “ይህ ሰው በአምላካችን በእግዚአብሔር ስም ተናግሯልና ሊገደል አይገባውም” አሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 አለቆቹና ሕዝቡም ሁሉ ለካህናትና ለነቢያት፦ “በአምላካችን በጌታ ስም ስለ ተናገረን ይህ ሰው ሞት አይገባውም” አሉ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ከዚህ በኋላ መሪዎቹና ሕዝቡ፦ “ይህ ሰው የተናገረን በአምላካችን በእግዚአብሔር ስም ስለ ሆነ ሞት አይገባውም” ሲሉ ለካህናቱና ለነቢያቱ ተናገሩ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 አለቆቹና ሕዝቡም ሁሉ ለካህናትና ለነቢያት፦ ይህ ሰው በአምላካችን በእግዚአብሔር ስም ተናግሮናልና ሞት አይገባውም አሉ።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 26:16
19 Cross References  

ስለ ሕጋ​ቸ​ውም ብቻ እንደ ከሰ​ሱት ተረ​ዳሁ፤ ለሞ​ትና ለመ​ታ​ሰር የሚ​ያ​በቃ ሌላ በደል ግን የለ​በ​ትም።


ታላቅ ውካ​ታም ሆነ፤ ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያ​ንም ወገን የሆኑ ጸሐ​ፍት ተነ​ሥ​ተው ይጣ​ሉና ይከ​ራ​ከሩ ጀመሩ፤ “በዚህ ሰው ላይ ያገ​ኘ​ነው ክፉ ነገር የለም፤ መን​ፈስ ወይም መል​አክ ተና​ግ​ሮት እንደ ሆነ እንጃ፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር አን​ጣላ” አሉ።


እኔ ግን ለሞት የሚ​ያ​ደ​ር​ሰው በደል እን​ዳ​ል​ሠራ እጅግ መር​ምሬ፥ እር​ሱም ራሱ ወደ ቄሣር ይግ​ባኝ ማለ​ትን ስለ​ወ​ደደ እን​ግ​ዲህ ልል​ከው ቈር​ጫ​ለሁ።


ነገር ግን ኤል​ና​ታ​ንና ጎዶ​ልያ፥ ገማ​ር​ያም ክር​ታ​ሱን እን​ዳ​ያ​ቃ​ጥል ንጉ​ሡን ለመ​ኑት፤ እርሱ ግን አል​ሰ​ማ​ቸ​ውም።


አለ​ቆ​ቹም ባሮ​ክን፥ “አን​ተና ኤር​ም​ያስ ሂዱ፤ ተሸ​ሸጉ፤ ወዴ​ትም እንደ ሆና​ችሁ ማንም አይ​ወቅ” አሉት።


የመቶ አለ​ቃ​ውም የሆ​ነ​ውን ነገር አይቶ፥ “ይህ ሰው በእ​ው​ነት ጻድቅ ነበረ”ብሎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገ​ነው።


በእ​ኛስ በሚ​ገባ ተፈ​ር​ዶ​ብ​ናል፤ እንደ ሥራ​ች​ንም ፍዳ​ች​ንን ተቀ​በ​ልን፤ ይህ ግን ምንም የሠ​ራው ክፉ ሥራ የለም።”


የመቶ አለቃም ከእርሱም ጋር ኢየሱስን የሚጠብቁ መናወጡንና የሆነውን ነገር አይተው “ይህ በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነበረ፤” ብለው እጅግ ፈሩ።


ካህ​ና​ቱና ነቢ​ያተ ሐሰ​ትም ለአ​ለ​ቆ​ቹና ለሕ​ዝቡ ሁሉ፥ “በጆ​ሮ​አ​ችሁ እንደ ሰማ​ችሁ በዚች ከተማ ላይ ትን​ቢት ተና​ግ​ሮ​አ​ልና ይህ ሰው ሞት የሚ​ገ​ባው ነው” ብለው ተና​ገሩ።


ቅንነትን የሚሹ ሰላምን ያገኛሉ።


ሰው ሁሉ ወንድ ባሪ​ያ​ው​ንና ሴት ባሪ​ያ​ውን አር​ነት እን​ዲ​ያ​ወጣ፥ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲ​ህም ማንም እን​ዳ​ይ​ገ​ዛ​ቸው ወደ ቃል ኪዳኑ የገቡ አለ​ቆች ሁሉና ሕዝቡ ሁሉ ሰሙ፤ አር​ነ​ትም አወ​ጡ​አ​ቸው።


አለ​ቆ​ችም በኤ​ር​ም​ያስ ላይ ተቈ​ጥ​ተው መቱት፤ የግ​ዞት ቤት አድ​ር​ገ​ውት ነበ​ርና ወደ ጸሓ​ፊው ወደ ዮና​ታን ቤት ላኩት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements