Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 26:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 የይ​ሁ​ዳም አለ​ቆች ይህን በሰሙ ጊዜ ከን​ጉሡ ቤት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወጡ፤ በአ​ዲ​ሱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ደጅ መግ​ቢያ ተቀ​መጡ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 የይሁዳም ባለሥልጣኖች ስለ እነዚህ ነገሮች በሰሙ ጊዜ፣ ከቤተ መንግሥት ወደ እግዚአብሔር ቤት ወጡ፤ በእግዚአብሔር ቤት፣ አዲሱ በር በተባለው መግቢያ ተቀመጡ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 የይሁዳም አለቆች እነዚህን ነገሮች በሰሙ ጊዜ ከንጉሥ ቤት ወደ ጌታ ቤት ወጡ፥ በአዲሱም በጌታ ቤት ደጅ መግቢያ ተቀመጡ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 የይሁዳ መሪዎችም የሆነውን ነገር በሰሙ ጊዜ ከቤተ መንግሥት ወጥተው ወደ ቤተ መቅደስ መጡ፤ በቤተ መቅደሱም በአዲሱ የቅጽር በር ስፍራቸውን ያዙ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 የይሁዳም አለቆች ይህን በሰሙ ጊዜ ከንጉሥ ቤት ወደ እግዚአብሔር ቤት ወጡ፥ በአዲሱም በእግዚአብሔር ቤት ደጅ መግቢያ ተቀመጡ።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 26:10
15 Cross References  

ባሮ​ክም የኤ​ር​ም​ያ​ስን ቃል በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በላ​ይ​ኛው አደ​ባ​ባይ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በአ​ዲሱ በር መግ​ቢያ ባለው በጸ​ሓ​ፊው በሳ​ፋን ልጅ በገ​ማ​ርያ ክፍል በሕ​ዝቡ ሁሉ ጆሮ በመ​ጽ​ሐፉ አን​በበ።


በው​ስ​ጥዋ ያሉ አለ​ቆ​ችዋ የስ​ስ​ትን ትርፍ ለማ​ግ​ኘት ሲሉ ደምን ያፈ​ስሱ ዘንድ፥ ነፍ​ሶ​ች​ንም ያጠፉ ዘንድ እን​ደ​ሚ​ና​ጠቁ ተኵ​ላ​ዎች ናቸው።


“እነሆ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት አለ​ቆች እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ከዘ​መ​ዶ​ቻ​ቸው ጋር ደም ያፈ​ስሱ ዘንድ በአ​ንቺ ውስጥ ተባ​በሩ።


ነገር ግን ኤል​ና​ታ​ንና ጎዶ​ልያ፥ ገማ​ር​ያም ክር​ታ​ሱን እን​ዳ​ያ​ቃ​ጥል ንጉ​ሡን ለመ​ኑት፤ እርሱ ግን አል​ሰ​ማ​ቸ​ውም።


የይ​ሁ​ዳን አለ​ቆ​ችና የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን አለ​ቆች፥ ጃን​ደ​ረ​ቦ​ች​ንና ካህ​ና​ት​ንም፥ በእ​ን​ቦ​ሳም ቍራጭ መካ​ከል ያለ​ፉ​ትን የሀ​ገ​ሩን ሕዝብ ሁሉ፥


ነገር ግን በሕ​ዝቡ እጅ እን​ዳ​ይ​ሰ​ጥና እን​ዳ​ይ​ገ​ድ​ሉት የሳ​ፋን ልጅ የአ​ኪ​ቃም እጅ ከኤ​ር​ም​ያስ ጋር ነበ​ረች።


ነገር ግን የጣ​ዖ​ታ​ቱን ቤት አላ​ስ​ወ​ገ​ደም፤ ሕዝ​ቡም ገና በኮ​ረ​ብ​ቶች ላይ ይሠ​ዉና ያጥኑ ነበር። እር​ሱም የላ​ይ​ኛ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት በር ሠራ።


ንጉ​ሡም ኢዮ​አ​ቄም፥ ሠራ​ዊቱ ሁሉ፥ አለ​ቆ​ቹም ሁሉ ቃሉን በሰሙ ጊዜ ንጉሡ ሊገ​ድ​ለው ፈለገ፤ ኡር​ያም ይህን በሰማ ጊዜ ፈርቶ ሸሸ፤ ወደ ግብ​ፅም ገባ።


ሰው ሁሉ ወንድ ባሪ​ያ​ው​ንና ሴት ባሪ​ያ​ውን አር​ነት እን​ዲ​ያ​ወጣ፥ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲ​ህም ማንም እን​ዳ​ይ​ገ​ዛ​ቸው ወደ ቃል ኪዳኑ የገቡ አለ​ቆች ሁሉና ሕዝቡ ሁሉ ሰሙ፤ አር​ነ​ትም አወ​ጡ​አ​ቸው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት የላ​ይ​ኛ​ውን በር ሠራ፤ በዖ​ፌ​ልም ቅጥር ላይ ብዙ ሠራ።


ጳስ​ኮ​ርም ነቢ​ዩን ኤር​ም​ያ​ስን ገረ​ፈው፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት በነ​በ​ረው በላ​ይ​ኛው በብ​ን​ያም በር ባለው አዘ​ቅት ውስጥ ጣለው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements