Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 25:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 በይ​ሁዳ ንጉሥ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ በኢ​ዮ​አ​ቄም በአ​ራ​ተ​ኛው ዓመት፥ በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ዓመት፥ ስለ ይሁዳ ሕዝብ ሁሉ ወደ ኤር​ም​ያስ የመ​ጣው ቃል ይህ ነው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 የይሁዳ ንጉሥ የኢዮስያስ ልጅ ኢዮአቄም በነገሠ በአራተኛው ዓመት፣ ይህም ማለት በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር ዘመነ መንግሥት በመጀመሪያው ዓመት፣ ስለ ይሁዳ ሕዝብ ሁሉ ለኤርምያስ ቃል መጣለት፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም በአራተኛው ዓመት በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር በመጀመሪያው ዓመት፥ ስለ ይሁዳ ሕዝብ ሁሉ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 የኢዮስያስ ልጅ ኢዮአቄም በይሁዳ በነገሠ በአራተኛው ዓመት እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ሕዝብ ተናገረኝ፤ ይህም የሆነው የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በነገሠ በመጀመሪያው ዓመት ነበር፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም በአራተኛው ዓመት፥ በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር በመጀመሪያው ዓመት፥ ስለ ይሁዳ ሕዝብ ሁሉ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 25:1
13 Cross References  

እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በይ​ሁዳ ንጉሥ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ በኢ​ዮ​አ​ቄም በአ​ራ​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት ይህ ቃል ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወደ ኤር​ም​ያስ እን​ዲህ ሲል መጣ።


በግ​ብፅ ላይ፤ በኤ​ፍ​ራ​ጥስ ወንዝ አጠ​ገብ በከ​ር​ኬ​ማስ በነ​በ​ረው፥ በይ​ሁዳ ንጉሥ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ በኢ​ዮ​አ​ቄም በአ​ራ​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር በመ​ታው በግ​ብፅ ንጉሥ በፈ​ር​ዖን ኒካዑ ሠራ​ዊት፥


የግ​ብ​ፅም ንጉሥ ፈር​ዖን ኒካዑ የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ የኢ​ዮ​ስ​ያ​ስን ልጅ ኤል​ያ​ቄ​ምን በአ​ባቱ ፋንታ በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ አነ​ገሠ፤ ስሙ​ንም ኢዮ​አ​ቄም ብሎ ለወጠ፤ ፈር​ዖን ኒካ​ዑም ወን​ድ​ሙን ኢዮ​አ​ክ​ስን ይዞ ወደ ግብፅ ወሰ​ደው። በዚ​ያም ሞተ። 4 ‘ሀ’ ወር​ቅ​ንና ብርን ለፈ​ር​ዖን ሰጠ። በዚ​ያን ጊዜም ምድር በፈ​ር​ዖን ትእ​ዛዝ ብር መገ​በ​ሯን ጀመ​ረች። 4 ‘ለ’ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም እን​ደ​ሚ​ች​ለው ለፈ​ር​ዖን ኒካዑ እን​ዲ​ገ​ብር ከሀ​ገ​ሪቱ ሕዝብ ወር​ቅ​ንና ብርን ጠየቀ።


የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር በእ​ርሱ ላይ ወጥቶ ወደ ባቢ​ሎን ይወ​ስ​ደው ዘንድ በሰ​ን​ሰ​ለት አሰ​ረው።


በይ​ሁ​ዳም ንጉሥ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ በኢ​ዮ​አ​ቄም ዘመን፥ እስከ ይሁዳ ንጉሥ እስከ ኢዮ​ስ​ያስ ልጅ እስከ ሴዴ​ቅ​ያስ እስከ ዐሥራ አን​ደ​ኛው ዓመት ፍጻሜ፥ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እስከ ተማ​ረ​ከ​ች​በት እስከ አም​ስ​ተ​ኛው ወር ድረስ መጣ።


በይ​ሁዳ ንጉሥ በሴ​ዴ​ቅ​ያስ በዐ​ሥ​ረ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት፥ በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር በዐ​ሥራ ስም​ን​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወደ ኤር​ም​ያስ የመ​ጣው ቃል ይህ ነው።


በይ​ሁዳ ንጉሥ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ በኢ​ዮ​አ​ቄም በአ​ራ​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት እነ​ዚ​ህን ቃላት ከኤ​ር​ም​ያስ አፍ በመ​ጽ​ሐፍ በጻ​ፋ​ቸው ጊዜ፥ ነቢዩ ኤር​ም​ያስ ለኔ​ርዩ ልጅ ለባ​ሮክ የተ​ና​ገ​ረው ቃል ይህ ነው።


ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወደ ኤር​ም​ያስ የመጣ ቃል ይህ ነው፤ እን​ዲ​ህም አለ፦


በይ​ሁዳ ንጉሥ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ በኢ​ዮ​አ​ቄም ዘመን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወደ ኤር​ም​ያስ የመጣ ቃል ይህ ነው፤ እን​ዲህ ሲል፦


Follow us:

Advertisements


Advertisements