ኤርምያስ 23:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሕዝቤን ስለሚጠብቁ እረኞች እንዲህ ይላል፥ “በጎችን በትናችኋል፤ አባርራችኋቸውማል፥ አልጐበኛችኋቸውምም፤ እነሆ! እንደ ሥራችሁ ክፋት እጐበኛችኋለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም2 ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሕዝቤን ስለሚጠብቁ እረኞች እንዲህ ይላል፤ “መንጋዬን ስለ በተናችሁ፣ ስላባረራችሁና ተገቢውን ጥንቃቄ ስላላደረጋችሁላቸው፣ ለክፋታችሁ ተገቢውን ቅጣት አመጣባችኋለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 ስለዚህ የእስራኤል አምላክ ጌታ ሕዝቤን ስለሚጠብቁ እረኞች እንዲህ ይላል፦ “እናንተ በጎቼን በትናችኋል አባርራችኋቸዋልም አልጐበኛችኋቸውምም፤ እነሆ፥ ስለ ክፉ ሥራችሁ እጐበኛችኋለሁ፥ ይላል ጌታ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የሕዝቡ ጠባቂዎች መሆን ስለሚገባቸው መሪዎች እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቤን እንደሚገባ አልጠበቃችሁም፤ ይልቁንም አሳዳችሁ በተናችሁ፤ ስለዚህ ስለ ፈጸማችሁት ክፋት ሁሉ እቀጣችኋለሁ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሕዝቤን ስለሚጠብቁ እረኞች እንዲህ ይላል፦ በጎቼን በትናችኋል አባርራችኋቸውማል አልጐበኛችኋቸውምም፥ እነሆ፥ የሥራችሁን ክፋት እጐበኝባችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር። See the chapter |