Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 21:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 የይ​ሁዳ ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያስ የመ​ል​ክ​ያን ልጅ ጳስ​ኮ​ር​ንና የካ​ህ​ኑን የመ​ዕ​ሴ​ይን ልጅ ሶፎ​ን​ያ​ስን ወደ ኤር​ም​ያስ በላከ ጊዜ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወደ ኤር​ም​ያስ የመጣ ቃል ይህ ነው፦ እን​ዲ​ህም አለ፦

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ፣ የመልክያን ልጅ ፋስኮርን እንዲሁም የመዕሤያን ልጅ ካህኑን ሶፎንያስን ወደ እርሱ በላከ ጊዜ፣ ቃል ከእግዚአብሔር ወደ ኤርምያስ መጣ፤ የተላኩትም እንዲህ ብለውት ነበር፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ከጌታ ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፤ ይህም የሆነው ንጉሡ ሴዴቅያስ የመልክያን ልጅ ጳስኮርንና ካህኑን የመዕሤያን ልጅ ሶፎንያስ ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል በላከበት ጊዜ ነው፦

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ የመልክያን ልጅ ፓሽሑርንና የመዕሤያን ልጅ ካህኑን ሶፎንያስን ወደ እኔ ልኮ እንዲህ ሲል አስጠየቀኝ፦

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል ይህ ነው።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 21:1
20 Cross References  

ንጉ​ሡም ሴዴ​ቅ​ያስ፥ “ወደ አም​ላ​ካ​ችን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እኛ ጸልይ” ብሎ የሰ​ሌ​ም​ያን ልጅ ዮካ​ል​ንና ካህ​ኑን የማ​ሴ​ውን ልጅ ሶፎ​ን​ያ​ስን ወደ ነቢዩ ወደ ኤር​ም​ያስ ላከ።


“የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ አለው ሕዝብ ሁሉ፥ ወደ ካህ​ኑም ወደ ማሴው ልጅ ወደ ሶፎ​ን​ያስ፥ ወደ ካህ​ና​ቱም ሁሉ ደብ​ዳ​ቤ​ዎ​ችን በስሜ እን​ዲህ ስትል ልከ​ሃል፦


የአ​ዛ​ዦ​ቹም አለቃ ታላ​ቅን ካህን ሠራ​ያን፥ ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ካህን ሶፎ​ን​ያ​ስን፥ ሦስ​ቱ​ንም በረ​ኞች ወሰደ፤


ኤር​ም​ያስ ለሕ​ዝቡ ሁሉ እን​ዲህ ሲል የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል የና​ታን ልጅ ሰፋ​ን​ያስ፥ የጳ​ስ​ኮ​ርም ልጅ ጎዶ​ል​ያስ፥ የሰ​ሌ​ም​ያም ልጅ ዮካል፥ የመ​ል​ክ​ያም ልጅ ጳስ​ኮር ሰሙ።


የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር በይ​ሁዳ ያነ​ገ​ሠው የኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ ሴዴ​ቅ​ያስ በኢ​ዮ​አ​ቄም ልጅ በኢ​ኮ​ን​ያን ፋንታ ነገሠ።


የመ​ል​ክያ ልጅ፥ የጳ​ስ​ኮር ልጅ፥ የይ​ሮ​ሐም ልጅ፥ አዳያ፤ የኤ​ሜር ልጅ የም​ስ​ል​ሞት ልጅ፥ የሜ​ሱ​ላም ልጅ፥ የኤ​ሕ​ዜራ ልጅ፥ የዓ​ዴ​ኤል ልጅ መዕ​ሣይ፤


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የቤ​ቱን ሥራ የሠሩ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ስም​ንት መቶ ሃያ ሁለት የመ​ል​ክያ ልጅ፥ የፋ​ስ​ኩር ልጅ፥ የዘ​ካ​ር​ያስ ልጅ፥ የአ​ማሴ ልጅ፥ የፈ​ላ​ልያ ልጅ፥ የይ​ሮ​ሖም ልጅ ዓዳያ፥


የኢ​ዮ​ስ​ያ​ስም ልጆች፤ በኵሩ ዮሐ​ናን፥ ሁለ​ተ​ኛ​ውም ኢዮ​አ​ቄም፥ ሦስ​ተ​ኛ​ውም ሴዴ​ቅ​ያስ፥ አራ​ተ​ኛ​ውም ሰሎም።


ስለ​ዚ​ህም የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንን ንጉሥ አመ​ጣ​ባ​ቸው፤ እር​ሱም ጐል​ማ​ሶ​ቻ​ቸ​ውን በቤተ መቅ​ደሱ ውስጥ በሰ​ይፍ ገደ​ላ​ቸው፤ለን​ጉ​ሣ​ቸው ለሴ​ዴ​ቅ​ያ​ስም አል​ራ​ራ​ለ​ትም፤ ደና​ግ​ሉ​ንም አል​ማ​ረም፤ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ወሰ​ዳ​ቸው፤ ሁሉ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእጁ አሳ​ልፎ ሰጠው።


ካህ​ኑም ሶፎ​ን​ያስ ይህን ደብ​ዳቤ በነ​ቢዩ በኤ​ር​ም​ያስ ጆሮ አነ​በ​በው።


የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ከእኔ ትጠ​ይቁ ዘንድ የላ​ካ​ች​ሁን የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ እን​ዲህ በሉት፦ እነሆ ሊረ​ዳ​ችሁ የወ​ጣው የፈ​ር​ዖን ሠራ​ዊት ወደ ሀገሩ ወደ ግብፅ ይመ​ለ​ሳል።


ንጉ​ሡም ሴዴ​ቅ​ያስ ልኮ አስ​መ​ጣው፥ ንጉ​ሡም በቤቱ፥ “በውኑ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የሆነ ቃል አለን?” ብሎ በቈ​ይታ ጠየ​ቀው። ኤር​ም​ያ​ስም፥ “አዎን አለ፤ ደግ​ሞም በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ እጅ አል​ፈህ ትሰ​ጣ​ለህ” አለው።


ንጉ​ሡም ሴዴ​ቅ​ያስ ልኮ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወደ ነበ​ረው ወደ ሦስ​ተ​ኛው መግ​ቢያ ወደ እርሱ ነቢ​ዩን ኤር​ም​ያ​ስን አስ​መ​ጣው፤ ንጉ​ሡም ኤር​ም​ያ​ስን፥ “አን​ዲት ነገር እጠ​ይ​ቅ​ሃ​ለሁ፤ ምንም አት​ሸ​ሽ​ገኝ” አለው።


“አባ​ቶ​ቻ​ችን በእ​ር​ስዋ የተ​ጻ​ፈ​ውን ሁሉ ይሠሩ ዘንድ የዚ​ህ​ችን መጽ​ሐፍ ቃል ስላ​ል​ሰሙ በላ​ያ​ችን የነ​ደደ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ እጅግ ነውና ሄዳ​ችሁ ስለ እኔና ስለ ሕዝቡ ስለ ይሁ​ዳም ሁሉ ስለ​ዚ​ችም ስለ​ተ​ገ​ኘ​ችው መጽ​ሐፍ ቃል ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠይቁ።


ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት በበ​ረ​ኛው በሰ​ሎም ልጅ በማ​ሴው ጓዳ በላይ ባለው በአ​ለ​ቆቹ ጓዳ አጠ​ገብ ወደ አለው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ወደ ጎዶ​ልያ ልጅ ወደ ሐና​ንያ ልጆች ጓዳ አገ​ባ​ኋ​ቸው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements