Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 2:37 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

37 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተስ​ፋ​ሽን አስ​ቈ​ር​ጦ​ሻ​ልና፥ በእ​ር​ሱም አይ​ከ​ና​ወ​ን​ል​ሽ​ምና እጅ​ሽን በራ​ስሽ ላይ አድ​ር​ገሽ ከዚያ ደግሞ ትወ​ጫ​ለሽ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

37 የታመንሽባቸውን እግዚአብሔር ስላዋረደ፣ በእነርሱም ስለማይከናወንልሽ፣ እጆችሽን በራስሽ ላይ አድርገሽ ከዚያም ትወጫለሽ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

37 ከዚያ ደግሞ እጆችሽን በራስሽ ላይ አድርገሽ ትወጫለሽ፥ ምክንያቱም ጌታ የታመንሽባቸውን ጥሎአልና፥ በእነርሱም አይከናወንልሽም።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

37 እጅሽን በራስሽ ላይ አድርገሽ በዕፍረት ከዚያ ቦታ ትሄጂአለሽ፤ እኔ እግዚአብሔር አንቺ የምትታመኝባቸውን ሁሉ ስላስወገድኩ ከእነርሱ የምታገኚው ምንም ነገር አይኖርም።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

37 እግዚአብሔር የታመንሽባቸውን ጥሎአልና፥ በእነርሱም አይከናወንልሽምና እጅሽን በራስሽ ላይ አድርገሽ ከዚያ ደግሞ ትወጫለሽ።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 2:37
16 Cross References  

ትዕ​ማ​ርም አመድ ወስዳ በራ​ስዋ ላይ ነሰ​ነ​ሰች፤ በላ​ይዋ የነ​በ​ረ​ው​ንም ብዙ ኅብር ያለ​ውን ልብ​ስ​ዋን ቀደ​ደ​ችው፤ እጅ​ዋ​ንም በራ​ስዋ ላይ ጭና እየ​ጮ​ኸች ሄደች።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በሰው የሚ​ታ​መን የሥጋ ክን​ዱ​ንም በእ​ርሱ የሚ​ያ​ስ​ደ​ግፍ፥ ልቡም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ርቅ ሰው ርጉም ነው።


ሴዴ​ቅ​ያ​ስም ወደ ባቢ​ሎን ይገ​ባል፤ እኔም እስ​ክ​ጐ​በ​ኘው ድረስ በዚያ ይኖ​ራል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያን ጋር ብቷጉ ምንም አይ​ቀ​ና​ች​ሁም።”


መን​ገ​ድ​ሽን እጥፍ ታደ​ርጊ ዘንድ ለምን እጅግ ትሮ​ጫ​ለሽ? በአ​ሦር እን​ዳ​ፈ​ርሽ በግ​ብ​ፅም ታፍ​ሪ​ያ​ለሽ።


በሐ​ሣር እን​ዳ​ት​ወ​ድቁ፥ ክብ​ራ​ች​ሁን ወዴት ትተ​ዉ​ታ​ላ​ችሁ? በዚ​ህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም፤ ነገር ግን እጁ ገና ተዘ​ር​ግታ ትኖ​ራ​ለች።


እነ​ሆም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእኛ ላይ አለቃ ነው፤ መለ​ከ​ቱ​ንም የሚ​ነፉ ካህ​ናቱ ከእኛ ጋር ናቸው፤ በእ​ና​ን​ተም ላይ ይጮ​ኻሉ። የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሆይ፥ አይ​በ​ጃ​ች​ሁ​ምና ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ አም​ላክ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር አቷጉ።”


ሙሴም አለ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ለምን ትተ​ላ​ለ​ፋ​ላ​ችሁ? ይህ ለእ​ና​ንተ መል​ካም አይ​ደ​ለም።


ታላ​ላ​ቆ​ች​ዋም ብላ​ቴ​ኖ​ቻ​ቸ​ውን ወደ ውኃ ሰደዱ፤ ወደ ጕድ​ጓድ መጡ፤ ውኃም አላ​ገ​ኙም፤ ዕቃ​ቸ​ው​ንም ባዶ​ውን መለሱ፤ ዐፈ​ሩም፤ ተዋ​ረ​ዱም፤ ራሳ​ቸ​ው​ንም ተከ​ና​ነቡ።


በም​ድር ላይ አል​ዘ​ነ​በ​ምና መሬቱ ስን​ጥ​ቅ​ጥቅ ስለ ሆነ አራ​ሾች ዐፈሩ፤ ራሳ​ቸ​ው​ንም ተከ​ና​ነቡ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በዘ​መኑ አይ​ከ​ና​ወ​ን​ምና፥ ከዘ​ሩም በዳ​ዊት ዙፋን የሚ​ቀ​መጥ አይ​ነ​ሣ​ምና፥ እን​ግ​ዲህ ወዲ​ህም ለይ​ሁዳ ገዢ አይ​ሾ​ም​ምና ይህን ሰው እንደ ሞተ ቍጠ​ሪው” አለ።


ዳዊ​ትም ኦር​ዮን፥ “ዛሬ ደግሞ በዚህ ተቀ​መጥ፤ ነገም አሰ​ና​ብ​ት​ሃ​ለሁ” አለው። ኦር​ዮም በዚያ ቀንና በነ​ጋው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተቀ​መጠ።


ከሞ​ትም ጋር ያደ​ረ​ጋ​ች​ሁት ቃል ኪዳን ይፈ​ር​ሳል፤ ከኢ​ኦ​ልም ጋር የተ​ማ​ማ​ላ​ች​ሁት መሐላ አይ​ጸ​ናም፤ የሚ​ያ​ልፍ ዐውሎ ነፋስ በመጣ ጊዜ ይረ​ግ​ጣ​ች​ኋል፤ ትደ​ክ​ማ​ላ​ች​ሁም።


ወዳ​ጆ​ችሽ ሁሉ ጠፍ​ተ​ዋ​ልና ወደ ሊባ​ኖስ ወጥ​ተሽ ጩኺ፤ በባ​ሳ​ንም ላይ ድም​ፅ​ሽን አንሺ፤ በባ​ሕ​ሩም ማዶ ጩኺ።


ፌ። በማ​ያ​ድን ወገን እያ​መ​ንን ረዳ​ታ​ችን ከንቱ ስለ ሆነ፥ እኛ ገና በሕ​ይ​ወት ሳለን ዐይ​ኖ​ቻ​ችን ጠፉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements