ኤርምያስ 2:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)28 ለአንተ የሠራሃቸው አማልክትህ ግን ወዴት ናቸው? ይሁዳ ሆይ፥ አማልክትህ እንደ ከተሞችህ ቍጥር እንዲሁ ናቸውና ይነሡ፤ በመከራህም ጊዜ ያድኑህ። በኢየሩሳሌምም በመንገዶችዋ ቍጥር ለጣዖት ሠዉ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም28 ታዲያ፣ ልታመልካቸው ያበጀሃቸው አማልክት ወዴት ናቸው? በመከራህ ጊዜ ሊያድኑህ የሚችሉ ከሆነ፣ ይሁዳ ሆይ፤ እስኪ ይምጡና ያድኑህ፤ የከተሞችህን ቍጥር ያህል፣ የአማልክትህም ብዛት እንዲሁ ነውና። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)28 ለራስህ የሠራሃቸው አማልክትህ ወዴት ናቸው? ይሁዳ ሆይ! አማልክትህ እንደ ከተሞችህ ቍጥር ብዛት እንዲሁ ናቸውና እስቲ ይነሡ በመከራህም ጊዜ ያድኑህ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም28 “በእጃችሁ የሠራችኋቸው አማልክት እስቲ የት አሉ? የሚችሉ ከሆነ መከራ ሲደርስባችሁ ተነሥተው ያድኑአችሁ፤ ይሁዳ ሆይ! ከተሞችህ ብዙዎች በሆኑ መጠን አማልክትህም በዝተዋል።” See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)28 ለአንተ የሠራሃቸው አማልክትህ ወዴት ናቸው? ይሁዳ ሆይ፥ አማልክትህ እንደ ከተሞችህ ቍጥር እንዲሁ ናቸውና ይነሡ በመከራህም ጊዜ ያድኑህ። See the chapter |