ኤርምያስ 2:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)25 እግርሽን ከሰንከልካላ መንገድ፥ ጕሮሮሽንም ከውኃ ጥም ከልክዪ፤ እርስዋ ግን፥ “እጨክናለሁ፤ እንግዶችንም ወድጄአለሁ” ብላ ተከተለቻቸው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም25 እግርሽ እስኪነቃ አትሩጪ፤ ጕረሮሽም በውሃ ጥም እስኪደርቅ አትቅበዝበዢ። አንቺ ግን፣ ‘በከንቱ አትድከም፤ ባዕዳን አማልክትን ወድጃለሁ፤ እነርሱን እከተላለሁ’ አልሽ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)25 በባዶ እግርሽ ከመሄድ፥ ጉሮሮሽንም ከውኃ ጥም ከልክዪ፤ አንቺ ግን፦ ‘ተስፋ የለኝም፥ አይሆንም! እንግዶችን ወድጄአለሁና፥ እከተላቸዋለሁም’ አልሽ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም25 እስራኤል ሆይ! ከሌሎች አማልክት ጋር ለማመንዘር በየስፍራው በመዞር ጫማሽን አትጨርሺ፤ ጉሮሮሽም በውሃ ጥም አይድረቅ፤ አንቺ ግን ‘እኔ ባዕዳን አማልክትን ስለ ወደድኩና እነርሱን ለመከተል ስለ ቈረጥኩ ወደ ኋላ አልመለስም!’ ” ብለሻል። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)25 እግርሽን ከሸካራ መንገድ ጕሮሮሽንም ከውኃ ጥም ከልክዪ፥ አንቺ ግን፦ እጨክናለሁ፥ እንግዶችን ወድጄአለሁና፥ እከተላቸዋለሁም አልሽ። See the chapter |