Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 18:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ለሰ​ው​ነቴ ጕድ​ጓ​ድን ቈፍ​ረ​ዋል፤ በውኑ በመ​ል​ካም ፈንታ ክፉ ይመ​ለ​ሳ​ልን? ስለ እነ​ርሱ በመ​ል​ካም እና​ገር ዘንድ፥ ቍጣ​ህ​ንም ከእ​ነ​ርሱ ትመ​ልስ ዘንድ በፊ​ትህ እንደ ቆምሁ አስብ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 የመልካም ተግባር ወሮታው ክፉ ነውን? እነርሱ ግን ጕድጓድ ቈፈሩልኝ፤ ቍጣህን ከእነርሱ እንድትመልስ፣ በፊትህ ቆሜ፣ ስለ እነርሱ እንደ ተናገርሁ ዐስብ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ለነፍሴ ጉድጓድ ቈፍረዋልና በውኑ በመልካም ፋንታ ክፉ ይመለሳልን? ስለ እነርሱ በመልካም ለመናገር ቁጣህንም ከእነርሱ ለመመለስ በፊትህ እንደ ቆምሁ አስታውስ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ታዲያ የደግ ሥራ ዋጋው ክፉ ነገር ማድረግ ነውን? አንተ በእነርሱ ላይ እንዳትቈጣ እኔ በፊትህ ቆሜ ስለ እነርሱ እንደማለድኩህ አስብ፤ እነርሱ ግን እነሆ እኔ የምወድቅበትን ጒድጓድ ቈፈሩ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ለነፍሴ ጕድጓድ ቈፍረዋልና በውኑ በመልካም ፋንታ ክፉ ይመለሳልን? ስለ እነርሱ በመልካም እናገር ዘንድ ቍጣህንም ከእነርሱ እመልስ ዘንድ በፊትህ እንደ ቆምሁ አስብ።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 18:20
31 Cross References  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥር​ሳ​ቸ​ውን በአ​ፋ​ቸው ውስጥ ይሰ​ብ​ራል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ን​በ​ሶ​ቹን መን​ጋ​ጋ​ቸ​ውን ያደ​ቅ​ቃል።


አቤቱ፥ ሰው​ንና እን​ስ​ሳን ታድ​ና​ለህ። አቤቱ፥ ምሕ​ረ​ት​ህን እንደ አበ​ዛህ፥ የሰው ልጆች በክ​ን​ፎ​ችህ ጥላ ይታ​መ​ናሉ።


በመ​ር​ከ​ቦች ወደ ባሕር የሚ​ወ​ርዱ፥ በብዙ ውኃ ሥራ​ቸ​ውን የሚ​ሠሩ፥


ዐመ​ፃን የሚ​ያ​ደ​ርጉ ሁሉ በዚያ ይወ​ድ​ቃሉ፤ ይሰ​ደ​ዳሉ፥ መቆ​ምም አይ​ች​ሉም።


ሊይ​ዙኝ ጕድ​ጓድ ቈፍ​ረ​ዋ​ልና፥ ለእ​ግ​ሮ​ችም ወጥ​መድ ሸሽ​ገ​ዋ​ልና፥ በቤ​ታ​ቸው ጩኸት ይሰማ፤ ድን​ገ​ትም በላ​ያ​ቸው ወን​በ​ዴን አም​ጣ​ባ​ቸው።


ለባ​ል​ን​ጀ​ራው ጕድ​ጓ​ድን የሚ​ምስ ይወ​ድ​ቅ​በ​ታል፥ ቅጥ​ር​ንም የሚ​ያ​ፈ​ር​ስን እባብ ትነ​ድ​ፈ​ዋ​ለች።


ነገር ግን በኦ​ሪ​ታ​ቸው፦ በከ​ንቱ ጠሉኝ ተብሎ የተ​ጻ​ፈው ቃል ይፈ​ጸም ዘንድ ነው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ከአ​ባቴ ብዙ መል​ካም ሥራ አሳ​የ​ኋ​ችሁ፤ ከእ​ነ​ርሱ በየ​ት​ኛው ሥራ ምክ​ን​ያት ትወ​ግ​ሩ​ኛ​ላ​ችሁ?”


አቤቱ በአ​ንተ ላይ ኀጢ​አ​ትን ሠር​ተ​ና​ልና ክፋ​ታ​ች​ን​ንና የአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ንን በደል እና​ው​ቃ​ለን።


አን​ተም ስለ​ዚህ ሕዝብ አት​ጸ​ልይ፤ በመ​ከ​ራ​ቸው ቀን ወደ እኔ በጮኹ ጊዜ አል​ሰ​ማ​ቸ​ው​ምና ስለ እነ​ርሱ አት​ጸ​ልይ፤ በም​ል​ጃና በጸ​ሎት አት​ማ​ልድ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፥ “ስለ​ዚህ ሕዝብ አንተ አት​ጸ​ልይ፤ ይቅር እላ​ቸው ዘንድ አት​ማ​ል​ደኝ፤ የእ​ነ​ር​ሱን ነገር አል​ሰ​ማ​ህ​ምና ትለ​ም​ን​ላ​ቸው ዘንድ ወደ እኔ አት​ምጣ።”


በመልካም ፋንታ ክፉን የሚመልስ፥ ክፉ ነገር ከቤቱ አይርቅም።


ጕድ​ጓ​ድ​ንም ማሰ፥ ቈፈ​ረም። ባደ​ረ​ገ​ውም ጕድ​ጓድ ይወ​ድ​ቃል።


በድሃ አደጉ ላይ ትስ​ቃ​ላ​ች​ሁና፥ ወዳ​ጃ​ች​ሁ​ንም ትሰ​ድ​ባ​ላ​ች​ሁና።


ዮና​ታ​ንም ለአ​ባቱ ለሳ​ኦል ስለ ዳዊት መል​ካም ተና​ገረ እን​ዲ​ህም አለው፥ “እርሱ አል​በ​ደ​ለ​ህ​ምና፥ ሥራ​ውም ለአ​ንተ እጅግ መል​ካም ሆኖ​አ​ልና ንጉሡ ባሪ​ያ​ውን ዳዊ​ትን አይ​በ​ድ​ለው፤


በሕ​ዝቤ መካ​ከል ክፉ​ዎች ሰዎች ተገ​ኝ​ተ​ዋል፤ ሰዎ​ች​ንም ይዘው ይገ​ድሉ ዘንድ ወጥ​መ​ድን ይዘ​ረ​ጋሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለኝ፥ “ሙሴና ሳሙ​ኤል በፊቴ ቢቆ​ሙም፥ ልቤ ወደ​ዚህ ሕዝብ አያ​ዘ​ነ​ብ​ልም፤ እነ​ዚ​ህን ሕዝ​ቦች ከፊቴ አባ​ር​ራ​ቸው፤ ይውጡ።


“አቤቱ! አድ​ም​ጠኝ፤ የክ​ር​ክ​ሬ​ንም ቃል ስማ።


እነ​ርሱ ግን ነቢ​ያት ቢሆኑ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል በእ​ነ​ርሱ ዘንድ ቢገኝ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤትና በይ​ሁዳ ንጉሥ ቤት፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የቀ​ሩት ዕቃ​ዎች ወደ ባቢ​ሎን እን​ዳ​ይ​ሄዱ ወደ ሠራ​ዊት ጌታ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይማ​ለሉ።”


አቤቱ፥ ጭን​ቀ​ቴን አይ​ተ​ሃል፤ ፍር​ዴን ፍረ​ድ​ልኝ።


አሳ​ዳ​ጆች ይፈሩ፤ እኔ ግን አል​ፈር፤ እነ​ርሱ ይደ​ን​ግጡ፤ እኔ ግን አል​ደ​ን​ግጥ፤ ክፉ​ንም ቀን አም​ጣ​ባ​ቸው፤ በሁ​ለት እጥፍ ጥፋት ቀጥ​ቅ​ጣ​ቸው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements