Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 17:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይለ​ኛል፥ “ሂድ፤ የይ​ሁ​ዳም ነገ​ሥ​ታት በሚ​ገ​ቡ​በ​ትና በሚ​ወ​ጡ​በት በሕ​ዝ​ብህ ልጆች በር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም በሮች ሁሉ ቁም።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤ “ሄደህ የይሁዳ ነገሥታት በሚገቡበትና በሚወጡበት በሕዝቡ በር በሌሎቹም የኢየሩሳሌም በሮች ሁሉ ቁም፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ጌታ እንዲህ ይለኛል፦ “ሂድ፥ የይሁዳም ነገሥታት በሚገቡበትና በሚወጡበት በሕዝቡ ልጆች በር፥ በኢየሩሳሌምም በሮች ሁሉ ቁም፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “የይሁዳ ንጉሥ ከከተማይቱ በሚወጣበትና በሚገባበት ወደ ሕዝቡ ቅጽር በር እንዲሁም በኢየሩሳሌም ወደሚገኙት ወደ ሌሎቹም ቅጽር በሮች ሄደህ ቁም፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 እግዚአብሔር እንዲህ ይለኛል፦ ሂድ፥ የይሁዳም ነገሥታት በሚገቡበትና በሚወጡበት በሕዝቡ ልጆች በር በኢየሩሳሌምም በሮች ሁሉ ቁም፥

See the chapter Copy




ኤርምያስ 17:19
11 Cross References  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አደ​ባ​ባይ ቁም፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ውስጥ ይሰ​ግዱ ዘንድ ለሚ​መ​ጡት ለይ​ሁዳ ከተ​ሞች ሁሉ ትነ​ግ​ራ​ቸው ዘንድ ያዘ​ዝ​ሁ​ህን ቃል ሁሉ ተና​ገ​ራ​ቸው፤ አን​ዲ​ትም ቃል አታ​ጕ​ድል።


“በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በር ቁም፤ ይህ​ንም ቃል እን​ዲህ ብለህ ተና​ገር፦ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትሰ​ግዱ ዘንድ በእ​ነ​ዚህ በሮች የም​ት​ገቡ ከይ​ሁዳ ያላ​ችሁ ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።


“ሂዱ፤ ወደ ቤተ መቅ​ደ​ስም ግቡና ለሕ​ዝብ ይህን የሕ​ይ​ወት ቃል አስ​ተ​ም​ሩ​አ​ቸው።”


ባሮ​ክም የኤ​ር​ም​ያ​ስን ቃል በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በላ​ይ​ኛው አደ​ባ​ባይ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በአ​ዲሱ በር መግ​ቢያ ባለው በጸ​ሓ​ፊው በሳ​ፋን ልጅ በገ​ማ​ርያ ክፍል በሕ​ዝቡ ሁሉ ጆሮ በመ​ጽ​ሐፉ አን​በበ።


አንተ ግን ገብ​ተህ ከአፌ የጻ​ፍ​ኸ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል በጾም ቀን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በሕ​ዝቡ ጆሮ በክ​ር​ታሱ አን​ብብ፤ ደግ​ሞም ከከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው በሚ​ወጡ በይ​ሁዳ ሰዎች ሁሉ ጆሮ አን​ብ​በው።


በከ​ር​ሲት በር መግ​ቢያ አጠ​ገብ ወዳ​ለው ወደ ሄኖም ልጅ ሸለቆ ሂድ፥ በዚ​ያም የም​ነ​ግ​ር​ህን ቃል አን​ብብ፤ እን​ዲ​ህም በል፦


አገልጋዮችዋን ልካ በከፍተኛ ዐዋጅ ወደ ማዕድዋ ጠራች። እንዲህም አለች፦


አንተስ ጥበብን አስተምር፥ ማስተዋል ትመልስልህ ዘንድ፤


አሳ​ዳ​ጆች ይፈሩ፤ እኔ ግን አል​ፈር፤ እነ​ርሱ ይደ​ን​ግጡ፤ እኔ ግን አል​ደ​ን​ግጥ፤ ክፉ​ንም ቀን አም​ጣ​ባ​ቸው፤ በሁ​ለት እጥፍ ጥፋት ቀጥ​ቅ​ጣ​ቸው።


እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፥ “በእ​ነ​ዚህ በሮች የም​ት​ገቡ እና​ንተ የይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት፥ ይሁ​ዳም ሁሉ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የም​ት​ኖሩ ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements