ኤርምያስ 16:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 ስለዚህም የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ በዐይናችሁ ፊት በዘመናችሁም የእልልታን ድምፅና የደስታን ድምፅ፥ የወንድ ሙሽራን ድምፅና የሴት ሙሽራን ድምፅ ከዚህ ስፍራ አስቀራለሁ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ ‘እነሆ፤ በዐይናችሁ ፊት፣ በዘመናችሁም የደስታና የሐሤት ድምፅ፣ የሙሽራውንና የሙሽራዪቱን ድምፅ ከዚህ ስፍራ አስወግዳለሁ።’ See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላልና፦ እነሆ፥ በዓይናችሁ ፊት በዘመናችሁም፥ የእልልታን ድምፅና የደስታን ድምፅ፥ የሙሽራውን ድምፅና የሙሽራቱይን ድምፅ ከዚህ ስፍራ አስቀራለሁ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 እኔ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ የምልህን አድምጥ፥ አንተ ባለህበት በዚህ ዘመን የደስታና የሐሤት፥ የሠርግ ዘፈን ድምፅ እንዳይሰማ አደርጋለሁ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ እነሆ፥ በዓይናችሁ ፊት በዘመናችሁም የእልልታን ድምፅና የደስታን ድምፅ የወንድ ሙሽራን ድምፅና የሴት ሙሽራን ድምፅ ከዚህ ስፍራ አስቀራለሁ። See the chapter |