Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 16:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 “ለዚ​ህም ሕዝብ ይህን ቃል ሁሉ በተ​ና​ገ​ርህ ጊዜ፦ ይህን ሁሉ ትልቅ የሆነ ክፉ ነገ​ርን ስለ ምን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ገ​ረ​ብን? በደ​ላ​ች​ንስ ምን​ድን ነው? በአ​ም​ላ​ካ​ች​ንስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያደ​ረ​ግ​ነው ኀጢ​አት ምን​ድን ነው? ቢሉህ፥

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 “ይህን ሁሉ ለዚህ ሕዝብ በምትነግርበት ጊዜ ሰዎቹ፣ ‘እግዚአብሔር ይህን ሁሉ ታላቅ ጥፋት በእኛ ላይ ለምን ዐወጀ? በደላችንስ ምንድን ነው? በአምላካችንስ በእግዚአብሔር ላይ የሠራነው ኀጢአት ምንድን ነው?’ ብለው ቢጠይቁህ፣

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 “ለዚህም ሕዝብ ይህን ቃላት ሁሉ በተናገርህ ጊዜ፦ ‘ይህን ሁሉ ታላቅ የሆነ ክፉ ነገርን ለምን ጌታ ተናገረብን? በደላችንስ ምንድነው? በአምላካችንስ በጌታ ላይ የሠራነው ኃጢአታችን ምንድነው?’ ቢሉህ፥

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 “ይህን ሁሉ በምትነግራቸው ጊዜ ‘እግዚአብሔር በእኛ ላይ ይህን የሚያኽል ከባድ ጥፋት ለምን ወሰነብን? ምን በደልን? በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊትስ የሠራነው ኃጢአት ምንድን ነው?’ ብለው ይጠይቁሃል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ለዚህም ሕዝብ ይህን ቃል ሁሉ በተናገርህ ጊዜ፦ ይህን ሁሉ ታላቅ የሆነ ክፉ ነገርን ስለ ምን እግዚአብሔር ተናገረብን? በደላችንስ ምንድር ነው? በአምላካችንስ በእግዚአብሔር ላይ የሠራነው ኃጢአታችን ምንድር ነው? ቢሉህ፥

See the chapter Copy




ኤርምያስ 16:10
11 Cross References  

እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ እና​ንተ፥ “አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ነገር ሁሉ ስለ ምን አደ​ረ​ገ​ብን?” ብትሉ፥ አንተ፥ “እንደ ተዋ​ች​ሁኝ፥ በሀ​ገ​ራ​ች​ሁም ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት እን​ዳ​መ​ለ​ካ​ችሁ፥ እን​ዲሁ ለእ​ና​ንተ ባል​ሆነ ሀገር ለሌ​ሎች ሰዎች ትገ​ዛ​ላ​ችሁ” ትላ​ቸ​ዋ​ለህ።


በል​ብ​ሽም፦ እን​ዲህ ያለ ነገር ስለ ምን ደረ​ሰ​ብኝ? ብትዪ፥ ከኀ​ጢ​አ​ትሽ ብዛት የተ​ነሣ ልብ​ስሽ በስ​ተ​ኋ​ላሽ ተገ​ፎ​አል፤ ተረ​ከ​ዝ​ሽም ተገ​ል​ጦ​አል።


በከ​ነ​ዓን እጅ የዐ​መፅ ሚዛን አለ፤ ቅሚ​ያ​ንም ይወ​ድ​ዳል።


አንቺ ግን፦ ንጹሕ ነኝ፤ በእ​ው​ነት ቍጣው ከእኔ ይመ​ለስ አልሽ። እነሆ ኀጢ​አት አል​ሠ​ራ​ሁም ብለ​ሻ​ልና እፋ​ረ​ድ​ሻ​ለሁ።


ለበ​ዓ​ልም በማ​ጠ​ና​ቸው ያስ​ቈ​ጡኝ ዘንድ ለራ​ሳ​ቸው ስለ ሠሩ​አት ስለ እስ​ራ​ኤ​ልና ስለ ይሁዳ ቤት ክፋት የተ​ከ​ለሽ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክፉን ነገር ተና​ግ​ሮ​ብ​ሻል።


አን​ቺስ፦ አል​ረ​ከ​ስ​ሁም፤ በዓ​ሊ​ም​ንም አል​ተ​ከ​ተ​ል​ሁም፤ እን​ዴት ትያ​ለሽ? በሸ​ለቆ ያለ​ውን መን​ገ​ድ​ሽን ተመ​ል​ከቺ፤ ያደ​ረ​ግ​ሽ​ው​ንም ዕወቂ። ማታ ማታ በመ​ን​ገ​ዶች ትጮ​ኻ​ለች፤


ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም የፍ​ር​ስ​ራሽ ክምር፥ የቀ​በ​ሮም ማደ​ሪያ አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ፤ የይ​ሁ​ዳ​ንም ከተ​ሞች ሰው እን​ዳ​ይ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ቸው አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ይህም የሆ​ነው ያስ​ቈ​ጡኝ ዘንድ ስላ​ደ​ረ​ጉት ክፋት፥ እነ​ር​ሱና አባ​ቶ​ቻ​ቸው ለማ​ያ​ው​ቁ​አ​ቸው ለሌ​ሎች አማ​ል​ክት ያጥኑ ዘንድ፥ ያመ​ል​ኳ​ቸ​ውም ዘንድ ስለ​ሄዱ ነው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements