Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 15:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 በዋ​ዘ​ኞች ጉባኤ አል​ተ​ቀ​መ​ጥ​ሁም፤ ነገር ግን በእ​ጅህ ፊት ፈር​ቻ​ለሁ፤ ምሬ​ትን ሞል​ተ​ህ​ብ​ኛ​ልና ለብ​ቻዬ ተቀ​መ​ጥሁ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ፈንጠዝያ ከሚያደርጉት ጋራ አልተቀመጥሁም፤ ከእነርሱም ጋራ አልፈነጨሁም፤ እጅህ በላዬ ስለ ነበር፣ በቍጣህ ስለ ሞላኸኝ፣ ለብቻዬ ተቀመጥሁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 በዋዘኞች ጉባኤ አልተቀመጥኩም አልተደሰትኩምም፤ ቁጣን ሞልተህብኛልና እጅህ በእኔ ላይ ስለ ሆነ ለብቻዬ ተቀመጥሁ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ከሚፈነጥዙ ሰዎች ጋር አልተወዳጀሁም፤ ከእነርሱም ጋር አልተደሰትኩም፤ ቊጣህ በእኔ ላይ ስለ ሆነ ብቻዬን ተቀመጥኩ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 በዋዘኞችና በደስተኞች ጉባኤ አልተቀመጥሁም፥ ቍጣን ሞልተህብኛልና በእጅህ ፊት ለብቻዬ ተቀመጥሁ።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 15:17
13 Cross References  

ዮድ። እርሱ አሸ​ክ​ሞ​ታ​ልና ዝም ብሎ ለብ​ቻው ይቀ​መጥ።


ምስ​ጉን ነው፥ በዝ​ን​ጉ​ዎች ምክር ያል​ሄደ፥ በኀ​ጢ​አ​ተ​ኞ​ችም መን​ገድ ያል​ቆመ፥ በዋ​ዘ​ኞ​ችም ወን​በር ያል​ተ​ቀ​መጠ ሰው።


ስለ​ዚ​ህም “ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ተለ​ይ​ታ​ችሁ ውጡ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ተለዩ፤ ወደ ርኩ​ሳ​ንም አት​ቅ​ረቡ፥ እኔም እቀ​በ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።


ይህን ባት​ሰሙ ነፍሴ ስለ ትዕ​ቢ​ታ​ችሁ በስ​ውር ታለ​ቅ​ሳ​ለች፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መንጋ ተሰ​ብ​ሮ​አ​ልና ዐይኔ ታነ​ባ​ለች፤ እን​ባ​ንም ታፈ​ስ​ሳ​ለች።


ስለ​ዚህ ቍጣ​ዬን መላ​ሁ​ባ​ቸው፤ ታገ​ሥሁ፤ ፈጽ​ሜም አላ​ጠ​ፋ​ኋ​ቸ​ውም፤ በሜዳ በሕ​ፃ​ናት ላይ በጐ​ል​ማ​ሶ​ችም ጉባኤ ላይ መዓ​ቴን በአ​ን​ድ​ነት አፈ​ስ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ባል ከሚ​ስቱ ጋር ሽማ​ግ​ሌ​ውም ከጎ​በዙ ጋር ይያ​ያ​ዛ​ልና።


ለሙሴ መን​ገ​ዱን አሳየ፥ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችም ፈቃ​ዱን።


ትበ​ላና ትጠጣ ዘንድ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ለመ​ቀ​መጥ ወደ ግብዣ ቤት አት​ግባ።”


እነሆ ትነ​ቅ​ልና ታፈ​ርስ ዘንድ፥ ታጠ​ፋና ትገ​ለ​ብጥ ዘንድ፥ ትሠ​ራና ትተ​ክል ዘንድ በአ​ሕ​ዛ​ብና በመ​ን​ግ​ሥ​ታት ላይ ዛሬ ሾሜ​ሃ​ለሁ።”


የእግዚአብሔርም መልአክ መልሶ፦ አቤቱ፥ የሠራዊት ጌታ ሆይ፥ እነዚህ ሰባ ዓመት የተቈጣሃቸውን ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች የማትምራቸው እስከ መቼ ነው? አለ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements