Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 13:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ! ዐይ​ን​ሽን አን​ሥ​ተሽ እነ​ዚ​ህን ከሰ​ሜን የሚ​መ​ጡ​ትን ተመ​ል​ከቺ፤ ለአ​ንቺ የሰ​ጠ​ሁሽ መንጋ፤ የክ​ብር በጎ​ችሽ ወዴት አሉ?

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ዐይኖቻችሁን ከፍታችሁ፣ ከሰሜን የሚመጡትን እዩ። ለአንቺ የተሰጠው መንጋ፣ የተመካሽባቸው በጎች የት አሉ?

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 “ዓይናችሁን አንሥታችሁ እነዚህን ከሰሜን የሚመጡትን ተመልከቱ፤ ለአንቺ የተሰጠ መንጋ፥ የተዋበ መንጋሽ፥ ወዴት አለ?

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ኢየሩሳሌም ሆይ! ከሰሜን በኩል የጠላቶችሽን አመጣጥ ተመልከቺ፤ ስትንከባከቢያቸው የነበርሽና መመኪያዎችሽ የነበሩ ሕዝብ የት ደረሱ?

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ዓይናችሁን አንሥታችሁ እነዚህን ከሰሜን የሚመጡትን ተመልከቱ፥ ለአንቺ የተሰጠ መንጋ፥ የተዋበ መንጋሽ፥ ወዴት አለ?

See the chapter Copy




ኤርምያስ 13:20
14 Cross References  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ ሕዝብ ከሰ​ሜን ሀገር ይመ​ጣል፤ ታላቅ ሕዝ​ብም ከም​ድር ዳርቻ ይነ​ሣል።


እነሆ፥ የእነርሱ ያልሆነውን መኖሪያ ይወርሱ ዘንድ በምድር ስፋት ላይ የሚሄዱትን መራሮችንና ፈጣኖችን ሕዝብ ከለዳውያንን አስነሣለሁ።


ስለ​ዚህ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቤን ስለ​ሚ​ጠ​ብቁ እረ​ኞች እን​ዲህ ይላል፥ “በጎ​ችን በት​ና​ች​ኋል፤ አባ​ር​ራ​ች​ኋ​ቸ​ው​ማል፥ አል​ጐ​በ​ኛ​ች​ኋ​ቸ​ው​ምም፤ እነሆ! እንደ ሥራ​ችሁ ክፋት እጐ​በ​ኛ​ች​ኋ​ለሁ፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለኝ፥ “ከሰ​ሜን ወገን ክፉ ነገር በም​ድ​ሪቱ በተ​ቀ​መጡ ሁሉ ላይ ይፈ​ስ​ሳል።


ይህን ባት​ሰሙ ነፍሴ ስለ ትዕ​ቢ​ታ​ችሁ በስ​ውር ታለ​ቅ​ሳ​ለች፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መንጋ ተሰ​ብ​ሮ​አ​ልና ዐይኔ ታነ​ባ​ለች፤ እን​ባ​ንም ታፈ​ስ​ሳ​ለች።


የወሬ ድምፅ ተሰማ፤ እነ​ሆም የይ​ሁ​ዳን ከተ​ሞች ባድ​ማና የሰ​ገኖ ማደ​ሪያ ያደ​ር​ጋ​ቸው ዘንድ ከሰ​ሜን ምድር ታላቅ መነ​ዋ​ወጥ መጥ​ቶ​አል።


እነሆ እኔ በሰ​ሜን ያሉ​ትን የመ​ን​ግ​ሥ​ታ​ቱን ወገ​ኖች ሁሉ እጠ​ራ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እነ​ር​ሱም ይመ​ጣሉ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸ​ውም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በር መግ​ቢያ በዙ​ሪ​ያ​ዋና በቅ​ጥ​ርዋ ሁሉ ላይ፥ በይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞች ሁሉ ላይ ዙፋ​ና​ቸ​ውን ያስ​ቀ​ም​ጣሉ።


ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽኑ ቍጣ የተ​ነሣ የሰ​ላም ውበት ፈር​ሶ​አል።


የንጉሥ ክብር በሕዝብ ብዛት ነው፤ የገዥ ውድቀት ግን በሕዝብ ማነስ ነው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements