Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 13:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ስለ​ዚህ፦ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ማድጋ ሁሉ የወ​ይን ጠጅ ይሞ​ላል” ብለህ ትነ​ግ​ራ​ቸ​ዋ​ለህ፤ እነ​ር​ሱም፥ “ማድጋ ሁሉ የወ​ይን ጠጅ እን​ዲ​ሞላ በውኑ እኛ አና​ው​ቅ​ምን?” ቢሉህ፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 “እንዲህ በላቸው፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ማድጋ ሁሉ በወይን ጠጅ ይሞላል’፤ እነርሱም፣ ‘ማድጋ ሁሉ በወይን ጠጅ እንደሚሞላ እኛ አናውቅምን?’ ቢሉህ፣

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ስለዚህ፦ የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ማድጋ ሁሉ የወይን ጠጅ ይሞላል” ብለህ ይህን ቃል ትነግራቸዋለህ፤ እነርሱም፦ “ማድጋ ሁሉ የወይን ጠጅ እንደሚሞላ በእርግጥ እኛ አናውቅምን?” ይሉሃል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እግዚአብሔር አምላክ እንዲህ አለኝ፦ “ኤርምያስ ሆይ! ‘እያንዳንዱ ማድጋ በወይን ጠጅ የተሞላ ይሆናል’ ብለህ ለእስራኤል ሕዝብ ንገር፤ በዚያን ጊዜ እነርሱ ‘ማድጋ በወይን ጠጅ መሞላቱን የማናውቅ ይመስልሃልን?’ ይሉሃል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ስለዚህ፦ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ማድጋ ሁሉ የወይን ጠጅ ይሞላል ብለህ ትነግራቸዋለህ፥ እነርሱም፦ ማድጋ ሁሉ የወይን ጠጅ እንዲሞላ በውኑ እኛ አናውቅምን? ይሉሃል።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 13:12
4 Cross References  

ሕዝ​ቡም፥ “ይህ የም​ታ​ደ​ር​ገው ነገር ለእኛ ምን እንደ ሆነ አት​ነ​ግ​ረ​ን​ምን?” አሉኝ።


መታ​ጠ​ቂያ በሰው ወገብ ላይ እን​ደ​ም​ት​ጣ​በቅ፥ እን​ዲሁ ለስም፥ ለመ​መ​ኪ​ያና ለክ​ብር ሕዝብ ይሆ​ኑ​ልኝ ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቤት ሁሉ፥ የይ​ሁ​ዳ​ንም ቤት ሁሉ ከእኔ ጋር አጣ​ብ​ቄ​አ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ነገር ግን አል​ሰ​ሙም።”


አን​ተም እን​ዲህ ትላ​ቸ​ዋ​ለህ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ በዚ​ህች ምድር የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሁሉ፥ በዳ​ዊት ዙፋን የሚ​ቀ​መ​ጡ​ትን ነገ​ሥ​ታት፥ ካህ​ና​ቱ​ንም፥ ነቢ​ያ​ቱ​ንም፥ በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን ሁሉ በስ​ካር እሞ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ከም​ሰ​ድ​ድ​ባ​ቸ​ውም ሰይፍ የተ​ነሣ ይጠ​ጣሉ፤ ይወ​ላ​ገ​ዳሉ፤ ያብ​ዳ​ሉም።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements