ኤርምያስ 12:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 እግሮችህ ሮጠው ይደክማሉ፤ ፈረሶችን ለምን ታስጌጣለህ? በሰላምም ምድር ላይ ለምን ትታመናለህ? በዮርዳኖስስ ጩኸት ለምን እንዲህ ታደርጋለህ? See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 “ከእግረኞች ጋራ ሮጠህ፣ እነርሱ ካደከሙህ፣ ከፈረሰኞች ጋራ እንዴት ልትወዳደር ትችላለህ? በሰላም አገር ከተሰናከልህ፣ በዮርዳኖስ ደን ውስጥ እንዴት ልትሆን ነው? See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 “ከእግረኞች ጋር በሮጥህ ጊዜ እነርሱ ቢያደክሙህ፥ ከፈረሶች ጋር መታገል እንዴት ትችላለህ? በሰላምም ምድር ተሰናክለህ ከወደቅህ፥ በዮርዳኖስ ዱር እንዴት ታደርጋለህ? See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ኤርምያስ ሆይ! በእግር ሩጫ ከሰዎች ጋር መወዳደር የሚያደክምህ ከሆነ፥ ከፈረስ ጋር መወዳደር እንዴት ትችላለህ? ግልጥ በሆነው ሜዳ ላይ ጸንተህ መቆም ካቃተህ፥ በዮርዳኖስ ደን ውስጥ መቆም እንዴት ትችላለህ? See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 ከእግረኞች ጋር በሮጥህ ጊዜ እነርሱ ቢያደክሙህ፥ ከፈረሶች ጋር መታገል እንዴት ትችላለህ? በሰላምም ምድር ታምነህ ብትቀመጥ፥ በዮርዳኖስ ትዕቢት እንዴት ታደርጋለህ? See the chapter |