ኤርምያስ 12:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 አንተ ግን አቤቱ! ዐውቀኸኛል፤ አይተኸኛል፤ ልቤንም በፊትህ ፈትነሃል፤ እንደ በጎች ለመታረድ ጐትተህ ለያቸው፤ ለመታረድም ቀን አዘጋጃቸው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 ነገር ግን እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ እኔን ታውቀኛለህ፤ ታየኛለህ፤ ስለ አንተም ያለኝን ሐሳብ ትመረምራለህ። እንደሚታረዱ በጎች ንዳቸው፤ ለዕርድም ቀን ለይተህ አቈያቸው፤ See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 አቤቱ! አንተ ግን፥ አውቀኸኛል፤ አይተኸኛል፥ ልቤንም ወደ አንተ መሆኑን ፈትነሃል፤ እንደ ሚታረድ በግ ጐትተህ ለያቸው፥ ለመታረድም ቀን አዘጋጃቸው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 እግዚአብሔር ሆይ! እኔን ግን ታውቀኛለህ፤ ስለ አንተ ያለኝን አስተሳሰብ አይተህ ትፈትነኛለህ፤ እነዚህን ክፉ ሰዎች እንደሚታረዱ በጎች ውሰዳቸው፤ ለዕርድም ቀን ለይተህ አቈያቸው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 አንተ ግን፥ አቤቱ፥ አውቀኸኛል፥ አይተኸኛል፥ ልቤንም በፊትህ ፈትነሃል፥ እንደ በጎች ለመታረድ ጐትተህ ለያቸው፥ ለመታረድም ቀን አዘጋጃቸው። See the chapter |