Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 11:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ጌታ ሆይ! አስ​ታ​ው​ቀኝ፤ እኔም አው​ቃ​ለሁ፤ ያን​ጊ​ዜም ሥራ​ቸ​ውን ገለ​ጥ​ህ​ልኝ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 እግዚአብሔር ስውር ዕቅዳቸውን ገለጠልኝ፤ እኔም ዐወቅሁ፤ በዚያ ጊዜ ሥራቸውን አሳይቶኝ ነበርና።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ጌታም አስታወቀኝ እኔም አወቅሁ፤ ሥራቸውንም ገለጥህልኝ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 በዚያን ጊዜ እነርሱ የሚያደርጉትን ነገር እግዚአብሔር ስላሳየኝ ሤራቸውን ዐወቅሁት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 እግዚአብሔርም አስታወቀኝ እኔም አወቅሁ፥ ሥራቸውንም ገለጥህልኝ።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 11:18
8 Cross References  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እው​ነት በእኔ ሐሰ​ተ​ና​ነት ለክ​ብሩ ከፍ ከአለ እን​ግ​ዲህ እኔን እንደ ኀጢ​አ​ተና ለምን ይፈ​ር​ድ​ብ​ናል?


እኔም ለመ​ታ​ረድ እን​ደ​ሚ​ነዳ እንደ የዋህ ጠቦት በግ ሆንሁ፤ እነ​ር​ሱም በእ​ን​ጀ​ራው ዕን​ጨት እን​ጨ​ምር ስሙም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ እን​ዳ​ይ​ታ​ሰብ ከሕ​ያ​ዋን ምድር እና​ጥ​ፋው ብለው ክፉ ምክ​ርን እን​ዳ​ሰ​ቡ​ብኝ አላ​ወ​ቅ​ሁም ነበር።


ማንም አንዳች ቢላችሁ ‘ለጌታ ያስፈልጉታል፤’ በሉ፤ ወዲያውም ይሰዳቸዋል።”


ኤል​ሳዕ ግን በቤቱ ተቀ​ምጦ ነበር፤ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችም ከእ​ርሱ ጋር ተቀ​ም​ጠው ነበር፤ ንጉ​ሡም በፊቱ ከሚ​ቆ​ሙት አንድ ሰው ላከ፤ መል​እ​ክ​ተ​ኛ​ውም ገና ሳይ​ደ​ርስ ለሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎች፥ “ይህ የነ​ፍሰ ገዳይ ልጅ ራሴን ይቈ​ርጥ ዘንድ እንደ ላከ እዩ፤ መል​እ​ክ​ተ​ኛ​ውም በመጣ ጊዜ ደጁን ዘግ​ታ​ችሁ ከል​ክ​ሉት፤ በደ​ጅም ይቆም ዘንድ ተዉት፤ የጌ​ታው የእ​ግሩ ኮቴ በኋ​ላው ነው” አላ​ቸው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements