Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 1:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ሁለ​ተ​ኛም ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ መጣ፤ እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “ምን ታያ​ለህ?” እኔም፥ “የሚ​ፈላ አፍ​ላል አያ​ለሁ፤ ፊቱም ወደ ሰሜን ወገን ነው” አልሁ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ዳግመኛም የእግዚአብሔር ቃል፣ “ምን ታያለህ?” ሲል ወደ እኔ መጣ። እኔም፣ “አንድ የሚፈላ ማሰሮ አያለሁ፤ አፉም ከሰሜን ወደዚህ ያዘነበለ ነው” አልሁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ሁለተኛም ጊዜ የጌታ ቃል “ምን ታያለህ?” ሲል ወደ እኔ መጣ። እኔም “የሚፈላ የሸክላ ድስት ከሰሜን ፊቱን አዘንብሎ አያለሁ” አልሁ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እንደገናም እግዚአብሔር “ሌላስ የምታየው ነገር ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀኝ። እኔም “በስተ ሰሜን በኩል አንድ ማሰሮ ሲፈላ አያለሁ፤ ወደዚህም ለመገልበጥ አዘንብሎአል” ስል መለስኩለት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ሁለተኛም ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል፦ ምን ታያለህ? እያለ ወደ እኔ መጣ። እኔም፦ የሚፈላ አፍላል አያለሁ፥ ፊቱም ከሰሜን ወገን ነው አልሁ።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 1:13
10 Cross References  

ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በመ​ካ​ከ​ልዋ ያኖ​ራ​ች​ኋ​ቸው ግዳ​ዮ​ቻ​ችሁ እነ​ርሱ ሥጋ ናቸው፤ ይህ​ችም ከተማ ድስት ናት፤ እና​ን​ተን ግን ከመ​ካ​ከ​ልዋ አወ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ።


እነ​ር​ሱም፦ በውኑ ቤቶች በድ​ን​ገት የሚ​ሠሩ አይ​ደ​ለ​ምን? ይህች ከተማ ድስት እኛም ሥጋ ነን ብለ​ዋል።


እርሱም፦ የምታየው ምንድር ነው? አለኝ። እኔም፦እነሆ፥ ሁለንተናው ወርቅ የሆነውን መቅረዝ አየሁ፣ የዘይትም ማሰሮ በራሱ ላይ ነበረ፥ ሰባትም መብራቶች ነበሩበት፣ በራሱም ላይ ለነበሩት መብራቶች ሰባት ቧንቧዎች ነበሩአቸው።


ሕል​ሙም ለፈ​ር​ዖን ደጋ​ግሞ መታ​የቱ ነገሩ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ቈ​ረጠ ስለ​ሆነ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፈጥኖ ያደ​ር​ገ​ዋል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ኤር​ም​ያስ ሆይ! የም​ታ​የው ምን​ድን ነው?” አለኝ። እኔም፥ “በለ​ስን አያ​ለሁ፤ እጅግ መል​ካም የሆነ መል​ካም በለስ፥ ከክ​ፋ​ቱም የተ​ነሣ ይበላ ዘንድ የማ​ይ​ቻል እጅግ ክፉ የሆነ ክፉ በለስ ነው” አልሁ።


ከአፌ የሚ​ወጣ ቃሌ እን​ዲሁ ነው፤ የም​ሻ​ውን እስ​ኪ​ያ​ደ​ርግ ድረስ ወደ እኔ በከ​ንቱ አይ​መ​ለ​ስም፤ መን​ገ​ዴ​ንና ትእ​ዛ​ዜን አከ​ና​ው​ና​ለሁ።


ስለ​ዚህ በላ​ቸው፥ “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የም​ና​ገ​ረው ቃል ይፈ​ጸ​ማል እንጂ ከቃሌ ሁሉ ደግሞ የሚ​ዘ​ገይ የለም፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እር​ሱም፥ “አሞጽ ሆይ! የም​ታ​የው ምን​ድን ነው?” አለኝ። እኔም፥ “የቃ​ር​ሚያ ፍሬ የሞ​ላ​በት ዕን​ቅብ ነው” አል​ሁት። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፥ “ፍጻሜ በሕ​ዝቤ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ መጥ​ቶ​አል፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ደግሞ ይቅር አል​ላ​ቸ​ውም።


Follow us:

Advertisements


Advertisements