Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 1:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ትን እፈ​ጽ​መው ዘንድ እተ​ጋ​ለ​ሁና መል​ካም አይ​ተ​ሃል” አለኝ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 እግዚአብሔርም፣ “ትክክል አይተሃል፤ ቃሌን እፈጽመው ዘንድ እተጋለሁና” አለኝ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ጌታም “ቃሌን ልፈጽመው ነቅቼ እየጠበቅሁ ነኝና መልካም አይተሃል” አለኝ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እግዚአብሔርም “በትክክል አይተሃል፤ እኔም እንዲሁ ቃሌ እንዴት ተግባራዊ እንደሚሆን አተኵሬ እመለከታለሁ” አለኝ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 እግዚአብሔርም፦ እፈጽመው ዘንድ በቃሌ እተጋለሁና መልካም አይተሃል አለኝ።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 1:12
15 Cross References  

ስለ​ዚህ በላ​ቸው፥ “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የም​ና​ገ​ረው ቃል ይፈ​ጸ​ማል እንጂ ከቃሌ ሁሉ ደግሞ የሚ​ዘ​ገይ የለም፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ እና​ገ​ራ​ለሁ፤ የም​ና​ገ​ረ​ውም ቃል ይፈ​ጸ​ማል፤ ደግ​ሞም አይ​ዘ​ገ​ይም፤ እና​ንተ ዐመ​ፀኛ ቤት ሆይ! በዘ​መ​ና​ችሁ ቃሌን እና​ገ​ራ​ለሁ፤ እፈ​ጽ​መ​ው​ማ​ለሁ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “መል​ካም መል​ሰ​ሃል፤ እን​ዲሁ አድ​ርግ፤ ትድ​ና​ለ​ህም” አለው።


እር​ሱም፥ “አሞጽ ሆይ! የም​ታ​የው ምን​ድን ነው?” አለኝ። እኔም፥ “የቃ​ር​ሚያ ፍሬ የሞ​ላ​በት ዕን​ቅብ ነው” አል​ሁት። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፥ “ፍጻሜ በሕ​ዝቤ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ መጥ​ቶ​አል፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ደግሞ ይቅር አል​ላ​ቸ​ውም።


“በተ​ና​ገ​ራ​ች​ሁ​ኝም ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ና​ን​ተን ቃል ድምፅ ሰማ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፦ ይህ ሕዝብ የተ​ና​ገ​ሩ​ህን ቃል ድምፅ ሰም​ቼ​አ​ለሁ፤ የተ​ና​ገ​ሩህ ሁሉ ትክ​ክል ነው።


በፍ​ርድ ቀን እበ​ቀ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እግ​ራ​ቸው በሚ​ሰ​ና​ከ​ል​በት ጊዜ፥ የጥ​ፋ​ታ​ቸው ቀን ቀር​ቦ​አ​ልና፥ የተ​ዘ​ጋ​ጀ​ላ​ች​ሁም ፈጥኖ ይደ​ር​ስ​ባ​ች​ኋ​ልና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፦ ለአ​ንተ የተ​ና​ገ​ሩት ሁሉ ልክ ነው።


ከጻ​ፎ​ችም ወገን የሆኑ ሰዎች፥ “መም​ህር ሆይ፥ መል​ካም ብለ​ሃል” ብለው መለሱ።


እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ አፈ​ር​ሳ​ቸ​ውና ክፉ አደ​ር​ግ​ባ​ቸው ዘንድ እንደ ተጋ​ሁ​ባ​ቸው፥ እን​ዲሁ እሠ​ራ​ቸ​ውና እተ​ክ​ላ​ቸው ዘንድ እተ​ጋ​ለሁ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ሁለ​ተ​ኛም ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ መጣ፤ እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “ምን ታያ​ለህ?” እኔም፥ “የሚ​ፈላ አፍ​ላል አያ​ለሁ፤ ፊቱም ወደ ሰሜን ወገን ነው” አልሁ።


ከአፌ የሚ​ወጣ ቃሌ እን​ዲሁ ነው፤ የም​ሻ​ውን እስ​ኪ​ያ​ደ​ርግ ድረስ ወደ እኔ በከ​ንቱ አይ​መ​ለ​ስም፤ መን​ገ​ዴ​ንና ትእ​ዛ​ዜን አከ​ና​ው​ና​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ኤር​ም​ያስ ሆይ! የም​ታ​የው ምን​ድን ነው?” አለኝ። እኔም፥ “በለ​ስን አያ​ለሁ፤ እጅግ መል​ካም የሆነ መል​ካም በለስ፥ ከክ​ፋ​ቱም የተ​ነሣ ይበላ ዘንድ የማ​ይ​ቻል እጅግ ክፉ የሆነ ክፉ በለስ ነው” አልሁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements