Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ያዕቆብ 2:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 አባታችን አብርሃም ልጁን ይስሐቅን በመሠዊያው ባቀረበ ጊዜ በሥራ የጸደቀ አልነበረምን?

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 አባታችን አብርሃም ልጁን ይሥሐቅን በመሠዊያው ላይ ባቀረበ ጊዜ በሥራ የጸደቀ አልነበረምን?

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 አባታችን አብርሃም ልጁን ይስሐቅን በመሠዊያው ላይ ባቀረበ ጊዜ በሥራ የጸደቀ አልነበረምን?

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 አባታችን አብርሃም ልጁን ይስሐቅን በመሠዊያው ላይ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርጎ ባቀረበው ጊዜ የጸደቀው በሥራ አይደለምን?

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 አባታችን አብርሃም ልጁን ይስሐቅን በመሠዊያው ባቀረበ ጊዜ በሥራ የጸደቀ አልነበረምን?

See the chapter Copy




ያዕቆብ 2:21
21 Cross References  

እነ​ር​ሱም መል​ሰው፥ “የእ​ኛስ አባ​ታ​ችን አብ​ር​ሃም ነው” አሉት፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የአ​ብ​ር​ሃም ልጆች ብት​ሆ​ኑስ የአ​ብ​ር​ሃ​ምን ሥራ በሠ​ራ​ችሁ ነበር።


ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለዘሩ የሰ​ጠው ተስፋ የታ​መነ ይሆን ዘንድ፥ የሚ​ጸ​ድቁ በእ​ም​ነት እንጂ የኦ​ሪ​ትን ሥራ በመ​ፈ​ጸም ብቻ እን​ዳ​ይ​ደለ ያውቁ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽድ​ቅን በእ​ም​ነት አደ​ረገ።


ከቃልህ የተነሣ ትጸድቃለህና ከቃልህም የተነሣ ትኰነናለህ።”


ሰው በእምነት ብቻ ሳይሆን በሥራ እንዲጸድቅ ታያላችሁ።


ነገር ግን አንድ ሰው “አንተ እምነት አለህ እኔም ሥራ አለኝ፤ እምነትህን ከሥራህ ለይተህ አሳየኝ፤ እኔም እምነቴን በሥራዬ አሳይሃለሁ፤” ይላል።


ለተ​ገ​ዘ​ሩ​ትም አባት ይሆን ዘንድ ነው፤ ነገር ግን ለተ​ገ​ዘ​ሩት ብቻ አይ​ደ​ለም፤ እርሱ አባ​ታ​ችን አብ​ር​ሃም ሳይ​ገ​ዘር እንደ አመነ ሳይ​ገ​ዘሩ የአ​ባ​ታ​ችን የአ​ብ​ር​ሃ​ምን የሃ​ይ​ማ​ኖ​ቱን ፍለጋ ለሚ​ከ​ተሉ ደግሞ ነው እንጂ።


እን​ግ​ዲህ በሥጋ የቀ​ድሞ አባ​ታ​ችን የሆ​ነው አብ​ር​ሃም ምን አገኘ እን​ላ​ለን? ይህን በሥ​ራው አግ​ኝ​ቶ​አ​ልን?


ከኦ​ሪት የተ​ነሣ ኀጢ​አት ስለ ታወ​ቀች ሰው ሁሉ የኦ​ሪ​ትን ሥር​ዐት በመ​ፈ​ጸም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አይ​ጸ​ድ​ቅም።


እር​ሱም እን​ዲህ አለ፥ “ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ንና አባ​ቶ​ቻ​ችን ሆይ፥ ስሙ፤ የክ​ብር አም​ላክ ለአ​ባ​ታ​ችን ለአ​ብ​ር​ሃም በሁ​ለት ወን​ዞች መካ​ከል ሳለ ወደ ካራ​ንም ሳይ​መጣ ተገ​ለ​ጠ​ለት።


በውኑ ከሞ​ተው ከአ​ባ​ታ​ችን ከአ​ብ​ር​ሃም፥ አንተ ትበ​ል​ጣ​ለ​ህን? ነቢ​ያ​ትም ሞቱ፤ ራስ​ህን ማን ታደ​ር​ጋ​ለህ?”


እር​ሱም፦ ‘የለም፤ አባት አብ​ር​ሃም ሆይ፥ ከሙ​ታን አንዱ ወደ እነ​ርሱ ካል​ሄ​ደና ካል​ነ​ገ​ራ​ቸው ንስሓ አይ​ገ​ቡም’ አለው።


‘አባት አብ​ር​ሃም ሆይ፥ እዘ​ን​ልኝ፤ በዚች እሳት እጅግ ተሠ​ቃ​ይ​ቻ​ለ​ሁና፥ ጣቱን ከውኃ ነክሮ ምላ​ሴን ያቀ​ዘ​ቅ​ዝ​ልኝ ዘንድ አል​ዓ​ዛ​ርን ላከው’ ብሎ ተጣራ።


ለአ​ባ​ታ​ችን ለአ​ብ​ር​ሃም የማ​ለ​ውን መሐላ ያስብ ዘንድ።


በልባችሁም ‘አብርሃም አባት አለን’ እንደምትሉ አይምሰላችሁ፤ እላችኋለሁና ከነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆች ሊያስነሣለት እግዚአብሔር ይችላል።


ወደ አባ​ታ​ችሁ ወደ አብ​ር​ሃም፥ ወደ ወለ​ደ​ቻ​ች​ሁም ወደ ሳራ ተመ​ል​ከቱ፤ አንድ ብቻ​ውን በሆነ ጊዜ ጠራ​ሁት፤ ባረ​ክ​ሁ​ትም፤ ወደ​ድ​ሁ​ትም፤ አበ​ዛ​ሁ​ትም።


የሚ​ም​ረኝ፥ መሸ​ሸ​ጊ​ያዬ፥ መጠ​ጊ​ያ​ዬና አዳኜ፤ መታ​መ​ኛ​ዬም፤ እር​ሱን ታመ​ንሁ፤ ሕዝ​ቡ​ንም ከእኔ በታች የሚ​ያ​ስ​ገ​ዛ​ልኝ።


አባ​ታ​ች​ሁ​ንም አብ​ር​ሃ​ምን ከወ​ንዝ ማዶ ወስጄ በከ​ነ​ዓን ምድር ሁሉ መራ​ሁት፤ ዘሩ​ንም አበ​ዛሁ፤ ይስ​ሐ​ቅ​ንም ሰጠ​ሁት።


አብ​ር​ሃ​ምም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፈ​ተ​ነው ጊዜ ልጁን ይስ​ሐ​ቅን ይሠ​ዋው ዘንድ በእ​ም​ነት ወሰ​ደው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements