Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢሳይያስ 41:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 አንተ ከም​ድር ዳርቻ የያ​ዝ​ሁህ፥ ከማ​ዕ​ዘ​ን​ዋም የጠ​ራ​ሁህ ነህና፦ አንተ ባሪ​ያዬ ነህ፤ መር​ጬ​ሃ​ለሁ፤ አል​ጥ​ል​ህም፤ ያል​ሁህ ሆይ፥

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ከምድር ዳርቻ ያመጣሁህ፣ ከአጥናፍም የጠራሁህ፣ ‘አንተ ባሪያዬ ነህ’ ያልሁህ፤ መረጥሁህ እንጂ አልጣልሁህም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 አንተ ከምድር ዳርቻ የያዝሁህ ከማዕዘንዋም የጠራሁህና፦ “አንተ አገልጋዬ ነህ፥ መርጬሃለሁ፥ አልጥልህም!” ያልሁህ፥

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ከምድር ዳርቻ አመጣሁህ፥ ከአራቱም ማእዘን ጠራሁህ፤ ‘አገልጋዬ ትሆናለህ’ ብዬ መረጥኩህ እንጂ አልጣልኩህም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 አንተ ከምድር ዳርቻ የያዝሁህ ከማዕዘንዋም የጠራሁህና፦ አንተ ባሪያዬ ነህ መርጬሃለሁ አልጥልህም ያልሁህ ሆይ፥

See the chapter Copy




ኢሳይያስ 41:9
23 Cross References  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ርሱ ሕዝብ ያደ​ር​ጋ​ችሁ ዘንድ ተቀ​ብ​ሎ​አ​ች​ኋ​ልና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ታላቅ ስሙ ሕዝ​ቡን አይ​ተ​ውም።


የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ስሙ፤ እግዚአብሔር በእምነት ባለ ጠጎች እንዲሆኑ ለሚወዱትም ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን መንግሥት እንዲወርሱ የዚህን ዓለም ድኾች አልመረጠምን?


“መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል ታርደሃልና፤ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ፥ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፤ በምድርም ላይ ይነግሣሉ፤” እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።


ከም​ሥ​ራ​ቅና ከም​ዕ​ራብ፥ ከሰ​ሜ​ንና ከደ​ቡብ ይመ​ጣሉ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ግ​ሥት በማ​ዕድ ይቀ​መ​ጣሉ፤


ባሪ​ያዬ እስ​ራ​ኤል፥ የመ​ረ​ጥ​ሁህ ያዕ​ቆብ፥ የወ​ዳጄ የአ​ብ​ር​ሃም ዘር ሆይ፥


ከም​ሥ​ራቅ ጽድ​ቅን ያስ​ነሣ፥ ይከ​ተ​ለ​ውም ዘንድ ወደ እግሩ የጠ​ራው ማን ነው? በአ​ሕ​ዛ​ብና በነ​ገ​ሥ​ታት ፊት ድን​ጋ​ጤን ያመ​ጣል። ጦሮ​ቻ​ቸ​ውን በም​ድር ያስ​ጥ​ላ​ቸ​ዋል፤ ቀስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም እንደ ገለባ ይረ​ግ​ፋሉ።


ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አንተ ቅዱስ ሕዝብ ነህና፥ በም​ድ​ርም ላይ ከሚ​ኖሩ አሕ​ዛብ ሁሉ ይልቅ ለእ​ርሱ ለራሱ ሕዝብ ትሆ​ን​ለት ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አን​ተን መር​ጦ​አ​ልና።


እርሱ ብቻ​ውን ታላቅ ተአ​ም​ራ​ትን ያደ​ረገ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤


በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ ከአ​ሦ​ርና ከግ​ብፅ፥ ከባ​ቢ​ሎ​ንና ከኢ​ት​ዮ​ጵያ፥ ከኤ​ላ​ሜ​ጤን፥ ከም​ሥ​ራ​ቅና ከም​ዕ​ራብ ለቀ​ሩት ለሕ​ዝቡ ቅሬታ ይቀና ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ገና እጁን ይገ​ል​ጣል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያዕ​ቆ​ብን ይም​ረ​ዋል፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ደግሞ ይመ​ር​ጠ​ዋል፤ በሀ​ገ​ራ​ቸ​ውም ያር​ፋሉ፤ መጻ​ተ​ኞ​ችም ከእ​ነ​ርሱ ጋር አንድ ይሆ​ናሉ፤ ከያ​ዕ​ቆ​ብም ቤት ጋር ይጨ​መ​ራሉ።


እነሆ፥ ደግፌ የያ​ዝ​ሁት ባሪ​ያዬ ያዕ​ቆብ፤ ነፍሴ የተ​ቀ​በ​ለ​ችው ምርጤ እስ​ራ​ኤ​ልም፤ በእ​ርሱ ላይ መን​ፈ​ሴን አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ፤ እር​ሱም ለአ​ሕ​ዛብ ፍር​ድን ያመ​ጣል።


አሁ​ንም ባሪ​ያዬ ያዕ​ቆብ የመ​ረ​ጥ​ሁ​ህም እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ ስማ።


ስለ አገ​ል​ጋዬ ስለ ያዕ​ቆብ፥ ስለ መረ​ጥ​ሁ​ትም ስለ እስ​ራ​ኤል ብዬ በስ​ምህ ጠር​ቼ​ሃ​ለሁ፤ ተቀ​በ​ል​ሁ​ህም፤ አንተ ግን አላ​ወ​ቅ​ኸ​ኝም።


ወድጃችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፣ እናንተ ግን፦ በምን ወደድኸን? ብላችኋል። ዔሳው የያዕቆብ ወንድም አልነበረምን? ይላል እግዚአብሔር ያዕቆብንም ወደድሁ፥ ዔሳውንም ጠላሁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements