Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሆሴዕ 8:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 አም​ላክ ሆይ! እኛ እስ​ራ​ኤል ዐወ​ቅ​ንህ ብለው ወደ እኔ ይጮ​ኻሉ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 እስራኤልም፣ ‘አምላካችን ሆይ፤ እኛ እናውቅሃለን!’ እያሉ፣ ወደ እኔ ይጮኻሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 እነርሱም፦ “አምላክ ሆይ! እኛ እስራኤል እናውቅሃለን!” ብለው ወደ እኔ ጮሁ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 እነርሱም፥ “አምላክ ሆይ! እኛ ሕዝብህ እናውቅሃለን” እያሉ ወደ እኔ ይጮኻሉ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 እነርሱም፦ አምላክ ሆይ፥ እኛ እስራኤል አወቅንህ ብለው ወደ እኔ ይጮኻሉ።

See the chapter Copy




ሆሴዕ 8:2
14 Cross References  

እግዚአብሔርን እንዲያውቁ በግልጥ ይናገራሉ፤ ዳሩ ግን የሚያስጸይፉና የማይታዘዙ ለበጎ ሥራም ሁሉ የማይበቁ ስለ ሆኑ፥ በሥራቸው ይክዱታል።


በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ ‘ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ!’ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም።


አውቄዋለሁ የሚል ትእዛዛቱንም የማይጠብቅ ውሸተኛ ነው እውነትም በእርሱ ውስጥ የለም።


ባለ​ቤቱ ተነ​ሥቶ ደጁን ይዘ​ጋ​ልና፤ ያን​ጊዜ ከደጅ ቆመው፦ ‘አቤቱ፥ አቤቱ፥ ክፈ​ት​ልን’ እያሉ በር ሊመቱ ይጀ​ም​ራሉ፤ መል​ሶም፦ ከወ​ዴት እንደ ሆና​ችሁ አላ​ው​ቃ​ች​ሁም ይላ​ቸ​ዋል።


በኋላም ደግሞ የቀሩቱ ቈነጃጅት መጡና ‘ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ! ክፈትልን፤’ አሉ።


አለቆችዋ በጉቦ ይፈርዳሉ፥ ካህናቶችዋም በዋጋ ያስተምራሉ፥ ነቢያቶችዋም በገንዘብ ያምዋርታሉ፥ ከዚህም ጋር፦ እግዚአብሔር በመካከላችን አይደለምን? ክፉ ነገር ምንም አይመጣብንም እያሉ በእግዚአብሔር ይታመናሉ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ ይህ ነው እያ​ላ​ችሁ በሐ​ሰት ቃል በራ​ሳ​ችሁ አት​ታ​መኑ።


ነገር ግን እስ​ራ​ኤ​ልን ካሳ​ተው ከና​ባጥ ልጅ ከኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ኀጢ​አት ኢዩ አል​ራ​ቀም፥ በቤ​ቴ​ልና በዳን የነ​በ​ሩ​ትን የወ​ርቅ እን​ቦ​ሶ​ች​ንም፥ አላ​ስ​ወ​ገ​ደም።


“ከእኔ ጋር ና፥ ለሠ​ራ​ዊት ጌታ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ደ​ም​ቀና ታያ​ለህ” አለው። ከእ​ር​ሱም ጋር በሰ​ረ​ገ​ላው አስ​ቀ​መ​ጠው።


እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ፥ ፊቴ​ንም እስ​ኪሹ ድረስ እሄ​ዳ​ለሁ፤ ወደ ስፍ​ራ​ዬም እመ​ለ​ሳ​ለሁ።


እስ​ራ​ኤል ደግ​ነ​ቱን ጥሎ​አ​ልና፤ ጠላ​ትም ያሳ​ድ​ደ​ዋ​ልና።


Follow us:

Advertisements


Advertisements