Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሆሴዕ 13:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ስለ​ዚ​ህም እንደ ማለዳ ደመና፥ በጥ​ዋት እን​ደ​ሚ​ያ​ልፍ ጠል፥ በዐ​ውሎ ነፋ​ስም ከዐ​ው​ድማ እን​ደ​ሚ​በ​ተን እብቅ፥ ከም​ድ​ጃም እን​ደ​ሚ​ወጣ ጢስ ይሆ​ናሉ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ስለዚህ እንደ ማለዳ ጉም፣ ፈጥኖ እንደሚጠፋ የጧት ጤዛ፣ ከዐውድማ እንደሚጠረግ እብቅ፣ በመስኮትም እንደሚወጣ ጢስ ይሆናሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ስለዚህም እንደ ማለዳ ደመና፥ በጥዋትም እንደሚያልፍ ጠል፥ በዐውሎ ነፍስም ከአውድማ እንደሚበተን እብቅ፥ ከመስኮትም እንደሚወጣ ጢስ ይሆናሉ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 በዚህም ምክንያት እነርሱ እንደ ማለዳ ጉም ተነው ይጠፋሉ፤ እንደ ጠዋት ጤዛም ይረግፋሉ፤ ከአውድማ ላይ በዐውሎ ነፋስ እንደሚጠረግ እብቅ ወይም በጢስ መውጫ ወጥቶ እንደሚያልቅ ጢስ ይሆናሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ስለዚህም እንደ ማለዳ ደመና፥ በጥዋትም እንደሚያልፍ ጠል፥ በዐውሎ ነፍስም ከአውድማ እንደሚበተን እብቅ፥ ከመስኮትም እንደሚወጣ ጢስ ይሆናሉ።

See the chapter Copy




ሆሴዕ 13:3
11 Cross References  

“ምሕ​ረ​ታ​ችሁ እንደ ማለዳ ደመና፥ በማ​ለ​ዳም እን​ደ​ሚ​ያ​ልፍ ጠል ነውና ኤፍ​ሬም ሆይ! ምን ላድ​ር​ግ​ልህ? ይሁዳ ሆይ! ምን ላድ​ር​ግ​ልህ?


ኃጥ​ኣን እን​ዲህ አይ​ደ​ሉም፥ እን​ዲህ አይ​ደ​ሉም። ነገር ግን ነፋስ ከገጸ ምድር ጠርጎ እን​ደ​ሚ​ወ​ስ​ደው ትቢያ ናቸው።


በጥ​ልቅ ረግ​ረግ ጠለ​ቅሁ ኀይ​ልም የለ​ኝም፤ ወደ ጥልቁ ባሕ​ርም ደረ​ስሁ ማዕ​በ​ሉም አሰ​ጠ​መኝ።


ብዙ​ዎች አሕ​ዛብ እንደ ብዙ ውኃ ናቸው፤ ከፏ​ፏቴ ውስጥ በኀ​ይል እን​ደ​ሚ​ወ​ርድ እንደ ብዙ ውኃ ፈሳሽ ይጮ​ኻሉ፤ ያጠ​ፉ​ታ​ልም፤ እነ​ር​ሱም ከሩቅ ይወ​ር​ዳሉ፤ በተ​ራ​ራም ላይ እን​ዳለ እብቅ፥ በነ​ፋስ ፊት ዐውሎ ነፋስ እን​ደ​ሚ​ያ​ዞ​ረው እንደ መን​ኰ​ራ​ኵር ትቢ​ያም ይበ​ተ​ናሉ።


በነ​ፋ​ስም ፊት እንደ ገለባ፥ አውሎ ነፋ​ስም እን​ደ​ሚ​ወ​ስ​ደው ትቢያ ይሆ​ናሉ።


ድን​ጋጤ በላዬ ተመ​ላ​ለ​ሰ​ች​ብኝ፥ ነፍሴ ከእኔ ላይ እለይ እለይ አለች፥ ደኅ​ን​ነ​ቴም እንደ ተበ​ተነ ደመና አለ​ፈች።


ነገር ግን ሰላምን እዘራለሁ፣ ወይኑ ፍሬውን ይሰጣል፥ ምድርም አዝመራዋን ታወጣለች፥ ሰማያትም ጠላቸውን ይሰጣሉ፣ ለዚህም ሕዝብ ቅሬታ ይህን ነገር ሁሉ አወርሳለሁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements