Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሆሴዕ 1:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ደግሞ ፀነ​ሰች፤ ሴት ልጅ​ንም ወለ​ደች። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “መለ​የ​ትን እለ​ያ​ቸ​ዋ​ለሁ እንጂ ይቅር እላ​ቸው ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቤት ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አል​ም​ራ​ቸ​ው​ምና ስም​ዋን ኢሥ​ህ​ልት ብለህ ጥራት፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ጎሜር እንደ ገና ፀነሰች፤ ሴት ልጅም ወለደች፤ እግዚአብሔርም ሆሴዕን እንዲህ አለው፤ “ይቅር እላቸው ዘንድ ለእስራኤል ቤት ከእንግዲህ ስለማልራራላቸው፣ ስሟን ሎሩሃማ ብለህ ጥራት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ዳግመኛም ፀነሰች ሴት ልጅም ወለደች። ጌታም እንዲህ አለው፦ “የእስራኤልን ቤት ፈጽሞ ይቅር እንድላቸው ከእንግዲህ ወዲህ ርኅራኄ የለኝምና ስምዋን ሎሩሃማ ብለህ ጥራት፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ጎሜር ዳግመኛ ፀንሳ ሴት ልጅ ወለደች፤ እግዚአብሔርም ሆሴዕን እንዲህ አለው፦ “ለእስራኤል ሕዝብ ከእንግዲህ ወዲህ ፍቅር አላሳያቸውም፤ ይቅርታም አላደርግላቸውም፤ ስለዚህ የልጅህን ስም ‘ሎሩሐማ’ ብለህ ጥራት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ደግሞ ፀነሰች ሴት ልጅንም ወለደች። እግዚአብሔርም፦ ይቅር እላቸው ዘንድ የእስራኤልን ቤት ከእንግዲህ ወዲህ አልምርምና ስምዋን ሎሩሃማ ብለህ ጥራት፥

See the chapter Copy




ሆሴዕ 1:6
11 Cross References  

እናንተ ቀድሞ ወገን አልነበራችሁም፤ አሁን ግን የእግዚአብሔር ወገን ናችሁ፤ እናንተ ምሕረት ያገኛችሁ አልነበራችሁም፤ አሁን ግን ምሕረትን አግኝታችኋል።


በም​ድ​ርም ላይ ለእኔ እዘ​ራ​ታ​ለሁ፤ ይቅ​ርታ የሌ​ላ​ትን ይቅር እላ​ታ​ለሁ፤ ያል​ተ​ወ​ደ​ደች የነ​በ​ረ​ች​ውን እወ​ድ​ዳ​ታ​ለሁ፤ ሕዝ​ቤም ያል​ሆ​ነ​ውን፥ “አንተ ሕዝቤ ነህ” እለ​ዋ​ለሁ፤ እር​ሱም፥ “አንተ ጌታ​ዬና አም​ላኬ ነህ” ይለ​ኛል።


የዝ​ሙት ልጆች ናቸ​ውና ልጆ​ች​ዋን ይቅር አል​ላ​ቸ​ውም።


በሆ​ሴ​ዕም በዘ​ጠ​ነ​ኛው ዓመት የአ​ሦር ንጉሥ ሰማ​ር​ያን ያዘ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ወደ አሶር አፈ​ለሰ፤ በአ​ላ​ሔና በአ​ቦር፤ በጎ​ዛ​ንም ወንዝ፤ በሜ​ዶ​ንም ከተ​ሞች አኖ​ራ​ቸው።


ዘግ​ይቶ ይደ​ር​ቃል፤ በው​ስ​ጡም ልም​ላሜ ሁሉ አይ​ገ​ኝም፤ ከቲ​ኣሳ የም​ት​መጡ ሴቶች፥ ኑና ለሕ​ዝቤ አል​ቅሱ፤ የማ​ያ​ስ​ተ​ውል ሕዝብ ነውና፤ ስለ​ዚህ ፈጣ​ሪው አይ​ራ​ራ​ለ​ትም፤ ሠሪ​ውም ምሕ​ረት አያ​ደ​ር​ግ​ለ​ትም።


ኢሥ​ህ​ል​ት​ንም ጡት ባስ​ጣ​ሏት ጊዜ፥ ደግሞ ፀነ​ሰች፤ ወንድ ልጅ​ንም ወለ​ደች።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ዘር ሁሉ ተቈጣ፤ አስ​ጨ​ነ​ቃ​ቸ​ውም፤ ከፊ​ቱም እስ​ኪ​ጥ​ላ​ቸው ድረስ በበ​ዝ​ባ​ዦች እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “አሞጽ ሆይ! የም​ታ​የው ምን​ድን ነው?” አለኝ። እኔም፥ “ቱንቢ ነው” አልሁ። ጌታም፥ “እነሆ! በሕ​ዝቤ በእ​ስ​ራ​ኤል መካ​ከል ቱንቢ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ ደግሞ ይቅር አል​ላ​ቸ​ውም።


እነሆ የጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐይ​ኖች በኀ​ጢ​አ​ተኛ መን​ግ​ሥት ላይ ናቸው፤ ከም​ድ​ርም ፊት አጠ​ፋ​ታ​ለሁ፤ ነገር ግን የያ​ዕ​ቆ​ብን ቤት ፈጽሜ አላ​ጠ​ፋም፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


Follow us:

Advertisements


Advertisements